ሰባተኛው ንጉሥ ጉድ አፈላ! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

ቀድሞ ማመስገን ለተከታይ ወቀሣ አመቺ አለመሆኑ ተዘውትሮ ይጠቀሳል፡፡ ቢሆንም የየዕለቱ ነባራዊ ሁኔታዎች ተለዋዋጭ እንደመሆናቸው በዚህ ነጥብ ረገድ ግትርነት ወይም ይሉኝታ አስፈላጊ አይደለምና እውነቱን ተናግሬ እመሸብኝ ማደርን መርጫለሁ፡፡ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አሊን ወደማምለክ ደረጃ የደረሳችሁ ሰዎች ታገሱኝ ወይንም ይህንን ጽሑፍ አታንብቡ፡፡ እኔም ላመልከው ደርሼ ነበርና በሀገራችን ሰውን ማምለክና ለሰው መስገድ ብርቅ አይደለም፡፡ ከቅዠት ቶሎ መንቃት ግን ከተጨማሪ ውርደትና ጥቃት ይታደጋል፡፡ አምልኮት መጥፎ ነው፤ ያሳውራል፤ ምክንያትንም ያጠፋል፡፡

ዐቢይ አህመድ አፈ ጮሌ ነው፡፡ የሰውን ስሜት ቀፍድዶ በመያዝ ጎበዝ ነው – I wish him a good job in hypnosis after his death in politics which will take place very soon. He is a nice hypnotizer. በሌላ በኩል ግን የሊቀ ሣጥናኤል መልእክተኛ መሆኑን ለመረዳት ብዙ ጊዜ ፈጅቶብኛል፡፡ አምላከ አማልክት ዶ/ር ዐቢይ የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ቀልብ የገዛው ገና ወደ ሥልጣን በመጣ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ነበር፡፡ ከነዚያ እርጉማን ደቂቃዎች ጀምሮ ሰማይና ምድር ለዚህ ብላቴና ተንበረከኩ፤ ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቹ በስተቀር ከሞላ ጎደል ሁሉም በፍቅሩ ተንበረከከ፡፡ ታማኝ በየነ ሰገደለት፤ ፕሮፌሰር አልማርያም ተማረከለት፤ ፕሮፌስር መስፍን አለወትሮው በፍቅሩ ወደቀለት፤ የሆነውን ሁሉ ማስታወስ ለቀባሪ ማርዳት ነውና ይቅር፡፡ (የውስጥ ጠላቱ ዘርን መሠረት አድርገው “ዛሬና ነገ የኛ ናቸው” ብለው በሥልጣን ጥም የታወሩ ነገን ግን በጭራሽ የማያውቁ ድኩማን አማካሪዎቹና የራሱ የሥልጣን ‹ኢጎ› ሲሆን የውጭ ጠላቶቹ ደግሞ ወያኔዎች ናቸው፡፡)

ዐቢይ መቼም ቢሆን አይሳካላቸውም እንጂ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሌት ከቀን የሚማስኑት ኢሉሚናቲዎች ወኪል ነው፡፡ ይህን የፈጠጠ ገሃድ እውነት ዐቢይ ራሱም ላያውቀው ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ ኢሕአፓ እንኳን ባቅሟ አፈ ጮሌንና በትምህርት ጎበዝ የሆነን ሕጻን ሳይቀር ትመለምል ነበር፡፡ ስለዚህም አደገኛ ምሥጢራዊ ቡድኖች (cabalists or secret societies such as the Illuminati and related satanic groups and organizations) በሕዝብ ዘንድ ተሰሚነትና ተወዳጅነት ያላቸውን ሰዎች በኅቡዕ በመመልመል ለዓላማቸው ሥሙርነት ማሰማራታቸው የተለመደና የታወቀ እንጂ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ በዐቢይ የምታመልኩ እንግዲህ ዕበዱ፤ እውነቱ አሁን የምለው ነው – ሌላ አይደለም፡፡

አፈቅቤ ልበ ጩቤው ዐቢይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎትና የልብ ትርታ ጥንቅቅ አድርጎ ያውቃል፡፡ ለራሱ ሳይኖር ለዚህ ብቻ ኖሯል፡፡ ብዙ አንብቧል፤ ብዙ ጽፏል፡፡ ለዚህ ልዩ ተሰጥዖውና ራሱ ያዳበረው አስደማሚ ችሎታው የዕድሜ ልክ አድናቂው ነኝ፡፡ ከመጻሕፍትም፣ ከሰውም፣ ከሕይወት ውጣ ውረድ ገጠመኝም ብዙ ተምሯል፡፡ ስለዚህም ነው ለራሱ ሳይኖር ለዓላማው ሲል ከዕድሜው በላይ ኖሯል የምለው፡፡ መለስም እኮ በዕውቀት አይታማም፡፡ ዐቢይ መለስን የበለጠው በትንሽ ነገር ነው – እኔም አንተም ልናደርገው በምንችለው መለስ ግን ዘግቶበት ባላደረገው ትንንሽ ነገር ዐቢይ መለስ ዜናዊን ዘረረው፡፡ በተራው ግን ዐቢይም በስድስት ወራት ውስጥ ተዘረረ – እምብዝም ስለት ይቀዳል አፎት ነው ነገሩ፤ “የማያድግ ልጅ በአባቱ ብልት ይጫወታል”ም ይባላል ዐቢይን መሰል አሰለጥ ለመተቸት፡፡ መለስስ በጭካኔው ከ20 ዓመታት በላይ በሥልጣን ቆይቷል፡፡ አሳዛኙ ዐቢይ ግን አንድ ዓመት የሚደፍን መሆኑ እጅግ ያጠራጥረኛል፡፡ መቼም ስድስት ሰዓት ከገዛው ከንጉሥ አዙር በልጧል፡፡ የሚገርም ነገር!!

በነገራችን ላይ “ከብዙ ትርምስና ሁከት በኋላ ለሦስት ወር ወይም ግፋ ቢል ለሦስት ዓመት አንድ የእስላም ንጉሥ ኢትዮጵያን ይገዛል” የተባለው ትንቢት ምናልባት ይህ ሰው ሊሆን እንደሚችል እጠራጠራለሁ፡፡ ሆነም አልሆነም የኢትዮጵያ ነፃ መውጣት የጊዜ ጉዳይ እንጂ እጅግ ተቃርቧል፤ ምልክቶቹ ሁሉ ታይተዋል፡፡ ትንሽ ትንቢት ቢጤ በመጨረሻ አካባቢ ጣል ማድረጌ አይቀርም – “Who minus who?” “ማን ከማን ያንሳል?” ለማለት ነው – ደግሞ ለመተንበይ!

የሣጥናኤል ግብ እውን እንዲሆን የተሰለቸው ወያኔ በአዲስ ወያኔ መተካት ነበረበት፡፡ አሮጌው ወያኔ ለነባሩ የዲያቢሎስ ፍላጎት ስኬት አልተመቸም፡፡ ስለዚህ የተረት አባት ዐቢይ ራሱ እንዳለው “ዕንቁላል ከውስጥ ሲሰበር ሕይወት፣ ከውጭ ሲሰበር ሞት” ነውና ሌላ አካል ከውጭ መጥቶ ኢትዮጵያ ነፃ እንዳትወጣና ሃይማኖቱንም ፖለቲካውንም እንደልቡ የሚዘባነንበት ሊቀ ሣጥናኤል ከኢትዮጵያ ተዋርዶ እንዳይወጣ ሲባል ይህ ታላቅ ሤራ ሊጎነጎን በቃ፡፡ አበሻ ቁርጥህን ዕወቅ ሤራው ግልጽ ነው፡፡

ዐቢይ ወደ ሕዝብ ልብ ውስጥ እንዲገባ የድርሰታቸው ጊዜ በጣም አጭርና ፈጣን የሆኑ ድራማዎች ወደ መድረክ ብቅ ማለት ነበረባቸው፤ ያን ሕዝባዊ ዐመፅና እምቢታ በቶሎ ማብረድ አስፈላጊ ነበር፡፡ ብዙ አማካሪዎች አሉ፤ ብዙ ተዋንያን አሉ፤ ብዙ አሽቃባጮችና የሀሰት ወሬ አናፋሾች አሉ፡፡ እነ ባህታዊ ተብዬዎቹ ገ/መስቀልና እነ ታምራት ገለታን የመሳሰሉ ሣተና ጠንቋዮች እንኳን ስንትና ስንት የወሬ ቱሪናፋ የሚነዙ ተከፋይ ምልምሎች ነበሯቸው፤ አሏቸውም፡፡ የትክለ ሰውነት ግንባታ ቀድሞ ካልተካሄደ አስጠንቋይ ወደ ጠንቋይ፣ ተጠባይ ወደ ጠበል፣ ታካሚ ወደ ሀኪም፣ “ነቢያትንና ፈዋሾችን” ፈላጊ ችግረኛ ወደ “ቸርች” … አይሄዱም፤ ይቺ ምድር የትያትር ዓለም መሆኗን ከዘነጋን የለንም፡፡ ስለዚህ በመንግሥት ወጪ ፈንድ የሚደረግ ዝናን ገምቢና ስብዕናን አግዛፊ ሆዳም በመሙላቱ ሳቢያ ስመ-ጥርነቱ በጥቂት ጊዜያት እየገዘፈ የመጣው ዐቢያችን አሁን ይሠራውን አጣና ሀገራችን ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ ተዘፍቃበት ወደነበረው የዘረኝነት አዙሪት መልሶ በባሰ ሁኔታ ዘፍቋት ዐረፈው፡፡ ይሁን፡፡ ሁሉንም ማየቱ ጥሩ ነው፡፡ ያች ሴተኛ አዳሪ “አጭበርባሪ አይተኛኝም” ያለችውን ግን መርሳት የለብንምና የሀገራችን ትንሣኤ የሚመለከተን ዜጎች ሁሉ ጥንቃቄ እናድርግ፡፡

ከውጭ ሀገራት የታሰሩ ሰዎችን ይዞ መጣ – በአንድ አውሮፕላን ሊያውም “ሰልፊ” የሚሉትን ዘመነኛ ፎቶ አብሮ እየተነሣ፡፡ “እንዴት ያለ መሪ አገኘን!” ብለን ጉድ አልን፡፡ በቤት ውስጥ የታጎሩትን በሽዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን ግን ረሳናቸው፡፡ ሰሞኑን እንኳን የአዲስ አበባ ወጣቶች ባልታወቀ ሥፍራ ታስረው አባሰቸውን እያዩ ነው – “ዐቢያችን” በምትሃቱ አሳውሮናልና ይህንንም እንደበጎ ወሰድንለት፡፡ በትግራይ ጉድጓዶች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በተለይም እኚህ የፈረደባቸው አማሮች በጨለማ ታጉረው ይሰቃያሉ – ይህ “መሢህ” ስለነዚህ ሰዎች የተነፈሰው የለም፡፡ ኤርትራ ሄደ፡፡ የዘመናት ቁርሾ ሊያስወግድ ሞከረ – ግሩም ነው፡፡ ግን አንድም እስረኛ አላመጣም – ለዘዴ ነው ብለን ዝም አልንለት፡፡ እንዲያውም የሀገራችንን ኢኮኖሚ በተለይም የትግራይን ሕዝብ ኑሮ ይበልጥ አመሰቃቀለው፡፡ ያዘነችን ዜጋ ዕንባ ጠረገ፤ “ሆ! እንዲህ ዓይነቱን ሩህሩህ መሪ የት ደብቀህብን ኖርህ?” ብለን በደስታ ሲቃ እያነባን ፈጣሪን አመሰገንን፤ አይቻልም እንጂ ቢቻል ኖሮ ከየዕድሜያችን እየቆነጠርን ለዚህ ደግ መሪ ለመስጠትም ወረፋ ልንይዝ የዳዳን ብዙዎች ነን፡፡ ግን አሁንም በኢትዮጵያ ውስጥ በፍትህ ዕጦትና በርሀብ፣ በወምበዴ ፖሊስና በወያኔዎች ሸርና ተንኮል የሚያለቅሱ ሚሊዮኖች አሉ፡፡ ይህ ሁሉ የማስመሰል ተግባር የተቋጨው ግን በሰሞኑ ሽህሞት ነው – ሹመት፡፡ ሕይወት እንዲህ ናት ምዕመናን፡፡ “አፍ ያለው ያግባሽ ገንዘብ ያለው?” ተብላ ተጠየቀች አሉ አንዷ፡፡ “አፍ ያለው” ብላ መለሰች፡፡ እንደኛ ጉድ ስትሆን ለማልቀስ፡፡ ከዳግም ልቅሶ ይሠውረን፡፡ ዐይናችንን ይግለጥልን፡፡

ዕድሉን ባገኝ ከዐቢይም ጋር ሆነ ከተወካዩ ጋር መከራከር እችላለሁ፡፡ ሌላ ሌላው የማስመሰል ሥራው ይቅርና ይህ ሹመት ብቻውን የዐቢይን ማንነትና የሣጥናኤል ልዑክነት በግልጽ ይመሰክራል፡፡

ማሳሰቢያ – እኔ እገሌ ተሾመ አልተሾመ ጉዳየ አይደለም፡፡ በዘርና በጎሣ የምጠብና የምኮማተርም አይደለሁም፡፡ እንዲያውም ከኢትዮጵያ ሹመት ሞት እንደሚሻል አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በሹመቱ አሰጣጥና የሰዎች አመላመል ዙሪያ የተሰማኝን ቅሬታ ለመግለጽ እንጂ “ደቻሣ ተሹሞ ለምን አጎናፍር ሳይሾም ቀረ?” ከሚል ጠባብ የጎሠኝነት ስሜት ተነስቼ እንዳልሆነ ሁሉም ሊረዳልኝ ይገባል፡፡ እውነቴን ነው፡፡

ሚኒስትሮች መቀነሳቸው ጥሩ ነው፡፡ በድሃ አገር ዱሮውንም ይህን ያህል የካቢኔ አባላት ሊኖሩ ባልተገባ – ወያኔ ሰዎቿን ለመሰግሰግና ለመጥቀም ብላ እንጂ በአስፈላጊነቱ አምናበት እንዳልነበር መገመት ይቻላል፡፡ በእግረ መንገድም የፓርላማውና የሕዝብ ተወካዮች ተብየውም መቀመጫ ተንዛዝቷል፡፡ ለደናቁርት እንቅልፋም ፓርላማ ከ80 እና 90 በላይ አያስፈልግም፡፡ አንድ ሰው እንደፈለገው ለሚጫወትበት ፓርላማና የተወካዮች ንክር ቤት ማለትም ምክር ቤት ይህን ያህል ማይም መሰብሰብ አግባብ አይደለምና ዐቢይ በዚህም ላይ ቆራጥ እርምጃውን በቅርቡ እንደሚወስድበት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በነገራችን ላይ ከስሜታዊ አጻጻፍ ለመውጣት አንድ ቀን አሳልፌያለሁ፡፡ ወዲያውኑ ብጽው ኖሮ አንድም አንባ አላገኝም ነበር፡፡ እንዴ! ሥራቸው እኮ የሚገርም ነው፡፡

አሥሩ ሚኒስትሮች ሴቶች ናቸው፡፡ የአዲሱ መንግሥት ምክንያቶች ደግሞ ደስ ይላሉ – ለዚህ የተሰጠው መልስ “ሴቶች መምራት መቻላቸውን እንዲያረጋግጡ” ተባለልኝ፡፡ ውሸት ነው፡፡ ዘይኑ የሚሉት ያኛው ቀርፋፋ የፖሊስ አዛዥ ደግሞ “የአዲስ አበባ ወጣቶች የታሰሩት ማለትም ወደማሰልጠኛ የገቡት ሊሰለጥኑ ነው” አለንና አሳቀን፡፡ እንዴት እንደሚንቁን ስገነዘብ ኢትዮጵያዊነቴን ብቻ ሳይሆን ሰው መሆኔን ጭምር እጠላለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ከውሸታም ፖለቲከኛ ውጪ ላይገዛት፣ ከውሸታም የቴሌቪዥን ጣቢያ ውጪ ላይኖራት ተረግማ ይሆን?

ጥሩ ነው፡፡ አሥሩ ሴቶች ናቸው፡፡ በዕድሜ፣ በትምህርት፣ በተሞክሮ፣ በችሎታ … እነዚህ ሴቶች ማለቴ ሰዎች ምን ያህል ለቦታው ይመጥናሉ? ብሎ መጠየቅ ብልኅነት ይመስለኛል፡፡ ዐቢይ ግን ማንን ነው “እየቀፈለ” ያለው? እጃችን እስኪላጥ ስናጨበጭብለት ጊዜ አጠገቡ እንዳሉትና ቤተ መንግሥት የገባ አምባገነን ሁሉ እንደሚጫወትባቸው የፓርላማ አባላት የለዬልን ደናቁርት መስለነው ይሆን? ማን ያውቃል እንደነሱ ቆጥሮንም ሊሆን ይችላል፡፡ ግን አይደለንም፡፡ወደዚያ የሚሄዱት ወያ የሚመርጣቸው ጅሎችና ሆዳሞች ማይማንም ጭምር መሆናቸውን ንገሩት፡፡ ኢትዮጵያውያን ማን መሆናችንን ቆንጆዎቹ ሲወለዱ ያየናል፡፡ እስከዛው ይጫወትብን፡፡

እስኪ ስማቸውን እንይ –

 1. ወ/ሮ ሙፈሪያት ዐቢይ አህመድ
 2. (ወ/ሮ?) ኢንጂኔር አይሻ ዐቢይ አህመድ
 3. ወ/ሮ ፈትለወርቅ አባይ ፀሐዬ
 4. ወ/ሮ ዳግማዊት ገዱ አንዳጋቸው
 5. ዶ/ር ሒሩት ዐቢይ አህመድ
 6. ዶ/ር ኤርጎጌ ዐቢይ አህመድ
 7. ዶ/ር ሂሩት ዐቢይ አህመድ
 8. ወ/ሮ አዳነች ዐቢይ አህመድ
 9. ወ/ሮ ያለም ዐቢይ አህመድ
 10. ዶ/ር ፍጹም ዐቢይ አህመድ (ይህ ስም ወንድን ከወከለ ይቅርታ)

እነዚህና ሌሎቹም ከኦሮሞ ነገድ የመጡ ዜጎች ለዐቢይ ቅን ታዛዦች እንደሚሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ዐቢይ በካቢኔው ውስጥ ያሉት እንደራሴዎች ከአሥር በላይ ናቸው፡፡ በዐይን ጥቅሻና በስልክ የሚያሽቆጠቁጣቸውን ገራገር ሴቶች ማለትም ሰዎች መርጦ ለሹመት ማስቀመጡ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከመለስ በላይ እንዴት እንደሚንቀው ያሳያል፡፡ በነገራችን ላይ ተፎካካሪ እያለ በንግግር የሚያሽሞነሙናቸው ተቃዋሚዎችስ ኢትዮጵያ ሀገራቸው አይደለችም እንዴ? ከነሱስ መርጦ ቢሾም ከማን ያንሳሉ? ሀገሪቱን እንዲህ መጫወቻ ከሚያደርጋት – እንዲህ መሳቂያና መሳለቂያ ከሚያደርገን አንድ ሁለት ሦስት ያህል መርጦ ሚኒስትሮች ቢያደርጋቸው ምን ነበረበት? እነሱ ከነሙፈሪያት አንሰው ነው? ለአብነት ለገንዘብ ሚኒስትርነት ከብርሃኑ ነጋና ከአህመድ ሽዴ የትኞቹ ይቀርባሉ? እንዲያው ለመሆኑ ኢትዮጵያ የማን ናት? አይዞን! ኢትዮጵያ የሰማንያውም ጎሣና ነገድ ሀብት ንብረት የምትሆንበት ዘመን እየመጣ ነው፡፡ ወደ ፈጣሪ እንመለስ፤ ከክፋት እንራቅ፤ በጎ ሰዎች እንሁን፤ እንጸልይ፡፡

ልጨርስ መሰለኝ፡፡

ጦጣና ጉሬዛ ፍቅራቸው ያበቃል፡፡ ሥልታዊ ኅብረት የፈጠሩበትን ቃል ኪዳናቸውንም ያፈርሳሉ፡፡ ጦጣ የሰበሰበችውን አትበላም፡፡ ይልቁንም ጉሬዛን ለማጥቃት ያከማቸችውን ገንዘብ ከየጎሬዋ እያወጣች ጉሬዛን ትረብሻዋለች፡፡ ይህ መተናኮሏ ለጉሬዛ ሕልምና ቅዠት መኮላሸት ዋና ምክንያት ይሆናል፡፡ የኋላ የኋላ በዱባ ጥጋብ የነበረረው ጉሬዛ በሀብት ብዛት በሰከረችው ጦጣ ተሸንፎ “አጉራሽ ጠናኝ” ይላታል፡፡ በመጨረሻ ግን አንበሣ ከየት መጣ ሳይባል በሁለቱም መካከል ዕርቅ እንዲወርድና ጫካና ደኑ ሰላም እንዲወርድበት ያደርጋል፡፡ አንበሦች ካልመሰላቸው ጥንቸልም በፊታቸው ትሄዳለች፤ ዐይጥም በጆሯቸው ትመላለሳለች፡፡ ዐይጦችና ጥንቸሎች የአንበሣን ትግስት ወደ ፍርሀት ይለውጡታል፡፡ አንበሣን ያሸነፉ እየመሰላቸው በአንበሣው ፊትና በሰውነቱ ላይ ጭምር አክሮባት ሊሠሩ ይዳዳሉ፡፡ ከአእዋፍ ጩኸት፣ ከደኑ ስፋት፣ ከከዋክብት ምህዋራዊ አቀማመትና ከዓለም አቀፍ እንስሳት የርስ በርስ ንትርክና አለመግባባት የተነሣ መላ ሰውነቱ ዝሎና ግራ ተጋብቶ የነበረው አንበሣ ወደ ቀድሞ ጥንካሬውና የአስተዋይነት ቁመናው ይመለሳል፡፡ ያኔና በመጨረሻው ሁሉም የርሱ ምርኮ ይሆናሉ፡፡ አሁንም ያኔና በመጨረሻው መጨረሻ ደኑና ጫካው ማንም እንደፈለገው በጥጋብና በዕብሪት እየፈነጠዘ የሚያውከው ሳይሆን እውነተኛው ሰላም የሚያረብበትና ፍትህና ርትዕ የሚሠፍንበት ይሆናል፡፡ አበቃ፡፡

2 COMMENTS

 1. Comment:እልም ያልክ ጎጠኛ ሆነህ ነገር ግን እኔ ጎጠኛ አይደለሁም ማለትህ ያስገርማል የእናንተን ስንኩል ፖለቲካ የሚያክምላችሁ እስኪገኝ ቅርሻታችሁ ሀገር እያገማ እስከመቼ እንደሚቀጥል ፈጣሪ ይወቀው ፤

  ቀና ከማለታችሁ ቁና ሙሉ ቅርሻት ትተፋላችሁ የትምክህት ለሀጭ ብሎም በአቶ አለምነው የተገለጠው ይሄው መሰለኝ ፤

 2. ውድ ጉዱ ገዱ አንዳርጋቸው፤
  ስለ አገር ጉዳይ የተሰማህን ቁጭት እንደ ቀላል አላየውም።
  “ኢሉሚናቲ” “ደባ” ለምትለዋ ጥሩ መረጃ አላቀረብክም። ጥረትህን ከንቱ አድርጎብሃል።
  የዘነጋኸው ዋነኛ ቁምነገር፣ ዶ/ር ዐብይ የኢሕአዴግ መሪ ነው። ኢሕአዴግ የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የደቡብና የትግሬ ፓርቲ ጥርቅም ነው። ዐብይ የተመረጠው እኔና አንተን ወክሎ ሳይሆን፣ ኢሕአዴግ ባወጣው መመሪያ እርስበርስ ምርጫ አካሂዶ ዐብይና ገዱ፣ ከኦሮሞና ከአማራ ፓርቲ ከፍተኛውን ድምጽ ስላገኙ ነው። ሹመቱ፣ ወንድና ሴቱን ጨምሮ፣ ይህን ዓይነት የፖለቲካ ጨዋታ እያሳየን ነው። ዐብይ እንደ መለስ ዜናዊ ፈላጭ ቆራጭ ከመሰለህ ተሳስተሃል። ህወሓት አልቆለታል ካልክ አሁንም ተሳስተሃል። ግርግር እያካሄደ ያለው ህወሓት ነው። ግርግር ከሌለ ትርፍ አያገኝማ! ደግሞ 27 ዓመት ሙሉ ሲያነታርክ፣ ሲያፋጅ፣ ሲደልል ከኖረ ዐብይ በምን አቅሙ በ6 ወር ያን ሁሉ ጉንጉን ይፈታል ብለህ አሰብክ? ንግግርህ የማይመስል ነው። ከስሜተኝነት መላቀቅ አልቻልክም። አቃናለሁ ብለህ ይልቅ የህወሓትን ሥራ ያለ ክፍያ ሠራህለት። ከሁለት ዓመት ምርጫ ይካሄዳል የተባለው ከሆነ ብቻ አንድ ተስፋ አለ። ሌሎች ፓርቲዎች ተወዳድረው ሥልጣን ሊጋሩ። ሌሎች ፓርቲዎችን እስካስተናገደ ኢሕአዴግ መኖሩ ምንም ችግር አይመስለኝም። የኔ ሥጋት “ተፎካካሪ” የተባሉት በጥቃቅኑ ሲፋጩ እንዳያመልጣቸው ነው። ሁሉም አንተን ጨምሮ “ዘራፍ!” ብቻ ከሆነ ብልሃቱ ከየት ይምጣ። ሌላው ሥጋቴ እነ ዶ/ር ብርሃኑ፣ ጃዋር፣ ዳውድ ከነአጀባቸው የመጡት ከኤርትራ ነው። ኢሳይያስ (ይቅርታ “ኢሱ”) ገና ቀድሞ አስቦበታልና፣ ሳይመቸው ወይም የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብር ሲመጣ፣ የሚያበጣብጥበትን ፕሮግራም ነድፏል። አሁን የምንገኝበትን የፈጠረልን ባብዛኛው “ኢሱ” ነው። ዶ/ር ዐብይ እንዳሰብከው አልሆነም ማለትህን እቀበላለሁ። ስለ ንግግሩ ቅልጥፍና እርግጥ ነው። ግን ፈላጭ ቆራጩ እርሱ እንዳልሆነ ተረዳ! ህወሓት ፓርላማ ብሎ ያሰባሰበው አብዛኛው ጥቅሙን እንጂ ግራና ቀኙን የሚያወቅ አይደለም። ትንሽ የሚያወቀው ደግሞ ለጥ ብሎ ካላደረ ይወገዳል። ትንሽ ተስፋ የሚሰጥ ነገር፤ እነ ገዱና ለማ ህወሓት የሰገሰጋቸውን ጀሌዎች አጥርተው አስወግደዋል። ብዙ የተማሩና ትጋት ያላቸው ተተክተዋል። አማራ ክልል ባንዲራውንና አመራሩን መለወጡን እንደ ቀላል አትመልከት። ኦሮሞ ለሹመት ከታጨ አገር ፈረሰች ማለት አቁም። ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ አይደለም የምትል ያስመስልብሃል። ይህን ጥያቄ ሁሌ ጠይቅ፣ ትልቁ አጀንዳ የቱ ነው? ህወሓት ቀዳዳ እንዳያገኝ ምን ይደረግ? ቄሮ የክልሉን ባንዲራ አውለበለበ ብለህ አትብገን። ሁሉም ክልል የራሱ ባንዲራ አለው፤ ይኸ 27 ዓመት አስቆጥሯል። የክርክር ደጅ ሳይዘጋ ያድራል። ክፍት ደጅ ደግሞ ጅብ ያስገባል። ሰምተህ ከሆነ የቀን ጅብ አለ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.