የማለዳ ወግ …ዞን 9 ኞችን አደግፋለሁ !አግብቷቸው ስለጦመሩ መብታቸው መገፈፍ የለበትም

ነቢዩ ሲራክ
የማለዳ ወግ …ዞን 9 ኞችን አደግፋለሁ ! አግብቷቸው  ስለጦመሩ መብታቸው መገፈፍ የለበትም  !
ዞን 9 ኞችን አከብራቸዋለሁ ፣ እዎዳቸዋለሁ!” የሃገር የህዝባችን ጉዳይ ያገባናል !” በሚል በፖለቲካ ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ህይዎታችን ዙሪያ የሚያቀርቧቸው መጣጥፎች አስተማሪ ለመሆናቸው እማኝ ነኝ  !  ጦማርያኑ ቀፍድዶ ከያዘን ፍርሃት ወጥተን ህገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ ለመብታችን እንድንተጋ ማነቃቃታቸው ቢያስመሰግን እንጅ የሚያስኮንን ፣ የሚያስወግዝ ፣ ብሎም ወህኒ የሚያስወርድ ነው አልልም።ዞን 9 ኞችን የምንወድ የምንደግፍ  እኔና እኔን መሰሎች ጥቂቶች አይደለንም ። እልፍ አእላፎች ነን ። ቢያንስ እኔ በግል የወጣት ጦማርያኑ እንግልትና ጉዳት የሃገር  ጉዳት ነው ብየ አምናለሁ ። እልፍ  አእላፎች ጦማሪዎች ” ህገ መንግስቱን አልጣሱም “ስንል  ” ህገ መንግስቱ ይከበር ፣ ዞን 9ኞች ይፈቱ !” ዘንድ ድምጻችን ከፍ አድርገን እናሰማለን  !የዞን 9 ጦማርያን የመጻፍ የመናገር መብታቸውን ተጠቅመው ተደራጅተው በሰለጠነና በዘመነ አካሔድ ፍርሃት ዝምታችን ሰብረውልናል።ስለዚህም የሃገርና የህዝብ ድንቅ ልጆች እንጅ በጠላትነት ሊፈረጁ አይገባም። “የህዝብ የሃገር ጉዳይ ያገባናል!” ብለው ግንባራቸውን ለመስዋዕት የሰጡት ወጣቶች የህግ ከለላ ያስፈልጋቸዋል እንጅ ህግ እየተሸራረፈ መብታቸው መጣስ የለበትም።ዞን 9 ኞች የማይወዷቸው የማግፈልጓቸው ” ሃገርና ህዝብ በድለዋል ፣ በብዕራቸው ሰላም አደፍርሰዋል!” ካሉ  የተጨበጠ መረጃ ይዘው አይሞግቷቸው አልልም። ጉዳያቸው በህግ ማዕቀፍ ተመርምሮ እና የዋስ መብታቸው ተከብሮ ትክክለኛ ፍትህን ሊያገኙ  ይገባል። ይህ ሳይደረግ የሳሾቻቸው አቤቱታ ብቻ እየተሰማ ፣  ባልረባባ ምክንያት እየወነጀሉ ዞን 9ኞችን ሊያዳክሙና ከአደባባይ መድረኩ ሊያጠፏቸው አይገባም ። በዚህ ረገድ የፍትህ አካላት የሃገርንና የህዝብን ደህንነት ከማስጠበቁ ባልተናነሰ  የታዳጊ ወጣት ጦማሪዎችን መብት የማስጠበቅ ሰው የመሆን የሞራል ግዴታ አለባቸው  ! “የህዝበና የሃገር ጉዳይ ያገባናል!” ያልን ፍዳችን በዝቷል ። ያም ሆኖ ዝም አንልም ፣ ያገባናልና በአደጋ ተከበን እንጦምራለን  !  አዎ  ! ያገባናልና ! ሰላም … ነቢዩ ሲራክ
Sent from Samsung Mobile
zone-9-300×300.jpg

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.