የቀድሞ ብአዴን የአሁኑ የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባለት በሚኒስትሮች ሹመት ደስተኛ አለመሆናቸውን ይናገራሉ

ዶ/ር አምባቸው መኮንን

ዶ/ር አብይ ሁለቱን እሳተነበልባል የአዴፓ ትንታግ አመራሮች በአዲሱ የሚኒስተር ሽግሽግ ቦታ የነሳቸው በቅርቡ ሀዋሳ በተካሄደው የኢህአዴግ ጉባኤ የወልቃይትና ራያን የማንነት ጉዳይ ላይ ባሳዩት የከረረ አቋም እንደሆነ ተጨባጭ ጥቆማ ደርሶናል፡፡

 

አሁን አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ዶ/ር አብይ አማራጭ አልባ መሪዋ እንደሆነ ባንጠራጠርም ሁለቱን የአዴፓ አመራሮች በአቋማቸው ምክንያት የሚመጥናቸው ቦታ ላይ ማግለል ወያኔ መላኩ ፋንታን ባህርዳር በነበረው ተማሳሳይ የኢህአዴግ ጉባኤ ተንኮል ከሸረበበት አካሄድ ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡

ይህ በንዲህ እንዳለ እንደ ወልቃይት ጠገዴ አማራ ምንጮች ዶክተር አምባቸው መኮንን የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚሾሙ ታውቋል፡፡

በብአዴን በዋና የፊት መስመር የለውጥ ሞተር ሆኖ የሚታወቅ ሰው ዶክተር አምባቸው መኮንን ነው፤ ነገር ግን ጠ/ሚ/ር አብይ የዶ/ር አምባቸውን አቅምና አቋም ጠንቅቆ ስለተረዳ እና በኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ጊዜ በአማራና በትግራይ ሕዝብ መካከል ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የወልቃይትና የራያ ጉዳይ ምላሽ ማግኘት አለበት በማለት በሚያነሳቸው ጥያቄዎች የተነሳ ዶ/ር አምባቸውን ከፌደራል ስልጣን መዋቅር ውስጥ እንዳይካተትና ከፖለቲካ ተሳትፎው ለማራቅ በማሰብ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ቦታ እንደተያዘለት የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴዎች የተሰራውን ሴራ በግልፅ ይናገራሉ።

በተደረገው የሚኒስትሮች ሹመትም የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ደስተኛ አለመሆናቸውንም ይናገራሉ፤ ሹመቱ አዴፓን አግልሏል ለአዴፓ የተሰጠውም ሹመት አቅም የሌለው የስም ብቻ ነው በማለት በአቶ ገዱና በአቶ ደመቀ ላይ ከፍተኛ ትችት በማቅረብ ይሄ አይን ያወጣ ህገ ወጥ የዘረኝነት አካሄድ አዴፓን ወደፊት ዋጋ እንደሚያስከፍለው ሳይታለም የተፈታና ግልጽ ነው ብለዋል።

ዶ/ር አምባቸው መኮንን ሹመቱ በአማራ ክልል ምክር ቤት ሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2011 ዓ.ም ይሰጣቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.