በመዲናዋ ከ161 ሺህ በላይ አዳዲስ የስራ እድሎችን ለወጣቶች የሚፈጥር መነሻ እቅድ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ161 ሺህ በላይ አዳዲስ የስራ እድሎችን ለወጣቶች የሚፈጥር መነሻ እቅድ ቀረበ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ዕድል ፈጠራና የኢንተርፕራይዞች ልማት ምክር ቤት የጋራ የምክክር መድረክ ዛሬ በሂልተን ሆቴል ተካሂዷል።

በምክክሩ መድረኩ ላይ የስራ ዕድል ፈጠራና የኢንተርፕራይዞች ልማት ምክር ቤት አሰራርና አደረጃጀት መመሪያ እንዲሁም የ2011 በጀት ዓመት የባለድርሻ አካላት የስራ እድል ፈጠራ እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በከተማዋ አስሩም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶችን ማወያየታቸው ይታወሳል።

በወቅቱም ወጣቶቹ የስራ እድል ፈጠራ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ለምክትል ከንቲባው አንስተው ነበር።

ይህን ተከትሎም በስራ እድል ፈጠራና በኢንተርፕራይዞች ልማት ላይ የሚሰራ ምክር ቤት ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል።

የቀረበው የስራ እድል መነሻ እቅድ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቀውና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ስልጠና አጠናቀው የስራ እድል ለሚጠባበቁና በተለያየ ምክንያት ስራ አጥ ሆነው ለቆዩ ወጣቶች ነው ተብሏል።

ኢንጅነር ታከለ በዚህ ወቅት ለጊዜው የታቀደው ቁጥር ብዙ አለመሆኑን ጠቅሰው፥ የከተማ አስተዳደሩና ምክር ቤቱ ልዩ ትኩረት በመስጠት ቁጥሩን ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ነው፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.