ጠ/ሚ አቢይ አህመድ እውነቱን ተናግረው የመሸበት ይደሩ! (ሐይሉ አባይ ተገኝ)

በበታችነት ስሜት ያበዱና በግል ዝና የመቃተት በሽታ (Histrionic Personality Disorder) የሚሰቃዩ ኦነጋውያንን በቀን የታለመን ህልም ለመፍታት ሲባል የህዝብ ልጆችን ማሠቃየት ኢ-ሞራላዊ ብቻ ሳይሆን ወንጀል ነው።

ለ27 ዓመታት ሲገድሉ፣ ሕዝብን እርስ በርሱ ሲያጋጩና የዘር ጭፍጨፋን ሲተገብሩና ሲያስፈፅሙ የነበሩ የወያኔ ሽፍታዎችን “በሰላምና በፍቅር” ሥም ነፃ ለቆ፣ የቡራዩ ጨፍጫፊዎችን ያሰማሩ ጃዋርያን ጋር አንሶላ እየተጋፈፉና “ለአብላጫ ቁጥር አምባገነንነት” (tyranny of majority) ሥርዐት ዝግጅታቸው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረጉ ንፁሃን የአዲስ አበባ ወጣቶችን ያለሃጢያታቸው ያውም በጦላይ የጦር ሠፈር ወስዶ በወባ ማስነደፍ ሂትለር በተቃዋሚዎቹ ላይ አንትራክስ (anthrax) ከመርጨቱ ጋር በምን ይለያል? የወያኔ ሲራጅ ፈርቄሳና የጠ/ሚ አቢይ ዘይኑና ታዬ ደንደና የሚለያዩት በቁመት ብቻ ነው።

ጠ/ሚ አቢይ አህመድ ያስተውሉ!

ጊዜው የዲሞክራሲ እንጂ የጎጥና የጎሣ አምባገነንነት አይደለም። የፓለቲካ ሥልጣን የቀበሌ ሱቅ የስኳር ሠልፍ አይደለም። ሕዝቡ የደገፈዎት ለዴሞክራሲ ጥማቱ መንገድ ይከፍታሉ ብሎ እንጂ ጆርጅ ኦርዌልን ሆነው ሠው ዘቅዝቀው ከሚሠቅሉ እንሠሦች ጋር በመሆን “የእንሠሦችን ዐመፅ” እንዲያደራጁና ድርሣናትን እንዲፅፉልን አልነበረም። የህዳጣኖቹን የወያኔ አፓርታይዳዊ አገዛዝ”ለአብላጫ ቁጥር አምባገነንነት” (tyranny of majority)” እንዲተኩልን አልተማለድንም። “ለሚቀጥለው 3000 ዓመት እንገዛችኋለን” የሚሉንን የኦነግ ጭር ያሉና እንቁላል የማይጥሉ ዶሮዎች እንዲያስካኩብን አልነበረም።

ጠ/ሚ አቢይ የርስዎ “መደመር” የኦነግ ቅንቅን በልቶታል። ተፈጥሮዓዊ ሕግን ጥሰው በማዕቀፉ (Bracket) ውስጥ የማይታረቁ የ19ኛውና የ21ኛው ክፍለ ዘመን አስተሳሰቦችን፣ ቆሞ ቀር ፓለቲከኞችና የለውጥ ሃይሎችን፣ አይጥና ድመትን፣ ኢትዮጵያዊና ፀረ-ኢትዮጵያ ሃይሎችን እንዲሁም ጅብና አህያ አጉረው እንደ ስፓርታ ነገስታት እነዚህ የተቃርኖ ውህደቶች ሲናጩ የሚያሳይ ዘግናኝ ፊልም (Horror) እርስዎ እያዩ እኛንም እያስደመጡን ነው። ኢትዮጵያዊ ሙዚቃ ከፍተውልን ኦነጋዊ ዳንስ እንድንጨፍር አይጋብዙን። ይህ ላለፉት 50 ዓመታት የሠለቸንን ዳንስና ከኢትዮጵያዊነት ቅላፄ ጋር ስለማይሄድ እንደ ላቲን ፊደል አውሮፓ ሙዚየም ይላኩልን። “የብዝሃን ቁጥር አምባገነንነት (tyranny of majority)” የሆነው የኦነጋውያን ቅዠት እስኪደራጅ እኛን በኢትዮጵያዊነት ዘፈን አያደንቁሩን።

ሂትለር በማራኪ ንግግሩ (demagogues) የብዙ ጀርመናዊ ዜጎችን ድጋፍ አግኝቶ ቀጥሎም ለእልቂት ዳርጓቸዋል። የሂትለርን አስከፊ መንገድ ጀርመናውያን ለመረዳት ሺ ዓመት አልፈጀባቸውም። ኦነጋውያን የሚፈልጉትና የጠማቸው ነፃነትና መብት እንዲሁም ዴሞክራሲ ሣይሆን ለቀጣዩ 3000 ዓመት ስንቅ የሚሆናቸው የፓለቲካ ሥልጣን ነው።
የ”ተራው የኛ ነው” ፓለቲካቸው ግብ እስኪመታ ነው። ብዙ ጊዜ ባለተራ ነበሩ። ለምሣሌ ከአፄ ሚኒሊክ 13 ጀነራሎች ውስጥ 11፤ በአፄ ሃ/ስላሴ 75%፣ በደርግ ዘመን ኮ/ል መንግስቱን ጨምሮ ከቁጥር በላይ የሆኑና አስከፊውን “ቀይ ሽብር” መሐንዲስ የነበሩ ኦሮምኛ ተናጋሪ ባለስልጣኖች ነበሩ። እውነቱ ሂትለር ጀርመናውያንን ይገድል የነበረው ጀርመናዊ ስላልነበረ አልነበረም። ሂትለርም ስልጣን ላይ ስለነበረ ይገዙ የነበሩት ጀርመናውያን በሙሉም አልነበሩም። ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል!!

ዴሞክራሲያዊ ሽግግር በቅድሚያ የሚፈልገው ነፃና ገለልተኛ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ነው። ዴሞክራሲ የሚፈልገው ከዘር፣ ጎሣ፣ ፆታና ሃይማኖት ነፃ የሆኑ ድርጅቶችን ነው። ከመንግስታዊ የደህንነት፣ ቢሮክራሲና ወታደራዊ ተፅዕኖ ነፃ የሆነ የምርጫ ኮሚሽን ነው። በድርጅቶች መካከል የሚፈረም የመግባቢያ ሠነድ ነው። ይህ የለም።

አይቻልም እንጂ ቢቻል እንኳን ወደ ዴሞክራሲ የሚወስደው መንገድ “አብዮታዊ ዴሞክራሲና የጎሣ ፌደራሊዝም” እንዲሁም የጎሣ ፓለቲካ ብቻ ነው ብትሉኝ እስከወዲያኛው ዴሞክራሲን ላለማየት ያለጥርጥር እመርጣለሁ።

የመንገዳችንን ፍኖተ ካርታ፣ የምንጓዝበትንና የምንደርስበትን በአስቸኩዋይ ሊያሣዩን ካልፈለጉ እያዘጋጁን ያሉት የኦነጋውያን ጅቦች የሚያልሙትን “ለአብላጫ ቁጥር አምባገነንነት” (tyranny of majority)” ዝግጅት ነው ብዬ ለማመን እገደዳለሁ።

እኛ ኢትዮጵያውያን ማየት የምንፈልገው ዴሞክራሲያዊ ሥርዐትና የሕግ የበላይነት እንጂ “አብዮታዊ ዴሞክራሲና የጎሣ ፌደራሊዝም” ለሁለተኛ ባል የሚዳሩበትን ሠርግ ለመታደም አይደለም። ኢትዮጵያ ሐገራችን የህዳጣኖቹን የወያኔ አፓርታይዳዊ አገዛዝ ጋር ተፋታ “ከአብላጫ ቁጥር አምባገነንነት” (tyranny of majority)” በቤተሰብ ትዕዛዝ (arrange marriage) ስታገባ ማየት አይሆንም።

የፕሮፓጋንዳውን እውነትና ውሸት ተቀላቅሏል።
ክረስ ጃሚን ይህን ይጋብዝዎታል “አንድ ነገር ውሸት ባይሆንም አሣሳች አይደለም ማለት ግን አይቻልም። ውሸታም እንደሚዋሽ ያውቃል። ነገር ግን ሠዎችን ለማታለል ሲል አንዳንድ የእውነት ዘለላ እየጨመረ የሚያወራ የጥፋት ባለሙያና መሃንዲስ ነው”.

“አብዮታዊ ዴሞክራሲና የጎሣ ፌደራሊዝም” የወሰደን ወደ “ህዳጣኖቹን የወያኔ አፓርታይዳዊ አገዛዝ” አሁንም ይዞን መሄድ የፈለገው ወደ”ለአብላጫ ቁጥር አምባገነንነት” (tyranny of majority)” ነው። ስልቻን በቀልቀሎ ቀይረው ስለዴሞክራሲ አይንገሩን። ደቡብ ሱዳንን የቅርብ ማስረጃ ነው። እንደ ሐገር በዴሞክራሲያዊ ሥርዐት መኖር ካልቻልን እንደ ሕዝብ እንጠፋለን። ወደለየለትና ማብቂያ ከሌለው የርስበርስ ጦርነት እንገባለን።

ችግራችን የሚፈታው በዴሞክራሲና የሕግ የበላይነት እንጂ “ለአብላጫ ቁጥር አምባገነንነት” አይደለም!

ሞት ‘ለጎሣ ፌደራሊዝምና አብዮታዊ ዴሞክራሲ”!

#PrimeMinisterAbeiyAhmed

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.