ታዬንም አየነው! (ጌታቸው ሽፈራው)

ታዬንም አየነው! (ጌታቸው ሽፈራው) 1ታዬ ደንድአን በአካል አላውቀውም። ስለ እሱ ግን አሳዘኝ ታሪክ አንብቤያለሁ። ሰምቻለሁ። በአፋኞች ምክንያት የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ያቋረጠበት ታሪክ የግፍ ሰለበዎች መከከል ሆኖ እንድናውቀው አድርጎናል። በሁለተኛው ጊዜያዊ አዋጅ ከታሰሩት መከከል የታዬን ያህል የተጮኸለት ያለ አይመስለኝም። ይህ ጩኸት ከምንም የመጣ አይመስለኝም። የበደል ገፈት ቀማሽ በመሆኑ ነው።

ይህ ሰው የኢህአዴግ ስልጣንም ቢሆን የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ ሲሆን ብዙ ሰዎች በዚሁ ፌስ ቡክ ደስታቸውን ሲገልፁ አንብቤያለሁ። ይህን ያደረጉት የአፋኞችን የግፍ ፅዋ የቀመሱት እነ ታዬ እንደቆዩት አሳሪዎች አይሆኑም በሚል ነበር። ሆኖም ታዬን፣ ያን በትህነግ/ህወሓት ዘመን የግፍ እስር ቀማሹን ታዬን ዘመን ሰጥቶት፣ ከአሳሪዎች ወገን፣ ከከሳሽና አሳሪው መስርያ ቤት ደመወዝ እየተከፈለው የሚያረምደውን አመለካከት አየን። ታስሮ የተጮኸለት ታዬ፣ ስለ ታሰሩት መጮህን ወንጀል ሲያደርገው አዬን። በወራት ልዩነት!

የታዬ ደንድአ አቋም የለየለት ከኦነግ አቀበበል፣ ከቡራዩው ጭካኔ በኋላ ነው። በዛን ቀን እንደ አቃቤ ሕግ ቃለ አቀባይ ሳይሆን እንደ ድሮው መለስ ዜናዊ “እንተያያለን” ብሎ በይፋ ፎከረ። እንደፎከረው በሁለት ሶስት ቀን ውስጥ የአዲስ አበባ ወጣቶች በጊዜያዊ አዋጁ፣ በ1998፣ በደርግ ዘመን እንደሆነው ሲታፈሱ እየየን ማመን አቃተን። ይህን እነ ታዬ በሕግ አግባብ እንደተደረገ ያወሩታል።

ሰሞኑን ስለ አዲስ አበባ ወጣቶች አፈሳ ዘመቻ ተጀምሯል። ታዬ ዛሬ በፃፈው ፅሁፍ “የፖለቲካ አሻጥር ነው” ብሎ ፅፏል። ያን ልብ የሚነካ የታዬ ደንድአ የእስር ታሪክ ሲነገረንም የፖለቲካ አሻጥር ነበር ማለት ነው። ታዬ በአዋጁ ሲታሰር የተደረገው ዘመቻም አሻጥር ነበር ማለት ነው። ወጣቶች አዲስ አበባ ከእስር ይፈታል ብለው በፀሀይ እስር ቤት በር ላይ ቆመው የዋሉት፣ ሲወጣ አበባ ይዘው የተቀበሉት አሻጥር ነበር ማለት ነው! ብቻ ያን የመከራ ቀን ያየውን፣ በእስር የተሰቃየውን ታዬ ደንድአም በፖለቲካ እስረኞች ሲቀልድ፣ ፍትህ ላይ ሲያላግጥ አየነው።

ታዬ በዛሬው ፅሁፉ “ሁኔታዉ ከቁጥጥር በላይ ሆኖ የበለጠ አደጋ እንዳይከሰት እና ጥፋተኞቹን ለህግ ለማቅረብ ሲባል ፖሊስ የጠረጠራቸዉን ሰዎች ይዟል።” ይለናል። የሆነ እውነታ አለው። ገና አዲስ አበባ ላይ ተቃውሞ ይገጥመናል ብለው ነው ወጣቱን ያፈሱት። ለዛም ነው “ሁኔታው ከቁጥጥር በላይ ሆኖ የበለጠ አደጋ እንዳይከሰት” የሚለን። ገና ስጋት ነበር፣ የተቃውሞ ስጋት ነበር። ለዛም ነው ይሄ ነው የሚባል ወንጀል ሳይሆን ለስልጠና ወታደራዊ ካምፕ ያስገቧቸው። ለዛ ነው “አጣርተን እናስራለን እንጅ አስረን አናጣራም” እያሉ ከሕግ ውጭ በግድ ሊያሳምኑ የወሰዷቸው። ታየ በአዋጁ ሲታሰር ማዕከላዊ ነው። ጠበቃ ይጠይቀው ነበር፣ ቤተሰብና ጓደኛ ይጠይቀው ነበር። እስር ቤቱ ጭካኔ የሚፈፀምበት ይሁን እንጅ በሕግ የታወቀ መቆያ ነው። ታዬ አንድ ቃለ አቀባይ ሆኖ በሚፎክርበት ዘመን ግን የታፈሱት የታሰሩት በሕግ በማይታወቅ እስር ቤት ነው፣ ጠበቃም ቤተሰብም አይጠይቃቸውም። እነ ታዬን እነሱ ከነበሩበት የስቃይ እስር ቤት በከፋ ወጣቶቹን ሲያሰቃዩ፣ ይህን የመከራ እስር ሕጋዊ ለማስመሰል ሲጥሩ አየን። እነ ታዬን ከአሳሪዎቻቸው ብሰው አየን! የጭካኔ ሰለባ የሆኑት እነ ታዬ ይበልጥ ጨክነው አየን!

እነ ታዬ፣ ይህ የትግል ውጤት የእኔ ነው የሚሉት ጋር ሆነው “አስፈታን እንዳትሉ” እያሉን ነው። ይህ የአንድ ጊዜ ግፊትን ላለማመን የተፃፈ ብቻ አይደለም። ወደፊትም ምንም አታመጡም፣ ካሰርነው እኛ ካልፈለግን በጫና ማስፈታት አትችሉም እያለን ነው። የመለስ ዜናዊና ከእነ አብይ የቀደመው ጊዜ እንዳላለፈ ሁሉ፣ በጫና ብዙ እስረኛ እንዳልተፈታ ሁሉ ታዬ “ያለፈውን በእኛ ዘመን ማድረግ አትችሉም” እያለን ነው። ማስፈራሪያ ነው። እብሪት ነው! ያን ሁሉ ግፍ ካየ ሰው የማይጠበቅ እብሪት ነው! ጊዜ ደጉ ታዬንም ስልጣን ላይ ሆኖ አየንው! ከሳሽ ሆኖ አየነው! አሳሳሪ፣ የአሳሪዎቹ ወገን ሆኖ አየነው!

ታዬ የከሳሽ አቃቤ ሕጉ ቃል አቀባይ ነው። እንደ እውነቱ የእስካሁኑ አቃቤ ሕግ አሳሪነቱ እንጅ በቃለ አቀባዩ በኩል ፈላጭ ቆራጭነቱን፣ ፉከራውን አናውቀውም። ከታዬ በፊት እንደዚህ እየወጣ ቡራ ከረዩ የሚል የአቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ አላስታውስም። የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ካልሆነ በስተቀር። ታዬ የከሳሽ አቃቤ ሕግ ቃለ አቀባይነቱን ብቻ ሳይሆን የፓርቲ ጎራን ፅንፍ ይዞ እያስፈራራ ነው። ሌላው 3 ሺህ አመት ሲለን፣ ታዬ ያ ክፉ አገዛዝ ከዛሬ እንደሚጀምር እያሳየን ነው።

ታዬ በመጨረሻው አረፍተ ነገር እንቅጩን ነግሮናል። “ፖለቲካዉ ገብቶናል!” ብሏል። የዚህ ሀገር ፖለቲካ፣ የኢህአዴግ ፖለቲካ እስር ነው፣ አፈሳ ነው፣ አፈና ነው፣ እብሪት ነው። በፖለቲካ የሚባል ነገር አለ። ስልጣን ያበላሻል። ታዬ ብቻ ሳይሆን ዋናው አቃቤ ሕግ የቲም ለማ አካል ነው፣ ታዬ ስለ አዲስ አበባ ወጣቶች በጭካኔ እንደሚናገረው ሁሉ ከንቲባውም በተመሳሳይ ይናገራል። ከንቲባውም የቲም ለማ አባል ነው። ብዙ ቦታ እነ ቲም ለማ አሉ። አዎ ስልጣን ያበላሸል። ስብአዊነትን ይገድላል። ፍፁማዊ ስልጣን ሲሆን ደግሞ የራስን የክፉ ቀን ታሪክ ጨምሮ ያስረሳል። የግፍ ሰለባ ያደረጉት የቀድሞ አሳሪዎች የከፋ አሳሪና ጨካኝ ያደርጋል! ስልጣን ክፉ ነው። ጊዜ ደጉ እነ ታዬም ታሪካቸውን ረስተው፣ ከአሳሪዎቻቸው ብሰው አየን። ስልጣን ክፉው፣ ፍፁማዊ ስልጣን ክፉው፣ ለፍፁማዊ ስልጣን ማሰብ ክፉው እነ ታዬንም ክፉ አድርጎ አሳዬን!

2 COMMENTS

 1. ሁሉን መነካከስ ተጣብቷችሁ እንደ አበደ ውሻ ያንንም ይህንንም ትለካክፋላችሁ ምን አልባት ምክንያታዊነት መልካም ነበር በሻይ ጓደኞቻችሁ ሞራል ታላቁን ጉዳይ መነካካት አክቲቪስት አያሰኝም ፤

  መራርነት በተጠናወተው ጣዕም አልባና ድንግዝግዝ በሆነ እይታችሁ በምታስተላልፉት ጠብ አጫሪ መልዕክት ብዙዎች ተጎድተውበታል ፤ እናንተ አይጦቹ በምትበሉት ደዋዉ ተመትቷል ፤

  ምን አልባት የመጻፍ ሱስ እንጂ እውቀቱ የላችሁምና ጥበብ ይጎድላችኋል፤ ሁሉን በመተቸት መና ማስወረድ የምትችሉ ይመስላችኋል፤ አንድም ጥበብ አልባ ጠባቦች ናችሁና እኛ (አማሮች)ካልወጠወጥነው አይጣፍጥም ዓይነት ሸውራራ እይታ የሌሎችን ስራ ማጠልሸትን እንደስራ ይዛችሁ ለጥፋት ትታትራላችሁ ፤

  ያን ደግ ህዝብ (አማራን)ያላወቀ ሰው የእናንተን ክፋት እና ተንኮል ብቻ በማየት ከስህተት ላይ ሊወድቅ ይችላል፤ ምክንያቱም ላትወክሉት የጥላቻ አረም እየዘራችሁለት ነውና ፤ በየቦታው የሚፈናቀለው አለብላቢት ምላሳችሁ በምታመጣበት ጣጣም አይደል? ዳሩ እናንተ ምን ተዕዳችሁ? አበሳው የምሥኪኑ!

  ያልገባችሁ አንድ ነገር ከጊዜው ጋር መራመድ አለመቻላችሁ እና በድሮ በሬ ለማረስ መታተራችሁ ነው ቀድሞ በመጮህ እና የሌላውን ጀብዱ የራስ አስመስሎ በመተረክ ታሪክን የመንጠቅ ደባ ጊዜው አልፎበታል ፤
  ስለዚህ መፈራገጥ ከመላላጥ ውጭ አንዳችም የሚፈይደው ነገር አይኖርም ስለዚህ መሆን ያለበት ሁሉ እናንተ ስለተንጫጫችሁ ሳይሆን የሚቀር አይሆንም፤ ጫጫታችሁም የሚለውጠው ምንም ነገር አይኖርም ፤ እንደተባለውም “ጅቦቹ ይጮሃሉ ግመሎቹ ግን ያልፋሉ”

 2. The lumpens and their coordinators will face justice and be punished for their misbehaviors. We will not let anarchy. Campaigning against the Oromo will not serve your latent racism. It is better if you shut up your filthy mouth.

  In the last couple of days you have been campaigning against the beloved Oromo sons, Taye Danda’a and Takle Uma. But it is futile. For you and those like you it doesn’t matter what ever happens to the Oromo. Where are you when the Oromo deprived their rights every where and everyday all over in that country? The Oromo nation doesn’t deserve human dignity?

  The hooligans and pseudo journalists of the ESAT TV and the so called Getachew Shifera claim the savoir of Ethiopia is only G7 and the wise leaders are only the arrogant Berehanu Nega and the racist Adergschew Tsege . All other alternatives are nonsense and unacceptable for them.
  Most of you including these hooligans appreciate and acknowledge all efforts against the basic human rights of the Oromo people. Even you have no problem with Woyane as far as it is against the Oromo interests. For example most of you were cheering as Woyane declared the so called Addis Ababa Master plan. It is you main motto to appreciate all individuals like the Debtera Labero, Getachew Haile, this boy and other anti-Oromo elements. But you don’t want to hear about the very bright minded Oromo like Dr. Tsegaye Ararassa, Jawar Mohammed, Prof. Ezekiel Gabissa, Prof. Abbas Genamo and so on. That is way I say that the way of your thinking is outdated and not modern and contemporary.

  The struggle of the Oromo nation is not against any nation in this country. It is only against subjugation, exploitation, discrimination and forcibly imposed assimilation. We believe the Oromo nation is the pillar of peace, stability, security and prosperity of the Horn of Africa. You should have to accept these facts and work with us so that we can promote together mutual understanding and respect.

  Change your way of thinking! Give up bad mentality! Think with you mind but not with your belly!

  Narrow nationalists and primitive minded individuals are those who are against the democratic rights of the different nations in Ethiopia. They have been using always derogatory terminologies in order to undermine the demands of the Oromo nation. Those individuals are desperate and hopeless. No more business as a usual.

  No to the Oromo phobia!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.