“ሸዋ የሌለበት፣ ሴት የበዛበት ካቢኔ!” (በያሬድ ጥበቡ)

በትላንትናው ዕለት ዶክተር አቢይ አህመድ የኢትዮጵያን የሚኒስትሮች ምክርቤት በግማሹ በሴቶች በመሙላታቸው ደሰታውን የሚገልፀው ወንድ ብዙ ነው። ለብዙ አስርተ ዓመታት ለሴቶች እኩልነት የተሟገትኩ በመሆኔና በትጥቅ ትግሉ ረጅም ዓመታትም የነበራቸውን የመንፈስም ሆነ የአካል ጥንካሬ ስላየሁ እንደብዙው የዓለም ወንድ በጉዳዩ ላይ ችግር የለኝም። ዛሬ ግን ምስቅልቅል ስሜት ነው የተሰማኝ፣ የደስታም የስጋትም ።

በትላትናው ዕለት የተሾሙት ሴት ሚኒስትሮች

ከዓለሙ ተለይተን እኛና ሩዋንዳ ብቻ ካቢኔዎቻችንን በሴቶች ማጋመሳችን፣ እውን የተሻለ ለሴቶች መብት ተቆርቋሪ በመሆናችን ነውን? ጡት መያዣቸውን ያቃጠሉ የሴት አርበኞች የሞሉባቸው የምእራብ ሃገራት በ200 ዓመታት የዴሞክራሲ ጉዞዋቸው ያላደረጉት ለምን ለኛ ቀለለን? ወይስ እንደ ክልል ፌዴራሊዝማችን ይሄኛውም ቤተሙከራ ይሆን?

አንድ ከአዲስ አበባ ጉብኝቴ የታዘብኩት ነገር ቢኖር የአቶ መለስ የመተካካት ፖሊሲ በሃገሩ ላይ ያረበበውን የወጣት ጊዜው የኛ ነው መንፈስ ነው። ስለተማሩ፣ ስላጠኑ፣ ስለተዘጋጁ ወዘተ ሳይሆን ዝም ብሎ ወጣት በመሆናቸው ብቻ ሃገሩን ሊረከቡ የሚችሉ አይነት መዳፈር ነው ያየሁት። የፌስቡክ መድረክም ላይ ይታያል። ሸበት ያለ ሰው ሁሉ በእድሜው ይዋረዳል፣ ይሰደባል ወዘተ። ይህ ፍፁም ውሸት የሆነ ስሜት ነው። የዛሬውም የሴቶች ሹመት እንደ ክልል ፌዴራሊዝሙና መተካካቱ የቤተ-ሙከራ ጉዳይ እንዳይሆን ፍርሃት አለኝ።

አሁን ከሴትነቷ በላይ የመከላከያ ሚኒስትሯን ለዚህ ሹመት የሚያበቃት ምን ይሆን? ያውም የከብት አርቢዎች እኩልነት በተንሰራፋበት የአፋር ባህል ያደገች ሴት፣ የሥልጣን ተዋረድና ሹመት የሞት ሽረት ጉዳይ የሆነበትን የሩብ ሚሊዮን የጦር ሃይል የሚያስተዳድሩትን ጄኔራሎች የሚመራ ተቋም እንዴት አድርጋ ልትመራው ይሆን? ወይስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “መከላከያውን እኔ ራሴ እመራዋለሁ፣ በደከመችበት አግዛታለሁ” ብለው አስበው ይሆን? ከሁሉም በላይ ግን ሌላው ዓለም ይህን ሴቶችን የሥልጣን ቁንጮ ላይ የማውጣት ጉዳይ ለምን ሳይደፍረው ቀረ? ትምክህተኛ ስለሆነ ነው ማለት በጣም ቀላል መልስ ነው። ከዚህ የበለጠ ምክንያት ይኖራቸው ይሆን?

አንዳንዴ፣ አንድ ውሳኔ ስናደርግ፣ በተቃራኒው ባለመወሰናችን የምናጣውን ማሰብ ተገቢ ይመስለኛል። በታሪካችን የቆየውን የትምህርት፣ የሥልጠና፣ የዝግጅት፣ የሥራ ልምድ ወዘተ ታሳቢ ስናደርግ፣ ለእያንዳንዷ ተሿሚ ሚኒስትር፣ ለቦታው የሚመጥኗት እንዲያውም የሚበልጧት ሌሎች 200 ወንዶች ይኖራሉ ብለን ብናስብ፣ ኢትዮጵያችን የነዚያን ትጉሃን ወይም አዋቂ ወንዶች ችሎታ አጥታለች ማለት ነው። ይህ ምን ያህል ተገቢ ነው? ያዋጣል? ያበላል?

የምንወዳቸው ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከሁለት ሳምንታት በሁዋላ የጀርመኗን ቻንስለር አንገላ መርክልን እንደሚያገኙ እናውቃለን ። የመርክልን ድጋፍና ፍቅርም ያስገኝ ይሆናል ይህ ሹመት። የፈረንጅ መያዶችንም ፍቅርና ድጋፍ እንዲሁ ። ግን የኢትዮጵያ ህዝብስ? ካቢኔው በግማሽ በሴቶች ቢሞላስ ተብሎ መጠየቅ፣ ቢያንስ አስቀድሞ በነገሩ ላይ መጨቃጨቅ አልነበረበትም? ከበር ጀርባ በፈረንጅ አማካሪዎችና በአዋጅ የሚሠራ ነገር የሚበቃን መቼ ነው? መቼ ነው በሃገራችን ላይ ባለቤት የምንሆነው? ዶክተር አቢይ አስቀድመው ቢያማክሩን ምን ነበር የሚጎዳቸው? አንዳንዴ ሳያማክሩን የሚያደርጉት ነገር ሊጎዳን እንደሚችል ከኦነግ የትጥቅ ግርግር እንኳን መማር አልነበረባቸውም?

የኦነግስ ይሁን የውስጥ ጉዳይ ነው፣ ለመሆኑ ከኤርትራ ጋር ያለን ስምምነት ምንድን ነው? መካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ውይይት መጀመሩን ሰምተን ነበር። የአረብ አደራዳሪዎች የሚያውቁት ለእኛ ለባለቤቶቹ ባእድ መሆን ይገባዋል? ሃሳባችንስ መጠየቅ የለበትም? ከጀርባችንና የታሪክ ምሁራኖቻችን፣ የህግ አዋቂዎቻችን፣ የፖለቲካ ሳይንስ ጠበብቶቻችን ሳይሳተፉበት የሚደረግ ውል የአልጀርስ ስምምነት ላይ በባዶ እጅ አስጨብጭቦ እንዳስቀረን የትናንት ትዝታ አይደለምን? አበው ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሃኒቱ ያሉት ለዚህ መስሎኝ! አሁንስ ሆድ ሊብሰኝ ነው መሰለኝ ። የሚወዱትን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዴት ነው የሚተቹት? ይጨክኑበታል? ወይስ ራርተው ይሸፋፍኑለታል? ለዚህ አበው መልስ አላቸው ፣ “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” ብለው። ወይስ በአረሙ መመለስ ይሻል ይሆን? የጨነቀ ነገር ነው ይላል የጎንደር ሰው።

ዶክተር አቢይ የሹመኞቹን የትውልድ ቦታ ሲጠሩ ባዳምጥ ባዳምጥ ከሸዋ ተሿሚ አጣሁ። መቼም አዲስ አበባ ሸዋን አይወክልም ። አዲስ አበባ ሸገር ነው፣ ራሱን የቻለ። ባስበው ባስበው የሸዋ መገለል የአቢይ ሳይሆን የአዴፓ/ብአዴን ችግር ነው። የብአዴን ችግር ደግሞ ከወያኔ የሸዋ ጥላቻ የተቀዳ ነው። ህወሓት ብአዴን ላይ የበላይነት በነበረው ዓመታት የሸዋ ምሁር መመልመል አይችልም ነበር ፣ በተፃፈ ህግ ሳይሆን ባልተፃፈ መግባባት። አሁንም አዴፓ አስቀድሞ ያላዘጋጀውን ከየት ያምጣው? ለሚኒስትር ሹመት የሚበቁ አቅርብ ሲባል እነዚያኑ የጎጃምና ወሎ መንደርተኞቹን ሊስት ነው የሚያቀርበው። ሆኖም ብአዴን ማቅረብ ባይችልም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሰቸው “እስከመቼ ሸዋን አግልለን እንዘልቃለን” ብለው፣ ከብአዴን ውጪም ለቦታው የሚመጥኑ ሰዎችን መሾም ነበረባቸው ። ለወደፊቱ ይማሩበታል ብዬ አስባለሁ ።

በተረፈ፣ በመካከለኛ እርከን ክፍት የሥራ ቦታ በተገኘ ቁጥር በኦሮሞዎች ይሞላሉ የሚለው ቅሬታ እየጨመረ የ26 ዓመት ወጣት ኢንደስትሪያል ፓርኮችን ሁሉ ለሚመራው ተቋም ሲኢኦነት ሲመድቡ ሳይ ተሳቅቄ ስለነበርና፣ “ጊዜው የኛ ነው” የሚለውም የኦሮሞ ብሄርተኞች ተፅእኖ ከፍተኛ መሆኑን ስለማውቅ፣ አዲሱን ካቢኔ ሲያቋቁሙ ወደ ኦሮሞው ያዘነብሉና ከሂሳዊ ደጋፊነት ወደተቃዋሚነት ይገፉን ይሆን የሚል ፍርሃት ነበረኝ። ያ ፍርሃቴ በመምከኑ ደስ ተሰኝቻለሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትራችንንም ማመስገን እወዳለሁ ። የሴቶቹን ሹመት ግን ደግመው ቢያሰላስሉት ደስ ይለኛል። ሌላው ዓለም ትምክህተኛ ሰለሆነ አይመስለኝም እኛ ያደረግነውን ማድረግ ያቀተው ። በአዋጅ ስለማይሠራ ይመስለኛል። ኢትዮጵያችንም ከዝግ በርና ከአዋጅ አሠራር፣ ከፈረንጆችና ከመያዶች ምክር ወጥታ፣ በልጆቿ ሁሉ ፍፁም ባለቤትነት የምትተዳደርበትን ቀን በመመኘት ሂሳዊ ድጋፌን በዚህ ለቋጭ ። በሌላ ሂሳዊ ድጋፍ ትችት እስክንገናኝ፣ መልካሙን እመኝላችኋለሁ!


ምንጭ፦ ከያሬድ ጥበቡ ፌስቡክ ገፅ የተወሰደ

 

አቶ ያሬድ ጥበቡ


9 COMMENTS

 1. I used to believe that Yared Tibebu is one of those rational politicians. But with some of his writings he has already justified that I was wrong. Now I realized even more that Girma Kassa was shaped and thought by Yared Tibebu concerning his political stands. That is why Girma Kassa writes here and there his nonsense pieces about the so called Shewa.

  Yared Tibrbu and Girma Kassa cannot even tolerate the names which the Oromo have given for their land and areas like Oromia, Finfinne, Adama, Bushofitu and so on. But they try to preach a fake unity and mutual understanding and respect. Yared Tibebu tries sometimes to sell himself as someone who has been struggling for the rights of the Oromo nation. But he is latent anti-Oromo. He better shares his ideas with hardliners and illusionists like the debtera Larebo, Getachew Haile, his colleague in crime Girma Kassa and other anti-Oromo elements. The Oromo are self sufficient to protect their natural rights and to regain all their political and economic rights in thier fathers’ land, Oromia sooner or later. Watch out!

  No more business as usual. Period!

  There is nobody without national background and heritages in this planet. All human beings have ethnic backgrounds regardless of the composition of their ethnicity. Those who try to nullify their ethnic backgrounds are claiming Amhara ethnicity by default under the mask of Ethiopianism. They speak amharic and claim the cultures from north as their culture. They try to impose their default identity (Amaharaism as Ethiopianism) on the others. But it is not acceptable!

  The politics of one language, one culture and a single nation cannot be accepted any more in Ethiopia. Don’t forget that such demands have no room in today’s Ethiopian politics. But now temporally you can make noise here and there. That is all what you can do right now.

  De-Amharanisation of the whole Ethiopian politics is indispensable and absolutely necessary in order to reform and reshape Ethiopia as a country of multinational state. The politics of one language, one culture and a single nation cannot be accepted any more. Also there is no Ethiopian identity as some idiotic individuals try preach us those like the chameleon Ermias Legesse. It is a fake identity and ridiculous.

  Dissociating Ethiopia from the politics of Menilik is indispensable for emancipation of all the nations.

  The creation a new national flag is crucially important in order to build a national consensus. The new flag should have reflect a true multinationality of that country.

 2. ውድ ያሬድ ጥበቡ፣
  እኔም እንዳንተው ትልቅ አሳብ ገብቶኛል፡፡ “ከሸዋ” በመሆን ባለመሆን ግን አይደለም፡፡ ዶ/ር ዐብይ፣ የተሿሚዎቹ አመራረጥ “ብቃት፣ ልምድ፣ የትምህርት ዝግጅትና ለውጥ ለመምራት ያለውን ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ” ነው ብለውናል፡፡ አገራችንን እያወደመ ያለ አንድ የህወሓት ሴራ፣ በጎሳ ፓርቲ ውስጥ አባል ያልሆነ አገሩን በእውቀቱና በልምዱ አያገለግልም የሚለው ነው፡፡ “ዶ/ር” ወርቅነህ ገበየሁ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር መሆኑ እንደ አንድ ዜጋ ያሳፍረኛል፡፡ ትግሬ ስለ መሆኑ ግድ የለኝም። ብቃቱን ማለቴ ነው፣ አሳቡን በእንግሊዝኛ አውጣጥቶ መግለጽ እንኳ አይችልም፡፡ ከደቡብ አፍሪካ አገኘ ስለ ተባለው ዶክትሬት የጻፈውን ዲሰርቴሽን መመልከት ብቻውን ብዙ ነገር ያስረዳሃል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት ውስጥ በየእርከኑ የተመደቡትን ብትመለከት ቁልፍ ቦታዎች በህወሓት ሰዎች ተይዞ ታገኛለህ፡፡ በየኤምባሲና ቆንጽላ ጽ/ቤትም እንደዚሁ ብዙዎች ብቃት የሌላቸው ተላላኪዎች ተሰልፈው ታገኛለህ፡፡ ካሳ ተ/ብርሃን በአሜሪካ “ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር” ነው፡፡ ልምዱም እውቀቱም የለውም፡፡ የ30 ኣመቱ ዶ/ር አማን አሚር ሃጎስ ለጤና ጥበቃ በቂ ልምድና እውቀት የለውም፤ ከጤና ኮሌጅ እንደ ተመረቀ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር ተመደበ፤ አንድ አመት ተኩል በጤና ጣቢያ ውስጥ የሠለጠነበትን የህክምና ሙያ ተለማመደ፤ 3 ወር በሚ/ር መ/ቤት በበጀትና ፖሊሲ ክፍል ተመደበ፤ በቢል ጌትስ በኩል ደቡብ አፍሪካ ተልኮ የአንድ ኣመት ፐብሊክ ሄልዝ ዲፕሎማ አገኘ፡፡ ከዚያ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚንስትር ሆነ፡፡ አሳፋሪ ነው፡፡ ምሥጢሩ ቴድሮስ አድሃኖም ዘመዱ ነው፤ ቢል ጌትስ ቴድሮስን የተባበሩት መንግሥታት ያስቀጠረው ነው፤ በወሊድ ቁጥጥር/ውርጃ ፕሮጄክት ቢል ጌትስ ዓላማው አፍሪካውያን እንደ ጥንቸል ተራብተው አውሮጳንና አሜርካን እንዳይወርሩ ከመሠረቱ ለማድረቅ ነው፡፡ አማን ትግሬ ሆኖ እያለ በአማራነት ስም ተሾመ፡፡ በጤና ጥበቃ ኃላፊ መደረጉ ቢል ጌትስና ህወሓት ለወጠኑት ፕሮጄክት መሳካት አስፈላጊ ነው፡፡ ወርቅነህ የአያቱን ስም በኦሮሞ ቀይሮ እንደ ተሾመ ሁሉ፡፡ ህገ ወጥ ብቻ ሳይሆን ዐይን ያወጣ ቅጥፈት ነው! ለአገር መከላከያ የተመደበችው ሴትም እንዳልከው ለኮታና ለጉራ ካልሆነ “ብቃት፣ ልምድ፣ የትምህርት ዝግጅት” የላትም፡፡

  ከሁሉ ይልቅ የሚያሳስበኝ በኢትዮጵያ ስም እየተገባ ያለው ውል ነው፡፡ እርግጥ ከበስተጀርባ አሜሪካኖች ሳውዲና ዐረቦችን እስራኤልን ጭምር የኢራንን ተስፋፊነት መግታት በሚል ስም እየዘወሩ ነው፡፡ ከኤርትራ ጋር የተካሄደው ሁሉ ለኢትዮጵያ ምን ጥቅም እያስገኘ ነው፡፡ አሁን የምናየው ጥቅሙ ለኤርትራ ብቻ ነው! ዶ/ር ዐብይ፣ ድንበር በሁለቱ አገሮች መሓል የማያስፈልገው፣ የድንበር ኗሪዎች ድንበር ኖረ አልኖረ ከወዲህ ወዲያ መመላለሳቸውን ማቆም ስለማይቻል ነው ብሎናል፡፡ ለዚህም ከኬንያ ጋር ያለውን እንደ ምሳሌ ጠቅሷል፡፡ የተሳሳተው ግን ከኬንያ ጋር ድንበር አለ፡፡ ከሱዳንም ጋር፤ ከሱማልያም ጋር፡፡ በዓለም ሁሉ ድንበሮች በህግ ይታወቃሉ፡፡ የሚገርመው ባሁኑ ወቅት ኤርትራውያን “ወንድሞቻችን” ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ሥራና ንግድ የትምህርት እድል እያገኙ ነው፡፡ ዜጋ ግን ይህን እድል ተነፍጎአል፡፡ ወደ ኤርትራ የሚጋዘው ቁሳቁስ ያለ ቀረጥ እየተሸጠ ነው፡፡ ሁለት የተለያዩ አገሮች በዓለም መንግሥታትም የተመዘገቡ ሆነው እንደ አንድ አገር እየተገበያዩ ነው፡፡ ነገ ካለፈው ጋር የሚመሳሰል ችግር እንደሚገጥመን አንርሳ፡፡ ሌላኛው እንዳልከው ሁሉ በምሥጢር መያዙ ነው፡፡ “ኢሱ” ኢሳይያስ ኢትዮጵያን ለዚህ ሁሉ ያበቃት ሰው ነው፡፡ ተለውጦአል ብትለኝ አላምንህም፤ ለኤርትራውያንም አልበጀም እንኳን ለኛ! ህወሓት ባሁኑ ወቅት ከኢሳይያስ ጋር ውይይት ይዘዋል፡፡ ኢሳይያስ ሦስተኛ ዙር የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ወሳኝ ሆኖ ቀርቧል፡፡ ኢትዮጵያ ያልተረጋጋች ብዙ ድምጽ የሚሰማባት አገር ነች፤ ኤርትራ አንድ ድምጽ ብቻ ናት፣ የኢሳይያስ ምድጽ ብቻ፡፡ ለማጥቃትና ፈቃዱን ለመፈጸም ቀላል ነው፡፡ ጫጫታችንን እያባባሰ፣ እያማለደ፣ ሲያስፈልግ በምሥጢር እየመከረ ገና ያሽከረክራል፡፡ እንደ ዶ/ር ብርሃኑ፣ ሌንጮ ለታ፣ ዳውድ ኢብሳ፣ ጃዋር፣ ኢሳት ሁላቸውም ኢሳይያስን ሲያሞግሱና በርሱ ድጋፍ ሲሯሯጡ የነበሩ ናቸው፡፡ (ከቻልክ ወደ ኋላ ሄደህ ዩቱብ ተመልከት፣ እነ መሳይ መኮንን፣ ሲሳይ አጌና፣ አበበ፣ ገላው፣ ነኣምን ዘለቀ ሲያስተጋቡ የነበረውን ኣሳፋሪ ቅንብር!) በቀደም ዳውድ ኢብሳ ትጥቅ አልፈታም ብሎ አስቸገረ ተብሎ ኢሳይያስ አማላጅ እንደ ተጠራ ሲነገር ነበር፡፡ ይኸ ለአገራችን ትልቅ ሓፍረት ነው፡፡ ዳውድ የሰላም ጥሪ ተቀብሎ መጥቶ በትጥቅ ካለ ያለው ምርጫ አገር ሳያጫርስ እስር ቤት ማስገባት ነው፡፡ ይኸ ህጋዊ አካሄድ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር፣ ኢሳይያስ በህወሓትና በሌሎች “ተፎካካሪዎች” ላይ ያለው ሥልጣን ቀላል አይደለም፤ የኢትዮጵያን ጉዳይ እንደ ገና እጁ አስገብቷል፡፡ ዶ/ር በረከት ሃ/ስላሴ በአሜሪካኖቹ በኩል ያለውን አያይዞለታል፡፡ እኛ በፍሬ ከርሢኪ ስንባላ እርሱ እንቅልፉን ትቶ ሥራ ሰርቷል፡፡

  ሌላው ጉዳይ፣ ቅደም ተከተል አለማወቅ “ተፎካካሪውን” ጫጫታና ንግግር ብቻ አድርጎታል፡፡ ቀረርቶ፣ ድንፋታ አእምሮ ቢስነት ነው፡፡ ዓለምጸሐይ ወዳጆ አገሯን ትወዳለች፣ ቦሌ ስትደርስ የጣይቱን ሐውልት ስለ ማስተከል ማውራቷ ቅደም ተከተል አለማወቅ ነው፡፡ እነ እስክንድር ባንዲራ ሲያውለበልቡ፣ ሌላው ማውለብለቡ ለምን ክህደትና ወንጀል እንዳስመሰሉት አይገባኝም፡፡ እያንዳንዱ ክልል ባንዲራ አለው እኮ፡፡ ህወሓት ያንን ለመከፋፈያ ተጠቅሞበታል፡፡ አሁን ግርግር ሲነሳ እንዳይረግብ ያራግባል፡፡ ያን ካላደረገ መግቢያ ያጣል፡፡ ቀዳሚ አጀንዳ የአማራና ኦሮሞ ህብረት ነው፡፡ ኦሮሞ በተሾመ ቁጥር ባእድ እንደ ተሾመ ከተቆጠረ፣ “ሸዋ የታለ?” ካልን መባላታችን ነው፡፡

  በቀደም ታማኝ በየነ ለዶ/ር ዐብይ የታፈሱት የአ/አበባ ወጣቶች እንዲፈቱ ግልጽ ደብዳቤ ጽፎ ነበር፡፡ ታማኝና ሌሎች ጥርጣሬ ገብቷቸዋል፡፡ ይህንን አብዝተው የሚዘውሩትና የሚፈልጉት ህወሓቶችና ካድሬዎቻቸው ናቸው፡፡ እነ ታማኝ ፈቅ እንደማይል ሲያውቁ ጥለው የሚመለሱ ናቸው፡፡ ውጤቱ ምን እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡ እነ ዶ/ር ብርሃኑ ተመልሰው ኤርትራ መሄድ አይችሉም፤ አበቃላቸው ማለት ነው፡፡ ኢሳይያስ እንደ ሆነ የሚፈልጋትን እያገኘ ነው፡፡ የተቀረውን ከዐረቦችና ከአሜሪካኖች ፍላጎት ጋር አያይዞ፣ ኢትዮጵያንም እዚያ ቀለበት ውስጥ አስገብቷታል፡፡ ዐረቦች ገንዘብ በየጊዜው ይበትኑልናል፣ ሴቶች ልጆቻችንን በባርነትና በመድፈር ያሰልሟቸዋል፡፡

  አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በጥቃቅኑ መጋደል አቁመው አጀንዳቸውን ቅደም ተከተል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እነ ኢሳት እሳት ከማንደድ ይልቅ መሪ ያጣውን፣ እውነት የተጠማውን ህዝብ ማገልገል ይጠበቅባቸዋል፡፡ እውነተኛ ወሬ ማቅረብ በፌስቡክ ላይ ከመሞነጫጨር በሴልፎን ከዲሲ ከመወያየትና ከራሳቸው ምንጭ ከመቅዳት እጅግ ይለያል፡፡ ለመሆኑ፣ የምርጫ ኮሚሽን ከሁለት ኣመት በኋላ ምርጫ ያካሄዳል፡፡ በቀደም፣ ኮሚሽኑ እስካሁ የአፋር ፓርቲ ብቻ ተመዝግቧል ሲል ነበር፡፡ ይኸን ማጣራት ያስፈልጋል፡፡ ዶ/ር ዐብይ የገባውን ቃል ምን ያህሉን ያስፈጽማል? ይህን መከታተል ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፡፡

 3. ለሸዋ መገለል ዛሬ የተቆጨኸው በሸዋ ላይ መለስና በረከት ሲዘምቱ በተራ ወታደርነት ስታገለግል ለምን አልታየህም? ሴቶችን በተመለከተ እናንተ ወንዶች ባቦካችሁት ፖለቲካ ብዙ ህዝብ ስላለቀ ለለውጥ ሴቶች በመሪነት እንዲመጡ ማሰብ ስልጡን ፖለቲካ ነው::

 4. ውድ አለም በመጀመሪያ ብዙዎቹ አለም የማውቃቸው ሴቶች ስለሆኑ በሴት አንቀጽ ልጥራሽ ምንም እንኳን አንዳንድ አለም የሚባሉ ወንዶችን ባውቅም። ከተሳሳትኩም አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

  ሲቀጥል እኔም እንዳቺ የምጋራውና የፌስ ቡክ ገጼን መክፈት እስክጠላ ድረስ ያቃረኝ ውርንጭላ ፖለቲከኞች የሚጽፉት ጽሁፍ÷ የድረ ገፅ ጋዜጦች የሚያቀርቡት ዜና÷እንደ ኢሳት ላይ ያሉ ጋዜጠኞች የሚያነሷቸው ርእሶች ቅደም ተከተልን ያልጠበቁ ሲያልፍም ሀገር የሚያቀጣጥሉ ናቸው። አንዳንዶቹ ርዕሰ ጉዳዮች ህብረተሰቡን sensationalize ሊያደርጉ እንደሚችሉና አሸናፊና ተሸናፊ ወደሌለው ጦርነት እያንደረደሩት እንደሆነ አላዩትም። ነገ ከነገ ወዲያ በንግግር ሊፈቱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ርእስ እየከፈቱ ህዝቡን ወደ አለመተማመንና መናከስ እያመሩት መሆኑን አልተገነዘቡትም። ሌላው ሊሰመርበት የሚገባው ትንታኔ ሲሰጡ(ትንታኔ ከተባለ ነው እሱም) የአንድ ወገንተኝነት ይታይባቸዋል በሌላ አባባል ሁሉን አቀፍ ሀሳብ አይሰጡም። የዚያኑ ያህል ሰው እነሱ የሚያቀነቅኑለትን ሀሳብ እንደሚቃወመው ከስር በሚሰጡ ኮሜንቶች በከፊል በተረዱት ነበር።

  ዛሬ በየስርቻው ተወሽቆ ማንነቱ በማይታወቅ የፌስ ቡክ ገጽ በሚለቀቅ ጽሁፍ ሰዉ እንዴት እየተባላ እንዳለ ለሚታዘብ ሰው የሀገሪቱ መጪው ጊዜ ያስፈራል። እኔ ደግሞ ከዋናው ጽሁፍ ይልቅ ከስር የሚሰጡ ኮሜንቶች ይስቡኛል። ኮሜንቶቹ ህዝቡ በተጻፈው ጉዳይ ላይ ያለውን ሀሳብ ሙሉ ቁመና ባይሰጡም በተወሰነ ደረጃ የየራሳችንን ግንዛቤ ወስደን አማካይ አስተሳሰቡን እንገምታለን። ከዚህም በመነሳት እነ ኢሳትን በመሰሉ መገናኛ ዘዴዎች የሚቀነቀኑ ነገሮች ሀገርን ወደትርምስ እየገፋት ስለሆነ ማሳሰብ እወዳለሁ።

  በአሁኑ ጊዜ እየታየ ያለውን የተለያዩ ብሄሮችን የማይገናኝ ፍላጎት እንዴት ማስታረቅ እንዳለባቸው ሊያውቁት ይገባል አንድ ጠርዝ ላይ ሆኖ ከሌላው
  ቡድንጋ ከመላተም። ከዚሁጋ እንዴት የዴሞክራሲ ተቋማት መጠንከር እንዳለባቸው ሊያስተምሩ ይገባቸዋል ቅደም ተከተሉን ያልጠበቀ ርእስ አንስተው ህዝብን ከሚያባሉ።

  በመጨረሻም ተደራሽነታቸው ሰፊ የሆኑ ሚዲያዎች ጊዜውን ያልጠበቀና አንድን ወገን አስደስቶ ሌላውን ቡድን የሚያስከፋ ጉዳይ እያነሱ እየደገፉ ሀገር ከማናከስ በስተቀር ምንም ሚና የሌለውን ጉዳይ እያነሱ ከማፍረጥ ተቆጥበው ልዩነትን የማቻቻል ተግባር ላይ ቢሰሩ ይሻላል።

 5. አንተ ደግሞ የለየልህ ደረቅ ነህ!ሹመቱን አስቡበት? ታስቃለህ፡፡ ለምን አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ አልሆነም ብለን ግን ቅሬታ ማሳየት ማቆም አለብን፡፡ የወያኔን ልክፍት ደግመን እንዳናይ መጣር አለብን፡፡ ጨዋታ ያሸነፉ ይመስል የተወለዱበትን አገራቸውን እየተጠራ ሹመት መስጠት ግ ን በጣም አሳፋሪ ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር አገራችን የተማረ ማግኘት ቀላል አይመስለኝም ተምሮም በተጨማሪ ፓለቲካ ፈላጊ፡፡ እና ያው ሰው ባለው ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ የመከላከያዋ ሴትዮ በእርግጥ ያሳስባል ችሎታዋ ሳይሆን ጾታዋ ያስደነግጣል፡፡ መክላከያ የሶቶች ጉዳይ ነገር ያያል? ድሮ የማውቀው መከላከያ ከሆነ አሳሳቢ ነው፡፡ እንደ አገራችን ላለ አባወራ በሚስማበትና በሚከበርበት አገር ለሴት ሃላፊ ዝጉጁ አይደለንም፡፡ ምን አይነት መልእክት ነው የምንሰጠው በእንደዚህ ቀውጢ ዘመን ላይ ሆነን?

  ፕ/ሚሩ ብስለት ይጎለዋል፡፡ ህዝቡ ምን አይቶ እንደሚበላቀጥለት ምስጢር ነው ሁሌ የሚሆንብኝ፡፡ ከአረብ ጋር ውኒጥ ውኒጥም ከአረብ ምንም የምናገኘው ጥቅም የለም እስልምናን ለማስፋፋት የስጡት የወለድ ቅናሽ ተደርጎለት ካልሆነ በስተቀር ፡፡ ሳውዲ ተቀዋሚ ጋዜጠኛቸውን ምን አንዳደርጉት አይተናል፣ በዛ ላይ የመን ላይ የሚፈጽሙት ወንጀል እና ኢሰ ብአዊ ድርጊት ህዝብ ላይ ልብ የሚሰብርና የሚዘገንን ነው፡፡ኢትዮጵያዊያውንም ላይ የሚያደርጉትን ወንጀል ፀሃይ የሞገ ጉዳይ ነው፡፡ ይሄ ሁሉ ሆኖ የአረብ ተፈላጊነት አልገባኝም፡፡ ማነው ዐብይን የሚያምክረው? እውነቱን ለመናገር ቡርካ ለባሽ ስልጣን ውስጥ የሚያበዛው አረቦቹን ለማስደሰትም ሊሆን ይችላል የሚል የግል ጥርጣሬ አለኝ ወይም የጅዋር አይነቱን የኦሮሞ እስላም ላይ ትኩረት የሚሰጥ ፓለቲከኛ፡፡
  ኤርትራውያን በሚመለከት አሁን አፈወርቂን በአካል ስለምናየው የተለየ ይመስለናል እንጂ ወያኔ ብዙ ኤርትራውያን ቱጃሮችን ብዙ የንግድ መስክ ውስጥ አንደሚያሳትፍ ነው የሚታወቀው ፡፡ የወደብ ተጠቃሚ መሆንና ለአሜሪካንም የሚሊቴሪ ቦታ መስጠት፣ ከኤርትራ ህዝብ ጋር እርቅ ማድረጉ እሰየው ነው ሆኖም የኤርትራን ስደተኛ አውሮፓን ማጣበቡ ያሰሰባቸው ለመፍትሄ ደፋ ቀና ሲሉ ፕ/ሚር ተብየው ምን ቃል እንደገቡለት ቢታወቅ ጥሩ ነበር፡፡ አውሮፓን በተለይ ኢትሊን ከሚያስቸግሩ ወይም በየባህሩ ከሚያልቁ
  ኢትዮጵያ ሥራ እየፈጠራላቸው ነው? አፈወርቂ አብሽር ስለሆነ አሁን ስደተኛ ስበቡን እያጠሩበት ነው፡፡

  አንድ ማስለመድ ያልብን ነገር ግን አስተዳደሩን ግልጽነትና ሃላፊነት እንዲኖረው ማስተማር አለብን፡፡ ህዝብ መጠየቅ አለበት፡፡የሚጠይቃቸው፣ የሚፈትሻቸው ያስፈልጋል፡፡

 6. ጊዜው የችሎታ ነው።አቶ ያሬድ ይህን ካሟላል በሚቀጥለው ዙር አንተም ሹመቱ ይደርስሀል።

 7. In the same way you also tried to explain I am not sure wether some of the cabinet members are eligible for the post. Having said that I am comfortable and strongly support the nomination of a woman (even with burka) as long as it would serve to disrespect & humiliate the majority of liar; corrupt; uncivilized; inhuman; illitrate; coward & baby killer TPLF generals who do not deserve such the post.

 8. የካቢኔቱን ሹመት ስመለከት የተደበላለቀ ስሜት ላይ ሆኜ በሙሉ ልብ መደገፍ ህሊናዬ አልቀበል ብሎኝ ግን በሴትነቴም ፆታዊ ድጋፍም እንድስጥ በሌላ በኩልም የሀገሬ ለሙያው ብቁ ሰው እንደሚገባት በማመን ለአሁን ብተለይ አገሬ ላለችበት ትርምስ እና ምን ያህል እውቀትና ልምድ ያለው ዜጋ ብቻ እንደሚያስፈልጋት ራሴን በማሳመን በመከላከያ ሚኒስትሩ ቦታ ላይ የተሰጠውን ሹመት ከመደገፍ ተቆጠብኩ አቶ ያሬድ ውሳኔዬን አጠናክረህ የህሊና እረፍት ስልሰጠኝ አመሰግናለሁ
  ሌላው የገረመኝ ፓርላማው እነዚህን እጩዎች ለማፅድቅ ሲያቀርቡላቸው እንደዚህ ባንዴ መርቀው ይሸኟቸዋል ብዪ አልጠበቅኩም ምንም አይንት debate ሳይደረግ ህዝቡም ስለነሱ ማንንት through the debateሳያውቅ ሸኝቷቸው እርፍ? ባጠቃላይ ይሄ ፓርላማ ወይ ከእውቀት ነፃ የሆነ የማይሰማ የማይልማ ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚል ክምችት ነው ወይም በህብ የተመረጠ የሚመስል ግን ከውስጥ ተፅኖ ያለበት አለያም የጎልማሶች መዋእለ ህፃናት
  ለማንኛውም ዞሮ ዞሮ አብዪታዊ ዲሞክራሲ እና ethnic federalism የሚባል የዞረበት ርእዮተ አለም ከስሩ ካልተመነቀለና አህዱአዊ Democratic መንግስት እስካልተቋቋመ ድረስ ፓርላማውም እየሄደ ይተኛ ዘረኛውም ጠባብነትን ትርጉሙን አጥቶ እስኪያጥወለውለው ድረስ ዘረኝነቱን ያጡዘው
  Oppositions የሚባሉትም እርስ በርስ እየተባሉ የስርአቱን እድሜ በማራዘም ይተባበሩ
  እኛም በኢትዮጵያ አንድነት የምናምነው ያለው ብቸኛ አማራጫችንን ፆምና ፀሎት እንቀጥል

 9. የጥላቻ ፓርቲ ሊቀመንበር በየ ሚዲያው እና በየመድረኩ ጥላቻንና ዘረኝነትን የሚሠብኩ ብዙ ግለሰቦች አሉን ። በ 47 ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በሠላም ፣ ደም ሳይፈስ ዴሞክራሢን እንገምባ የሚል መሪ ( አብይን ) ስናገኝ አሻፈረን ማለታችን በጣም ያሳዝናል ።
  የኢትዮጵያን ውድቀት የሚመኙላት ጠላቶቿ ናቸው ። ዕድላችንን አናሳልፍ ።
  በሀገሪቱ ሕግ እና ሠላም የበላይ ሆነው ከሠፈኑ ብልፅግና እድገት እና ዴሞክራሢን ልንገነባ እንችላለን ።
  ማንም ኢትዮጵያዊ ከሕግ በታች ወይም በላይ መሆን የለበትም ፤ ዘረኛውንና ጎሠኛውን እናርቅ ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.