ለመንቃት አምስት በመቶ ዕድል አላት የተባለችው ታዳጊ የእናቷን የፒያኖ ጨዋታ ሰምታ ለመንቃት በቃች (በአብርሃምፈቀደ)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2011 (ኤፍቢሲ) የ14 ዓመቷ ብሪታንያዊት ሚራንዳ ሜልድረም ባለፈው ዓመት ነበር የደም መፍሰስ ወይንም ሄሞሮይጅ አጋጥሟት ወላጆቿ አፋፍሰው ሐኪም ቤት የወሰዷት፡፡

በሖስፒታል በነበራት ህክምናም ውስብስብ ቀዶህክምና ከተደረገላት በኋላ ከሞት ለመትረፍ በቅታለች፡፡

ሆኖም በህመሙ ምክንያት ሰውነቷን ማንቀሳቀስ እንዲሁም ዙሪያ ገባዋንም ማወቅ ተስኗት ቆይቷል፡፡

በመጨረሻም ሐኪሞቹ የሚራንዳ የመንቃት ተስፋ አምስት በመቶ ብቻ መሆኑን ለወላጆቿ ገለጹ፡፡

የ54 ዓመቷ ወላጅ እናቷ ስቴላ ለ18 ወራት አካባቢ ስራዋን በመተው በሖስፒታል ከልጇ ጋር በማሳለፍ ላይ ትገኛለች፡፡

የልጇ የመንቃት ተስፋ አምስት በመቶ ብቻ መሆኑ የተነገራት እናትም ከአልጋዋ አጠገብ በቋሚነት ፒያኖ መጫወት ጀመረች፡፡

በአሁኑ ወቅት ታዳጊዋ እንዴት መራመድ እና ማውራት እንዳለበት ቀስ በቀስ እየተለማመደች መሆኑተነግሯል፡፡

ታዳጊዋ ብቸኛው ከህመሜ የማገገሜ ሚስጢር ሙዚቃ ነው ያለች ሲሆን፥ በተጨማሪም ጓደኞችዋ ለመዳኗ አስተዋጽዖ ማበርከታቸውን ገልጻለች፡፡

ምናልባትም ከ18 ወራት የሖስፒታል ቆይታ በኋላ በቀጣዩ ወር ወደ ትምህርት ቤት ትመለሳለች ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ሜይል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.