ኦብነግና የኢትዮጵያ መንግሥት አስመራ ውስጥ ምን ተስማሙ? (DW Amharic)

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) የሶማሌ ሕዝብ «ዕጣ ፈንታውን በነፃነት ራሱ መወሰን እንዳለበት» ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከስምምነት ላይ እንደደረሰ መናገራቸው ተዘገበ። የኦብነግ የውጭ ግንኙነት ጸሐፊ አቶ አህመድ ያሲን ሼክ ኢብራሂም፦ «ሕዝበ- ውሳኔ እንዲካሄድና ሕዝቡ ከኢትዮጵያ ጋር ለመቆየት ከፈለገ ያ መብቱ እንዲከበር፤ መገንጠል ከፈለገ ያ ውሳኔ እንዲከበርለት ውሳኔ ላይ ደርሰናል» ሲሉ ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ በድረ-ገጹ ዘግቧል።

ባለፈው እሁድ አስመራ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦብነግ ተወካዮች የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ቢገለጥም ዝርዝሩ ግን አልተነገረም ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት አስመራ ውስጥ ከኦብነግ ጋር ስለደረሰው ስምምነት ዝርዝር ኹኔታ እንዲያብራሩልን ለመጠየቅ የውጭ ጉዳይ ሚንሥቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ጋር ዛሬ ጠዋት ደውለን ነበር። በደወልንበት ሰአት ማነጋገር እንደማይችሉ ገልጠው፦ «ከቀኑ 10 ሰአት መልሰን እንድንደውልላቸው» ነግረውናል። የጠቅላይ ሚንሥትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋም ጋር በተደጋጋሚ ብንደውል ስልካቸው አይነሳም። ጉዳዩን በተመለከተ ከመንግሥት በኩል መረጃ እንዳገኘን ወዲያውኑ ለማቅረብ እንሞክራለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.