የህወሓት  ኢምፖርት ኤክስፖርት ንግድ ሞኖፖሊ!!! የባንክ ውጭ ምንዛሪ ለወያኔ ሲሳይ   (ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር››     ሚሊዮን ዘአማኑኤል)

ኢት-ኢኮኖሚ      /ET- ECONOMY

ለመምህራን መህበር መሪ ለነበረው በግፍ በወያኔ የተገደለው አቶ አሰፋ ማሩ መታሰቢያ ትሁን፣ ገዳዬቹ ለፍርድ ይቅረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ 21 አባላት ያሉት የፕራይቬታይዤሽን ምክር ቤት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ መብት ኃይል፣ኢትዮቴሌኮም፣ በማቆቆም የመንግስት ድርጅቶችን በከፊል ወደ ግል የሚዘዋወሩበትን ሂደት ግልፅና ተጠያቂነት እንዲኖረው ለማድረግ ኃላፊነት ተሠጥቶቸው ሥራ ጀምረዋል፡፡ የፕራይቬታይዤሽን ፕሮግራሙ በፓርቲዎች የንግድ ድርጅቶች የባንክ፣ ኢንሹራንስና ማይክሮ ፋይናንስ ድርጅቶች፣ ኢፈርት፣ ሜቴክ፣ ጥረጥ፣ ዲንሾ፣ ወንዶ  ድርጅቶችን በማጠናከር ሥራዎች ላይ ተጠምደው ለስድስት ወራት ሥራ ክንውናቸው በኢኮኖሚው ዘርፍ አሣማዎቹን ሊፒስቲክ በመቀባት ቆንጆ ለማድረግ የማህይም ስራ ላይ ተጠምደዋል፡፡ ይሄም ሳያውቁ ሳይሆን የህወሓት/ኢህአዴግ በትረ ሥልጣኑን ለኦህዴድ/ኢህአግ ሲያስተላልፍ ልማታዊ መንግስትና አብታዊ ዲሞክራሲ እንዲቀጥል፣ ህወሓት ሹማምንት ለህግ እንዳይቀርቡ ስምምነት፣ ህወሓት ትግራይ  ውስጥ ያለው መከላከያ ሠራዊት የአየር ጋይል ፣ የታንከኛ ብርጌድ፣ የጦር ግምጃ ቤቶች፣ የስለላ ተቆማት  ወዘተ እዛው እንዲቆዩ የኢኮኖሚ ምዝበራ ሁሉ እንዳይነሳ፣ የወልቃይት፣ የራያ፣ የአፋር ወዘተ ወደ ትግራይ የተጠቃለለ ህዝብ የማንነት ጥያቄ እንዳይነሳ፣ በተደረገ የፖለቲካ ስምምነት መሠረት ለኦህዴድ/ብአዴን ፖለቲካ ሥልጣን አስረክቦ፣ ህወሓት መቐሌ መሽጎ ሃገሪቱን ይበጠብጣል፡፡ ሽብር ስፖንሰር በማድረግ መሣሪያና ገንዘብ ያሰራጫል፡፡ ጥቅምት 7 ቀን 2011ዓ/ም በትግራይ ክልል ልዩ ሃይል አባላት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሰላማዊ ሠልፍ ላይ 8 ሰዎች በጥይት ቆስለዋል፡፡ በተመሳሳይ በአማራ ክልል ራያ፣ አላማጣና፣ ቆቦ ህዝብ ሠላማዊ ሠልፍ ላይ 5 ሰዎች ተገድለዋል ብዙ ሰዎች ቆስለዋል እንዲሁም ከአንድ ሽህ በላይ ሰዎች ታስረው፡፡ የወልቃይት ህዝብም ከቀየው እየተሰደደ ወደ ጎንደር ከተማ በመሄድ ይገኛል፡፡ የቻይና መንግስት በሽን ጃንግ ሙስሊሞችን በኮንስንትሬሽን ካንፖች እስር ቤቶች እየገነባች እንደሆነ በሳተላይት በማጋለጥ ቻይና መንግሥት ሙስሊም ዜጎቾን በማሰር እያስተማርናቸውና እያሰለጠንናቸው በማለት ለዓለም ህብረተሰብን ሲያጭበረብሩ እንዳለ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ከሰሞኑ አጋልጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአንድ ሽህ በላይ የአዲስ አበባ ወጣቶችን በግፋ አስሮ ፍርድ ቤት ሳያቀርብ ጦላይ ወስዶ ማሰሩ ከቻይና መንግሥት የተማረው የስልጠና ፕሮግራም  መሆኑ በዚህ አረጋግጠናል፡፡ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በወሎ ሀዝብ አላማጣ ቆቦና ራያ፣ በጎንደር ህዝብ ወልቃይት፣ በአፋር ህዝብ የሚፈፅመው የግፍ አገዛዝ እንደቀጠለ መሆኑ ለማወቅ ተችሎል፡፡ የህግ ሉዓላዊነት በሃገሪቱ ውስጥ እንደ ዜጋ ተዘዋውሮ የመስራት መብትና ሃብት አፍርቶ መኖር ዋስትና፣ ስራ አጥነት ሌላ ያገኘው ጥቅም የለም፡፡  አዲስ የኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ፣ የማክሮና ማይክሮ ኢኮኖሚ እቅድና የንዋይ መሠረተ ልማት ሲገነባ ብቻ በፖለቲካ በትረ ስልጣን ላይ መቆየት ይቻላል፣ ኢኮኖሚውን የሚመሩ በተግባር ሊቀይሩ የሚችሉ ፖለቲከኛ ያልሆኑ ቴክኖከረራቶች ያስፈልጋሉ፡፡ የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ግኝታቸው 30 በመቶ ለብሄራዊ ባንክ የሚሸጡበት ተመን  በመግዣና በመሸጫ መካከል ባለ (አማካይ) ዋጋ እንዲሆን የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ወስኖል፡፡ የግል ባንኮቹ የህወሃት የፖለቲካ ድርጅቶች የንግድ ድርጅቶች ናቸው፣ በዘር የተደራጁ ወጋገን፣ አንበሳ፣ እናት (ህወሃት)፣ የብአዴን፣ የኦህዴድና የደኢህዴድ ወዘተ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና ማይክሮ ፋይናንስ ድርጅቶች መሆናቸውን መግለፅ ግድ ይላል፡፡ የኢህአዴግ ባንኮች በወንጀል ተጸንሰው በሃጢኣት ይወለዳሉ! (“Banking was conceived in iniquity and born in sin.” Josiah Stamp) የባንክ ፋይናንሻ ዘርፍ ውድቀት በመንግሥት ፖሊሲ ብልሹነት፣  በመልካም አስተዳደር እጦት በሙስናና ሌብነት የብድር አሰጣጥ፣አሰባሰብና የተበላሸ ብድር ቁጥጥር መላላት፣ አድሎዊ አሰራር፣ ግልፅና ተጠያቂነት ያለው የባንክ ህግና ደንብና መመሪያ እጦት፣ ስግብግብነትና ግለኝነት ይነግሳል፡፡ “ The banking collapse was caused, more than anything, by bad government policy and the total failure of bad regulation, rather than by greed. “ Niigel Farage ዲያስፖራው የውጭ ምንዛሪ በምን ዘርፍ ላይ እንደሚውል መረጃ ከሌላቸው ገንዘባቸው ለወያኔ ገቢ ይሆናል፡፡

{1} 27 በመቶ የብሔራዊ ባንክ ሠነድ (ቦንድ) ግዥ፣ ባንኮች ከእያንዳንዱ ከሚሠጡት ብድር 27 በመቶ የብሔራዊ ባንክ ሠነድ (ቦንድ) ግዥ በማዋል  አነስተኛ 3 በመቶ ወለድ ያገኛሉ፡፡ የብሔራዊ ባንክ ደግሞ ለልማት ባንክ በመስጠት ባንኩ ለማኑ-ፋክቸሪንግና ለመሳሰሉት እንዲያበድር ያደርጋል፡፡ በዚህም የአገሪቱ ኦኮኖሚ ለማሳደግ ዋናው ኢንቨስትመንት እንደመሆኑ መጠን ለዚህ የሚሆን የረዥም ጊዜ ብድር የሚሆን ለማግኘት አስችሎል፡፡ የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ለህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ያለገደብ ያበድራል ፡፡ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክና የኢትዩጵያ ልማት ባንክ በመንግሥት ቀጭን ትዕዛዝ ያበድራሉ፡፡ የኢፈርት ብድር በቀጭን የስልክ ትዕዛዝ ይሠርዛል፡፡ የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ፣ባንኮች ከሚሰጡት  ብድር 27 በመቶ ለሰነድ ግዥ እንዲያውሉ፣ኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ደግሞ ለልማት ባንክ በመሰጠት ባንኩ ለማኑፋክቸሪንግና ለመሳሰሉት እንዲያበድር ለማድረግ ታቀደ፡፡ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ይሄን ገንዘብ  ለደንበኞቹ ቢያበድር፣ የበለጠ ትርፍ ማግኘት ይችል ነበር፡፡ እንዲሁም የግሉ ዘርፍ የብድር አቅርቦት ይጨምር ነበር፡፡ ‹‹27 በመቶ የብሔራዊ ባንክ ሠነድ (ቦንድ) ግዥ መመሪያ ለለውጥ ምክንያት ሆኖል፡፡ የባንኮች የትርፍ መጠን ይቀንሳል የተባለውም  እኮ አልሆነም፡፡ እንዲያውም የአገራችን ባንኮች የትርፍ  ድርሻ ምጣኔ ከዓለም አንደኛ ነው፡፡ 100 ብር አክሲዩን ያለው ሰው 40 ብር ትርፍ ያገኛል፡፡ 1000 ብር አክሲዩን ያለው ሰው 400 ብር ትርፍ ያገኛል፡፡10,000 ብር አክሲዩን ያለው ሰው 4000 ብር ትርፍ ያገኛል፡፡ ይህ በዓለም የሌለ ነው፡፡ ከፍተኛ ተብሎ የሚጠቀስ የትርፍ ድርሻ ነው፡፡ ገና በሚያድጉ አገሮች እንኮ ትልቅ የትርፍ ክፍፍል ድርሻ 20 በመቶ ነው፡፡ ወደ ትልልቆቹ አገሮች ብትሄድ የትርፍ ድርሻው አምስትና ስድስት በመቶ ነው፡፡›› ከኢትጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ የፋይናንስ እውቀት በጣም አጠያያቂ ያደርገዋል፡፡ ከውጭ ባንኮች ጋር መወዳደር ያልቻሉ ባህላዊ ያልሠለጠኑ ባንኮች ትርፍ የተመሰረተው በደንበኞች ባስቀመጡት ገንዘብ ርካሽ ወለድ በመስጠትና ለተበዳሪዎች በከፍተኛ ወለድ በማበደር የተገኘ እንጂ በባንኮች ትጋትና አገልግሎት መሥጠት አይደለም፡፡ የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ የነበሩት በጊዜው እንዳሉት ‹‹ባንኮች ከሚያበድሩት ገንዘብ 27 በመቶ እየቀነሱ ቦንድ እንዲገዙ የተገደዱት ለዓባይ ግድብ መዋጮ ሳይሆን፣ ለኢንዱስትሪ ልማት ነው ማለታቸው በየትኛው የመንግስት ፖሊሲ ላይ ተመሥርተው እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ሁሉም ሰው እንደሚያውቀው፣ 27 በመቶ የግዴታ የቦንድ ግዥ ለዓባይ ግድብ መሆኑ ይፋዊ በሆነ መንገድ የተገለፀ መረጃ ነው፡፡ ይህ የግዴታ ቦንድ ግዥ በባንኮች ላይ ምንም ጉዳት አላደረሰም ማለታቸው አስገራሚ ነው፡፡ አክለውም ይህ አዲስ ነገር አይደለም‹ እንዲያውም በህንድ 40 በመቶ ነው ብለዋል፡፡ ይህን መረጃ ለማረጋገጥ ሞክሬ አልቻልኩም፡፡››ተክለብርሃን ገብረሚካኤል ሞግቶቸዋል ነበር፡፡  የባንክ ባለአክሲዩኖች እስከ አርባ በመቶ የትርፍ ክፍፍል ድርሻ እንደሚያገኙ ገልፀዋል፡፡ ይህ እውነት ነው፡፡ የባንኩን ዘርፍ ጥቂት ባንኮች በከፊል ሞኖፖል ስለተቆጣጠሩት ነው፡፡ የአገር ውስጥ የግል ባንኮች ከብሄራዊ ባንክ ‹‹ 27 በመቶ ቦንድ ›› ብሄራዊ ባንክ የሚከፍላቸው ወለድ አሁን ካለበት 3 በመቶ 5 በመቶ ከፍ ማድረጉ ታውቆል፡፡

{2} ልማት ባንክ በህወሓት/ ኢህአዴግ  የፓርቲ የንግድ ኩባንያዎች ቁጥጥር ሥር ይገኛል፡፡ አሁንም የግሉ ዘርፍ የብድር አገልግሎት አያገኝም፡፡ የባንኩ ባለሥልጣኖች በስልጣናቸው የተደራጁና በጥቅም የተሳሰሩ በፖለቲካ ኔትወርክ የተጠላለፍ በመሆናቸው ለውጥ አይመጣም፡፡ ልማት ባንክ በኢህአዴግ ህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣  እና ደኢህዴን ካድሬዎች ቢተካካ ለውጥ አይመጣም የሰውለውጥ ሳይሆን የሚያስፈልገው የንዋዩን መሰረተልማት ማስለጥ የግሉን ዘርፍ እንዲሰራ ማድረግ፣ የካፒታል ማርኬት ሥርዓት መዘርጋት፣ የባንክ ባለሙያን ከፖለቲካ ካድሬ ሥራ መለየት ግድ ይላል፣ በባንኮች ስራ ጣልቃ አለመግባት የመሳሰሉት መተግበር አለባቸው፡፡ የባንኩን የብድር አሰጣጥ፣ አሰባሰብ በግል ዘርፍ፣ በኢኮኖሚ ዘርፍና በክልሎች የሚሠራጨውን የባንኩን አጠቃላይ አሰራር አስተካክሎ ግልፅና ተጠያቂነት ያለው አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ ነው፡፡  የባንኩ የቀድሞ ብልሹ አሰራር ሙያተኞች በአዲስ እስታልተተኩና እስካልተጠየቁ በህዝብ ገንዘብና ሃብት መቀለድ ነው የሚሆነው፣ ለውጥ አይኖርም፡፡

{3} ሜቴክ/ የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን  በሰኔ ወር 2009ዓ/ም 850 አውቶብሶች ለአዲስ አበባ ትርንስፖርት ባለሥልጣን  በ3.4 ቢሊዮን ብር  ሰርቶ ለማስረከብ የተዋዋለውን ውል 100 ብቻ በማስረከብ 700 ሊያስረክብ ያልቻለ ሌባ ድርጅት ይዞ መጎዥ ይልቅ ለህዝብ በአክሲን መሽጥ ይኖርበታል እንላለን፡፡ ሜቴክ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የተሠጠው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ልምድ የሌለው የእንግዴ ልጅ ሜቴክ እስካሁን አለመቆረጣቸው የፕሮጀክቱ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስኪያጅ ኤፍሬም ወ/ኪዳን አስታውቀዋል፡፡ ዶክተር አብይ አሳማውን ሜቴክ ሊፒስቲክ ቀብተው ሊያልፉት ዳድዶቸዋል፣ የማፍያ ድርጅት የልማት አጋር መሆን አይቻለውም እንላለን፡፡ የግድቡ ሰራተኞች በቀጣዩ ሥራ ላይ ተሳታፊ ሆነው ሃሳባቸው  ተደምጦ ከኢህአዴክ ካድሬ አስራር ተወግዶ በነፃነት መሥራት መብታቸው ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ ዶሞክራሲ ማለት እንዲያ ነው፡፡ ሜቴክ የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት የነበሩ ሁለት አብዬትና አባይ ወንዝ የተባሉትን ግዙፍ መርከቦችን  ከብዙ ኪሳራ በሆላ በህገውጥ መንገድ በመሸጡ ሊጠየቅ ይገባል፣ ዝርዝር የሙስናና የሌብነት ማስረጃው  የድረገፅ ወጥቶል፡፡ ሜቴክ ከ20 ሽህ በላይ ሠራተኞች ያሉትና በሥሩ 14 ንዕስ ኢንዱስትሪ ክፍሎችና 93 ፋብሪካዎች ለሁለት ተከፍለው ግማሹ በመከላከያ ሚኒስትር ስር፣ የንግድና የሲቪል ነክ ምርቶች የሚያመርቱት ደግሞ በኮርፖሬሽኑ ሥር እንደሚቆዩ የዶክተር አብይ መንግስት ተገልፆል፡፡ ሜቴክ የገማ ዘረኛ ሌባ ድርጅት ከግሉ ዘርፍ የነጠቀው ስራ ሳይውል ሳያድር ለግሉ ዘርፍ፣የሜቴክ የሲቪል ፋብሪካዎቹ የብሸፍቱ ኦቶሚቲቭ ጨምሮ በአፋጣኝ በአክሲዬን ለህዝብ መሸጥ ይኖርበቸዋል፡፡  ሜቴክ የወታደራዊ ዘርፉ ፋብሪካዎች ሥራ ብቻን በመስራት መቀጠል ይኖርበታል እንላለን፡፡ ሜቴክ የስኮር ኮርፖሬሽን 77 ቢሊን ብር ዘርፎ ለህግ ካልቀረበ ማንም ሹም ቢዘርፍ በህግ አይጠየቅም ህግ ተሸሮል ማለት ነው፡፡

{4} ጥረት / ብአዴን/አዴፓ የፓርቲ የንግድ ድርጅት የሚዘርፍቸው ከ20 የሚበልጡ ኩባንያዎች አምባሰል፣ዳሽን ቢራ፣ ዋሊያ ቆርኪ ፋብሪካ፣ ገንዳ ውሃ የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካ፣ጎንደር ብቅል ፋብሪካ፣ ጣና ኮሙኒኬሽን የማባይል መገጣጠሚያ ፣ አዛላ ኤሌትሮኒክስፋብሪካ፣ቲቲ ኢንጅነሪንግ ፣ ላፕላማ ዳይቶማይት ፋብሪካ፣ ጀሪ የተፈጥሮ ምንጭ ውሃ ፋብሪካ፣ ተላጅ የልብስ ስፌት፣ የቆቦ ዶሮ እርባታ፣ እንስሳት ማድለብና ስጋ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣  ጣና ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች፣ ቢዲሲ ኮንስትራክሽን፣ ተከራርዋ የፕላስቲክ ማምረቻ፣ ዘለቀ እርሻ መካኛይዜሽን፣ የዓሣ ላማት ፕሮጀክት፣ የትም የጂፕሰምና ውጤቶች ማምረቻ፣ ማዕድ የምግብ ኮምፕሌክስ፣ ቲአይ ሜታልስ ፈርሚንግ ፣የጁ ማርና ውጤቶች፣ የወተት ልማት፣ ጥቁር አባይ ትራንስፖርት፣ እሸት ስታርችና ውጤቶች፣ ጀርባ ፓኬጂንግ ፣ በለሳ የሎጂስቲክ አ.ማ ወዘተ  በአማራ ህዝብ ስም የበረከት ስምኦንና የታደሰ ጥንቅሹ የግል ኃብት መሆኑ በብአዴን አመራሮች ሲነገረን ቆይቶ አሁን ታድሶ ለተወሰኑ ከአማራ የወረዱ የአውራጃ ካድሬዎች ጎጃሜዎች፣ ጎንደሬዎች፣ ወሌዎች፣ የካድሬ ንብረት ለማድረግ ከልታሰበ በስተቀር ድርጅቶቹ ለግሉ ዘርፍ ተሸጦ ከብአዴን/አዴፓ የበሰበሰ የካድሬ መዋቅር ተላቆ መሸጥ ይኖርባቸዋል እንላለን፡፡ ህወኃት ብአዴን የነመለስ ዜናዊ በአማራ ስም የቱን አማራ እንደጠቀሙ የቱን እንደጎዱ የታሪክ ማህደር አንድ ቀን ያወጣዋል፣ የአማራ አሳማም የትግሬ አሳማም፣ የኦሮሞ አሳማም የደቡብም አሳማም አንድ ናቸው ፡፡ አሳማ አሳማ ነው! ፣ አሳማ አሳማ ነው! ፣ አሳማ……ሃቁ ያ ብቻ ነው ዘረኛ ዘረኛ ነው!!! የትግሬ ሆነ፣ የአማራ ሆነ፣ የኦሮሞ ሆነ የደቡብ ሆነ ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎ ስልቻ ነው፡፡ ከትግራ ወርዶ ወደ አውራጃ አድዋ፣ ሽሬ፣ አክሱም ሲባባሉ እንሰማለን፡፡ ከአማራ ወደ አውራጃ ወርዶ ጎጃሜ፣ ጎንደሬ፣ ወሌ፣ ሸዌ ሲባባሉ እናውቃለን፡፡ ከኦሮሚ ወርዶ በአውራጃ ወለጋ፣ ቦረና፣ አንቦ ወዘተ መንድር ለመንደር ውረድ እንውረድ ፖለቲካ ካድሬዎች  ሲባባሉ እናውቃለን፡፡  የፖለቲካ ፓርቲዎች ከንግድ ሥራ ውስጥ መግባት የለባቸውም፣ ፓለቲካ ፓርቲዎች በዘር፣ በሃይማኖት  መደራጀት የለባቸውም እንላለን፡፡(Political parties  organized with ethnic tags are not political parties. They are as one of civic and religious organizations or activists dealing with ethnic issues and are not political parties. It is the most dangerous and destabilizing agent organizing political party along ethnic and religious identities. It is a breeding ground for extremism for exploiting ethnic or religion issues for power and selfish economic motifs of politicians in the name of the tagged ethnic or religious group. Ethiopian constitution allows for parties to organize with ethnic tags, but does not allow religion tags. https://www.proposal-for-a-new-administrative-restructuring-of-Ethiopia.pdf) ስናጠቃልለው፣ በሃገራችን ኃብት ፣ንብረት፣ ንግድ፣ ኢንዱስትሪ፣ ግብርናና የአገልግሎት ዘርፍ በግል ባለሃብቱ መያዝ አለባቸው፡፡ የመንገስታዊው ዘርፍ በማዕድን ዘርፍ፣ በሃድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጨት፣ በአየር መንገድ፣ በጠፍር ቴክኖሎጅ፣ በመድሃኒት ቅመማ፣ ወዘተ ዘርፎች የኢኮኖሚ ዘርፍ መሳተፍ አለበት፡፡ የግልና መንግሥታዊ ዘርፍ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በመርከብ ትራንስፖርት፣ በባቡር አገልግሎት፣ በመብራት ኃይል ሥርጭት፣ ሆስፒታል፣ ሆቴል ወዘተ በጋራ መስራት ይችላሉ፡፡

{5} የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ገንዘብ የብር ህትመት ሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ፤ Sudan Currency Printing Press (SCPP) መሆኑ ያሳስባል፣ የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ገንዘብ የብር ህትመት ዕቅድ በማውጣት የብር ማተሚያ ፋብሪካ በሣይንሳዊ መንገድ፣ የወንጀል ማጭበርበር ሥራዎች እንዳይከሰት ሚስጢራዊ የህትመት ዘይቤንና የህዝብና የሃገር ደህንነትና ህልውና የሚያረጋግጥ ማተሚያ ፋብሪካ ለመገንባት በኢትዩጵያ ሄራልድ ዲሴንበር 2/2014 እኤአ በወጣው ጋዜጣ ላይ ዓለም ዓቀፍ አማካሪ ድርጅቶች ጥናት እንዲያቀርቡ የገንዘብ ማተሚያ  ፍብሪካን በሚመለከት በጨረታ ጋብዞ ነበር፡፡ የብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ማተሚያ ፋብሪካውን ለማቆቆም ዋነኛ አላማዎቹ ውስጥ በባህር ማዶ ሃገር ገንዘብ ለማሳተም የሚወጣዉን የውጪ ምንዛሪ ለመቆጠብ፣ የብር ህትመትን በአንድ መዕከል ሥር ለማድረግና ለመቆጣጠር እንዲሁም ከሁሉም በላይ ለህዝብና ለለሃገር ብሄራዊ ደህንነት፣ ለሃገር ሉዓላዊነት፣ብሎም ከበዓድ ሃገር ይልቅ፣ በራስ የመተማመን ዋስትና ለማዳበር የሚሉት ዓላማዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የገንዘብ ማተሚያ ፋብሪካና ግንባታ ትልቅ የኢንቨስትመንት ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን ለዚህ ሥራ ዘመናዊ ትምህርትና ክህሎት ያለው ፣የተማረ የሰው ኃይል ማሠልጠን ደግሞ ሌላው ተግዳሮቶች ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ ማለትም የኢንቨስትመንት ወጪና በዘርፉ የሠለጠነ የሰው ኃይል በሃገር ውስጥ አለመኖር የተነሳ፣ሃገራችን በባህር ማዶ አገራቶች ገንዘብ ለማሳተም ተገዳለች፡፡

{6} የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን 10 ቢሊዮን ብር በአንደኛው ሩብ ዓመት መሰብስብ አልቻለም፡፡ የ2011 ዓ/ም መጀመሪያው ሩብ አመት ሪፖርት፣  በ2010ዓ/ም በጀት አመት የፀደቀው 346.9 ቢሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 241.94 ቢሊዮን ብር ገቢ ከታክስና ሎሎች ገቢዎች በመሰብስብ ለመሸፈን የታቀደ ነበር፡፡  በአጠቃላይ ከአገር ውስጥ ገቢ 137.1  ከጉምሩክና ተያያዥ አገልግሎቶች ከ104.84 በአጠቃላይ 241.94 ቢሊዮን ብር የታክስና ሌሎች ገቢዋች  ገቢ መሰብስብ ዕቅድ ተይዞል፡፡ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን  ከአገር ውስጥ ገቢ በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲሰበሰብ የታቀደው ገቢ 28.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን አፈጻጸሙ 25.62 ቢሊዮን ብር በመሰብስብ በእቅድና በክንውኑ መካከል የ3.2 ቢሊዮን ብር ልዮነት ታይቶል፡፡ እንዲሁም ከጉምሩክና ተያያዥ አገልግሎቶች ከ6.7 ቢሊዮን ብር በላይ  መሰብሰብ አልተቻለም፡፡  በአጠቃላይ ከአገር ውስጥ ገቢ (3.2) ከጉምሩክና ተያያዥ አገልግሎቶች ከ6.7 ከታቀደው የታክስ ገቢ ውስጥ 10 ቢሊዮን ብር መሰብስብ አልተቻለም፡፡

{7} የ40/60 የመኖሪያ ቤት ፕሮግራም 37000 (ሠላሳ ሰባት ሽህ) ከተመዝጋቢዎች ተስፋ በመቁረጥ ውላቸውን አቆርጠዋል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2005 ዓ/ም ይፋ ባደረገው አራት የመኖሪያ ቤት ፕሮግራሞች የ10/90 እና 20/80  የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ አንድ ሚሊየን ነዋሪዎች ተመዝግበው ባንክ እየከፈሉ 7 አመታት አስቆጥረዋል፡፡ በ1996 ዓ/ም በተጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ግንባታ እስከ 2010ዓ/ም ድረስ ለተጠቃሚዎች የተላለፉ 175 ሽህ ቤቶች ብቻ ናቸው፡፡ የ40/60 ቤቶች ጨምሮ ከ132 ሽህ በላይ ቤቶች በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡ የ40/60 የመኖሪያ ቤት ፕሮግራም 164000 (መቶ ስልሳ አራት ሽህ ሰዎች ተመዝግበው 37000 (ሠላሳ ሰባት ሽህ) ከተመዝጋቢዎቹ 23 በመቶ፣ ዜጎች ተስፋ በመቁረጥ ውላቸውን አቆርጠዋል፣ ተጠያቂዎቹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሦስትና አራት አመት ሠርተው እናስረክባለን ብለው የህዝብ ገንዘብ ሰብስበው በተግባር ቤቶቹን ሠርተው ባለማስረከባቸው ሊጠየቁ ይገባል እንላለን፡፡ በሃገሪቱ የህዝብ የገንዘብ ቁጠባ ባህልን ያጠፋት ሁለቱ ድርጅቶች ለህግ መቅረብ ይኖርባቸዋል፣ ቤት ሰሪው ህብረተሰብም ለ7 ዓመታት በቤት ኪራይ እተሰቃየ ለተጨማሪ የቤት መሥሪያ ወጪ የዋጋ ግሽበት ተጠያቂ በመሆናቸው ህብረተሰቡ ተደራጅቶ ለፍርድ ማቅረብ ይኖርበታል ባንኮች በየአመቱ 14 ቢሊዮን ብር አተረፍን እያሉ የሚተርኩት የደሃውን ህብረተሰብ ተቀማጭ ገንዘብ እያበደሩ ባገኙት ትርፍ መሆኑ ይታወቃል ስለዚህ በህግ ሊጠየቁ ይገባል፡፡

{8} የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ፣ የውጭ ምንዛሪ፣ የኢምፖርት ኤክስፖርት በሞኖፖል የተያዘው በፓርቲ የንግድ ድርጅቶችና በቤተስብ በተደራጁ የንግድ ተቆማት መሆኑን የፌዴራል እምባ ጠባቂ ተቆም ያደረገውን ጥናት ይፋ አውጥቶል፡፡  በጥናቱም መሠረት ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የምትልከውንም ሆነ ወደ ሀገር ውስጥ የምታስገባውን (የውጭ ገቢ ንግድና የገቢ ንግድ ገቢ) በሞኖፖል የተያዘው በቤተሰብ በተደራጁ 5 ወይም 6 በሚሆኑ የንግድ ተቆማት አማካኝ መሆኑ ተረጋግጦል፡፡‹‹ ያ ማለት ከውጭ በሃምሳ ብር ያመጡትን ዕቃ ስድስት መቶ ብር ጣል አድርገውት በ650 ብር ይሸጡታል፡፡ ተወዳዳሪ የለም ቢኖርም ወይ ያስመጭው ልጅ ነው ወይ የልጁ ባል ነው፡፡ሰለዚህ ምርጫ የለህም፡፡ ድክ ድክ የሚል አዲስ ሚሊየነር ከነዚህ ሰዎች ጋር መወዳደር አይቻልም፡፡ ሁለትና ሦስት ኮንቴይነር ዘይት አምጥተህ መክከብ ሙሉ አምጥቶ የገበያውን ዋጋ እንደፈለገው ከሚወስን ቢሊየነር ጋር መወዳደር አይታሰብምና ነጋዴው ከውጭ ኢምፖርት ከማድረግ ይልቅ ከነሱ መግዛቱን ይመርጣል፡፡ እነዚህ ቢሊየነሮች ከጥቂት አመታት በፊት በብዙ ሚሊየን ቶን የሚቆጠር ዘይትና ደብተር አምጥተው ሀገር በሚያክል መጋዝናቸው ውስጥ ካስገቡት በኃላ ቆልፈው እጥረት እስኪከሰት መጠበቅ ጀመሩ፤ ስለጉዳዩ መረጃ የነበራቸው የያኔው ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ በፓርላማ ዘይትና ደብተር በመጋዘን ቆልፈው አርቲፊሻል እጥረት እንዲከሰት የሚያደርጉ ባለሃብቶች ላይ መንግሥት እርምጃ ለመውስድ እንደሚገደድ በገለፁ ማግስት ገበያው  በዘይትና ደብተር ተጥለቀለቀ፡፡ መንግሥት የዜጎቹን መተማመኛ ለማግኘት አሁንም በነዚህ ባለሃብቶች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ካልወሰደና የኢምፖርት ኤክስፖርት ሴክተሩን ከተደራጁ የቤተሰብ ዘራፊዎች እጅ መንጭቆ በማውጣት የትርፍ ህዳጉን ካልወሰነ የፌዴራል እንባ ጠባቂ እንዳጠናው የመቶ ብሩን እቃ አንድ ሽህ ብር ስንገዛ መኖራችን ነው›› (ዋሲሁን ተስፋዬ  ምንጭ፡መረጃ ዶት ኮም) በተመሳሳይ የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ፣ የውጭ ምንዛሪ ክፍያ እንዲቀበሉ የተፈቀደላቸው የንግድ ድርጅቶች በሥራ ላይ ካለው ዝርዝር በተጨማሪ በኤርፖርት ውስጥ የሚሰጥ የቴሌኮም አገልግሎት፣ የአየር መንገድ ኤርፖርት ውስጥ ያሉ የንግድ ዘርፎች በአንድ ዘር በአድሎ የተሰጡ ሱቆች፣ ለውጪ ቱሪስቶች የችርተርድ አገልግሎት የሚሠጡ አየር መንገዶች (ጎሽ አየር መንገድ የዳዊት ገብረእግዚአብሄር ንብረት)፣ የውጭ ዜጎችን የሚስተናግዱ የእንግዳ ማረፍያዎች (የነማን ሃብት የሆነ)፣ ልዩ ክሊኒኮችና (የማን ንብረት)፣ ሆስፒታሎች (የማን ድርጅት) እንዲጨምር የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ውሳኔ አስተላልፎል፡፡ በሃገሪቱ 5000 ኢንፖርት ከባህር ማዶ ሃገራት ምርትና ሸቀጥ የሚያስገቡ ድርጅቶች የህወሓት የፖለቲካ የንግድ ድርጅቶች የውጭ ምንዛሪ ተጠቃሚ የንግድ ድርጅቶች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ዲያስፖራው የውጭ ምንዛሪ በምን ዘርፍ ላይ እንደሚውል መረጃ ከሌላቸው ገንዘባቸው ለወያኔ ገቢ ይሆናል፡፡  ሆኖም የሃገሪቱ ገበሬ የቡና፣ ሰሊጥ፣ ጫት፣ ወዘተ 3 ቢሊዮን ዶላር አመንጪ ሆነው መድሓኒት፣ ላንባ፣ ዘይት፣ ስኮር፣ ስንዴ ዱቄት ማጣቱን ኮሚቴው የተገነዘበ አይመስልም፡፡ ዲያስፖራው 4 ቢሊዮን ዶላር እያመነጨ ቤት ለመስሪያ የሚሆን ማበረታቻ ሊያገኝ አለመቻሉ ያሳዝናል፡፡

{9}  የቻይና መንግሥት የብድር አከፋፈል ሥምምነት፣ የኮሜርሻል ብድሮችን ወደ ኮንሴሽናል ብድር እንዲቀየሩ ስምምነት ተደርሶል፣ ከ10 እስከ 30 አመታት የብድር እፎያታ ጊዜ ውስጥ የባቡር ፕሮጀክት ብድርን እንዲከፈል ስምምነት ተደርሶል፣ በዚህ ተጠቃሚዋ ቻይና ትሆናለች፡፡ የኢትዮጵያ ብድር 2000እኤአ 12.1 ቢሊዩን ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን 17.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለተለያዮ ፕሮጀክቶች መስሪያ አበድረዋል፡፡ ከዚሁ ውስጥ ዓለም አቀፋዊ የመሠረተልማት ግንባታ መንገድ፣ ባቡር፣ ወደብ የአንድ ሃር መንገድ የተሰኘው የቻይና መንግሥት 126 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት አውሮፓን ኤሽያንና አፍሪካን ለማገናኘት እየተገበረች ይገኛል፡፡ ቻይና መንግሥት በብድር ከአዲስ አበባ ጂቡቲ ወደብ የገነባው የኤሌትሪክ ባቡር ዘለቄታዊ አትራፊነቱ ደካማ በመሆኑ ከወልዲያ ወደ መቐለ ለተጀመረው የባቡር መስመር ግንባታ ብድር አልለቀቁም ዋናውም ምክንያት የአዋጭ ጥናትና ዘለቄታዊ አትራፊነት የፒኪንግ ዩኒቨርሲተው ፕሮፌሰር ታንግ ጆያንግ ብለዋል፡፡ Its debt burden at 59% of GDP, debt distressed Ethiopia learns crucial lesson: all the same in Chinese the phrase is ‘ there is no free lunch’ The Ethiopian Observatory (TEO)… “the intensifying repayment risks from the Ethiopian government’s debt reaching 59 percent of GDP is worrying investors,” China’s mission to Africa Union…. “The sustainability of the projects is weak…[ e.g. the] Chinese-funded light railway around the capital Addis Ababa and the Ethiopia- Djibouti rail project ”… “ExIm has become more risk-averse for new projects” Researcher at China Africa Research Initiative at SAIS. ከአዲስ አበባ ጂቡቲ ዘመናዊ የኤሌትሪክ ባቡር፣ በቻይና የሬል ዌይ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽንና ቻይና ሲቨል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን 3.4 (በሦስት ቢሊዩን አራት መቶ ሚሊዩን) ዶላር ብድር እየተገነባ ያለው 758 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው፣ የሰውና ዕቃ ማጎጎዣ የኤሌትሪክ ባቡር አዲስአበባ ከተማን ከጅቡቲ ጋር ያገናኛል፡፡የቻይና መንግሥት ብድር ባቡሩ ነዳጅ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ በማመላለስ እዳውን ለመክፈል በተደረገ ጥናት ዋና ሥራ ተቆራጩ በቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጁ ዩ ዋን ሊ ባቡሮቹ፤ የነዳጅ ፉርጎዎቹና የሲጊናል ሲስተሞች በቻይና ደረጃ መፈብረካቸውን አስታውቆ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እዳውን ለመክፈል ባደረገው ጥናት መሠረት ባቡሩ ነዳጅና ሌሎች ምርቶችን በማመላለስ በተለይም ነዳጅ ከጅቡቲ ወደ መሃል አገር በባቡር ለማመላለስ አንድ መቶ ያህል የነዳጅ ማመላለሻ ፉርጎዎች አዘጋጅቶል፡፡ የአዲስ አበባ ጂቡቲ የባቡር ፕሮጀክትና ለተበደረው 2.5 ቢሊዮን ዶላር የወለድና የግዴታ ክፍያ መክፈል የጀመረ ሲሆን ፕሮጀክቱ ግን ወደ ሥራ አለመግባቱ ይታወቃል፡፡ በሃምሌ ወር 2008 ዓ/ም 35.47 ሚሊዮን ዶላር (784 ሚሊዮን ብር) መክፈሉ ታውቆል፡፡ በ2009 ዓ/ም ጥር ወር 45 ሚሊዮን ዶላር (1.06 ቢሊዮን ብር) ለመክፈል አልቻለም፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ የኮሜርሻል ብድሮቹ ወደ ኮንሴሽናል ብድርነት እንዲቀየሩና ከ10 እስከ 30 አመታት ውስጥ የባቡር ፕሮጀክት ብድርን እንዲከፈል ተደራድረው መጥተዋል በዚህ ተጠቃሚዋ ቻይና ትሆናለች፡፡

ለማጠቃለል የኢትዩጵያ መንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሠረቱ በሦስቱ የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም በግብርና፣በኢንዱስትሪና የአገልግሎት ተስማሚ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመተግበር ለህዝብ ብልፅግናና ለኢኮኖሚ እድገት ማምጣት ይቻላል፡፡ የኢኮኖሚ ፖሊሲው ስርዓት በግብርና ታክስ፣  በመንግሥት በጀት፣ በገንዘብ አቅርቦት፣ የወለድ መጠን፣ የጉልበት ገበያ፣ ብሄራዊ ኃብትና  ሌሎች ኢኮኖሚ ዘርፎች በማበልፀግ እንዲሁም  የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ ከፍተኛውን ሚና እንዲጫወት በማድረግ፣ የመንግስት ጣልቃ ገብነት በተወሰኑ የኢኮኖሚ ዘርፍ በተለይም  በማዕድን ዘርፍ፣ በኢነርጂ ኃይል ማመንጨት፣ አየርመንገድ ወዘተ ውስጥ ብቻ እንዲወሰን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ የፓርቲ የንግድ ካንፓኒዎች የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ እንዳይሰራ በሩን ዘግተውበታል፡፡ የሃገሪቱ መንግሥት  የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ ዘርፈ ብዙ ፈርጆች በፊሲካል ፖሊሲና ሞኒተሪ ፖሊሲ መናበብ መቻል ይገባቸዋል እንላለን፡፡ የሃገሪቱ ፊሲካል ፖሊሲ፤ (Fiscal Policy) የግብርና ታክስ እንዲሁም የመንግሥትን ወጪ ሥርዓትን አፈፃፀም ፖሊሲን ያሳያል፡፡ የመንግሥትን ገቢና ወጪና የበጀት ጉድለትና ትርፍ ያሰላል፡፡ የመንግስትና የታክስና የግብር ገቢ አሰባሰብ ሥርዓትና ፖሊሲን እንዲሁም የመንግሥታዊ ዘርፍ ወጪን ይቆጣጠራል፡፡  የመንግሥትና የብሄራዊ ባንክ ፊሲካል ፖሊሲ፤ የግብርና ታክስ ስርዓት ፍትሃዊ ባለመሆኑ ምክንያት በሃገሪቱ የግብርና ታክስ በ2011 ዓ/ም የመጀመሪያ ሩብ አመት በ 10/ አስር ቢሊዮን ብር መቀነሱ ቀይ መብራት መሆኑን መገንዘብና ማሻሻል አስፈላጊ ነው፡፡ የሃገሪቱ ሞኒተሪ ፖሊሲ፤ (Monetary Policy) የመንግሥትና ብሄራዊ ባንክ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የገንዘብ ዝውውር፣ ገንዘብ ፍላጎትና አቅርቦት በመቆጣጠር የዋጋ ግሽበት መከላከልና የወለድ መጠን በመወሰን የገንዘብ ሥርዓት የሚቆጣጠርበት ሲሆን ከዓለም ዓቀፍ ኢንስቲቲውሽን ማለትም ከዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ ከዓለም ባንክ እንዲሁም የሃገራቱን የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የማህበረሰብ ልማት ፖሊሲዎች ጋር አዛምዶ መስራት ያካትታል፡፡ ሞኒተሪ ፖሊሲ ከሚያካትታቸው ውስጥ፤ የገቢ ፖሊስ፣ የሸቀጣ ሸቀጦችና ምርት የዋጋ ቁጥጥርና የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችትን ያካትታል፡፡ ዘለቄታዊ የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ እንዲኖር የውጭ ንግድ ገቢን መጨመር፣ የዲያስፖራ የሃዋላ ገቢና የዲያስፖራ የቤት ሥራ ገንዘብ በአግባቡ መሰብሰብ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡

 

የወያኔን የህዝብ ግድያ በተባበረ ክንድ እናስቁም!!!

የህግ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ ይከበር!!!

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.