ሸዋን ያላሳተፈ ፖለቲካ – መሐመድ አሊ

(አቶ መሐመድ አሊ የቀድሞ ቅንጅት ከፍተኛ አመራር የነብሩ ሲሆን፣ ቅንጅት ተክቶ በወ/ት ብርቷን ሚድቀሳ የሚመራው የአንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሆነው የሰሩ ናቸው። አቶ መሐመድ የሕግ ባለሞያና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚጦምሩ ጦማሪ ናቸው)

ሸዋን ያላሳተፈ ፖለቲካ sense አይሰጥም። “የኢትዮጵያን ፖለቲካ እንዳሻው ሲዘውር ነበር” ተብሎ የሚታማውና በአደባባይም የሚከሰሰው ሸዋ ያጠፋቸውና የሚወቀስባቸው ነገሮች መኖራቸው እሙን ነው። በሌላ በኩል ግን ያገጠጠውን ሐቅ መሸፈን አይቻልም። ወደድንም ጠላንም ሸዋ አገር “ሠርቶ” ሰጥቶናል። በሌላ አነጋገር ሸዋ በዘመናዊ ሀገረ- መንግሥት ምሥረታ (nation state building) ሂደት ውስጥ የማይተካ ሚና (indispensable role) እንደነበረው መካድ አይቻልም። ከዚህ አንፃር የሸዋን ታሪካዊ ውለታ መርሳትና ለዚህም የሚገባውን ዋጋ (due credit) አለመስጠት ንፉግነት ነው። በግሌ በፖለቲካው ውስጥ ሸዋን ጎላ ብሎ ካላየሁት የሆነ ነገር እንደጎደለ ይሰማኛል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ለጥፌው የነበረውን ጽሁፍ እንደገና ማጋራት ወደድኩ።

* * *

የሸዋ ፖለቲካ፣

ሸዋ በተለይ ከ19ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በተጨባጭ ሲዘውር እንደነበር አይካድም፡፡ ሸዋ “የሀገር እምብርት” ነው ማለትም ይቻላል፡፡ የሀገር እምብርት ነው ሲባል በመልከዓ-ምድራዊ አቀማመጡ ለሁሉም አማካይ ርቀት ላይ በመገኘቱ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም ሸዋ የአንድነት ማዕከል ሆኖ ሌሎችን ማሰባሰብ የቻለበት አንዳች መግነጢሳዊ ኃይል አለው፡፡ ሸዋ ዛሬም/ወደፊትም ቢሆን የስበት ማዕከል ነው።

ሸዋን ጉንፋን ሲይዘው ሁሉም በያለበት ያነጥሳል። ሸዋ በጠና ከታመመ ሁሉም ሊንገዳገድ ይችላል። ሸዋ የሀገር ራስ ነዋ! ያለሸዋ ሀገር ሊቆም አይችልም። ምስጢሩ ያለው እዚህ ጋ ነው። ይህ ነው “የሸዋ ፖለቲካ” የሚባለው፡፡ አንዳንዶች የሸዋ ፖለቲካ ሳይገባቸውና ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል። እንዳውም የሸዋን ጭንቅላት “በቴስታ” ነቅንቀው አገር ሊያፈርሱ ነበር። ራሱን ከመታኸው አገር እንዴት ይቆማል?! ይህን ልታደርግ የምትችለው የሸዋ ፖለቲካ ካልገባህ ብቻ ነው።

በርግጥ የሸዋ ፖለቲካ “በሴራ የተቃኘ” መሆኑን የሚያሳይ ትንተና የሚያቀርቡ ወገኖች ይኖራሉ፡፡ ቢሆንም ግን ሸዋ “ሀገርን ስለመበተን” አያሴርም፡፡ በአንፃራዊነት ሸዋ የሚያሴረው ለበጎ ነው ማለት ይቻላል። ሸዋ የኢትዮጵያን ግዛት ለማስፋፋትና አንድነቷን ለማጠናከር ሲባዝን የኖረ ባተሌ ማህበረሰብ ነው፡፡ በሸዋ ላይ የተለያዩ ክሶች የሚቀርቡ ቢሆንም፣ ሸዋ በታሪክ አጋጣሚ ያገኘውን የበላይነት በመጠቀም በተለይ ራሱን ለማበልፀግ አልሞከረም፡፡ ሸዋ ሀገር ወዳድ እንጅ ሁሉን ለራሱ የሚያግበሰብስ ስግብግብ አይደለም።

ሸዋ ሲባል ግን አማራውን፣ ኦሮሞውን፣ ጉራጌውንና ሌላውን ነባር የአካባቢው ነዋሪ ብቻ ሳይሆን በተለያዬ መንገድ ወደ ማዕከሉ እየተሳበና በዚያው ኑሮውን እየመሠረተ የሸዋን ሥነ-ልቦና የተላበሰውን ሁሉ የሚያካትት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ በሸዋ አገዛዝ ላይ የሚቀርብ ታሪካዊ ክስ ካለም ሁሉንም የሚመለከት እንጅ በተወሰነ ማህበረሰብ/ብሔር ላይ ብቻ የሚጫን/የሚደፈደፍ አይደለም፡፡ ሲጀመር ሸዋ የህብረብሔራዊነት መገለጫ እንጅ ተነጣይ ማንነት ያለው አይደለም፡፡ ወዳጄ; የሸዋ ሥነ-ልቦናዊ ሥሪትና የሞራል ከፍታ ከዚያ በላይ ነው። አስፈላጊ ከሆነ በዚህ መስመር አጠንክሮ መከራከር ይቻላል፡፡

ሸዋ “የሀገር ዋልታና ምሰሶ!”

6 COMMENTS

 1. አዲስ አበባ ተወልጄ ባድግም ቤተስቦቼ አዲስ አበባን የቆረቁሩትlol ከጁሩ፣ መንዝ፣ መርሃቤት መጥተው ስለሆነ የሸዋን ጉዳይ ላይ ትኩረት እስጣለሁ፡፡ እራሴን በአማራነት ብገልጽም እውነቱን ለመናገር የወልቃየት ጉዳይ ወይም የራያ ጉዳይ በክ/ሃገሩ የተፈጠረ ጉዳይ እና እዛው መፈታታ ያለበት ጉዳይ ነው ብዬ እማምነው እና ወልቃይት እያሉ ለሚያናፉት ግድ አይሰጠኝም፡፡
  በአማራነቴ ትልቅ ኩራት አለኝ ነገር ግ ን ለፓለቲካ በዘር፣ በአማራ ስር መደራጀት እምፈልገው አይደለም እምደግፈውም አይደለም፡፡ በአማራነት መደራጀት በጣም አስፈላጊነት የሚሆነው በየጊዜው አማራ እንደጠላት እየታየ፣ የንጉሥ ሳህለስላሴን አለማወቅ ጭካኔ፣ በቀል ለመውስድ አሁን በእምዬ ሚኒሊክ ሰበብ የሚበላቀጡ ክበቀል በስተቀር አንድነትን የማይፈልጉ ብዙ አሉ፡፡ በአማራ ወገኖቻችን ላይ በቃል ሆነ በአካል ጉዳት ላይ ለሚደረገበት ወንጀል፣ በመጤነት እየተቆጠሩ ለሚፈናቀሉት ወገኖቻችን ለሚደርሰባቸው ጉዳት መደራጀት አስፈላጊም ነው የግድ ነው፡፡ ለእራሴ ትንሽ ድጎማ ላድርግና የሽዋ ህዝብ ለአዲስ አበባም ስለምንቀርብ ሊሆን ይችላል በዛውም የተለያዩ ብሄርን በሰላም አቅፎ መከባበር ስላለ ሊሆንም ይችላል ሸዋዎች የአስተሳሰብ እድገታችን ከሌላው ከፍ ያለ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ጀግና ህዝብም አገሩን አፍቃሪ ቢሆንም ለመሻሻል ፈጣን ህዝብ ነው፡፡ ብላገር ዘመዶቼ አዲስ አበባ ሲመጡ ወዲይውኑ ተምረው ለመሻሻል እና አዲስ አበቤን ለመምሰል ግዜ አይፈጅባቸውም፡፡ ድርቅናም፣ ግትርነት ብዙም አይታይባቸውም፡፡ lol

  እዚህ ላይ ክጽሁፉ ጋር ባይገናኝም ማለት የምፈልገው የወያኔ መንግሥት የፈጠረው ውጅንብር አይን ቀቅሎ የበላ ሌባ፣ ቀማኛ የወልቃይትን የወሎን ጉዳይ ቢያባብሰውም ወሎን ግን ሰው በላው ጭራቅ የደርግ መንግሥት የላይ፣ የታች እያለ በመክፋፈል የራሱን አስተዋጾኦ አለው፡፡ በምዕራብ አገር ያሉትን ወልቃይቶች ለተመለከተ የተከፋፈሉ ናቸው፡፡ በተለይ ከአገራቸው ውጪ የተወለዱትን ስመለከት ያሳዝኑኛል፡፡ የማንነታቸው ጥያቄ በቤተሰብ ተጸእኖም እና ባለው ፓለቲካ የተምታታባቸው ነው፡፡
  ብዙ ግዜ አበሻ መጠጥ ቤት ድብድብ ባይጠፋም ከሁለት ግዜ በላይ ቴዲን ለማየት ሂጄ ድብድብ አጋጥሞኛል እና ሁለቱም ተደባድቢ ወልቃይቶች ወገን እዚህ ተውልደው ያደጉ ናቸው፡፡ አማርኛ አይችሉም የሚያግባባቸው እንግሊዘኛና ትግሪኛ መናገራቸው ነው፡፡ አንዱ ጎንደሬ ሆኖ አንዱ ትግራይ ነኝ ብሎ ነው እና ከሁለቱም ወገን ጠርሙስ ወርዋሪ አጫፋሪዎቻቸው አሉ፡፡ ብቻ ያስደንቃል ሁለቱም ወገን ልክ ነን ብለው ነው የሚነታራኩት ከዛም ለድብድብ ያበቃቸው፡፡
  ብቻ የማንነት ጥያቄ ለመፍረድም ያስቸግራል፡፡
  መንግሥት በሕግ መፍታት ካልቻለ ወይም ምርጫ ህዝቡን ማስመረጥና መወሰን ይሻላል፡፡ ክዚህ በፊት ካልተሞከረ፡፡my 2 cents

 2. Kuni,

  You have only skull, but not mind. Politically you have no existence.

  Just, your hobbies are barking every where like the human dog Girma Kassa and co.

 3. አቶ መሀመድ ዓሊ
  አንተን በደንብ አውቅሀለሁ። ወደድንም ጠላንም ሸዋ አገር “ሠርቶ” ሰጥቶናል። ብለህ ያልኸው ሸዋን ከመውደድ እና ዕውነትን ከመመስከር አኳያ ተነስተህ እንዳልሆነ በደንብ አውቃለሁ። ለምን በዚህ ሰሀት እንዲህ አይነት ነገር አነሳህ? አላማህ ሸዋን ለማሰደብ የሚጠሉትን ሰዎች አስተባብረህ እንዲነሱበት ለማድረግ ነው። የመኢአድ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል እነደነበርክ ይታወቃል» በዚያም ተጥቅመህበታል። ሆኖም ሸዋን ወደህ አታውቅም። መኢአድ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ምስክር ናቸው። በዚህ ዘመን ሸዋ አገር ሰርቶ ሰጥቶናል ብሎ ማለቱ ሌላው ቀርቶ በአማራውም ዘንድ የሚወደድ እንዳልሆነ በደንብ ታውቃለህ። አማራን ለማሰባሰብ የሚጥሩ ሰዎችን ህልም ከንቱ ለማስቀረት የታሰበም ተንኮል ነው። አማራ እንደማንኛውም ብሄር የኢትዮጵያ ባለውለታ ነው ብሎ ሁሉም አማራ ድምጹን በሚያሰማበት ሰአት ሸዋን ነጥለህ አገር ሰርቷል ስትል ለጥቃት ማመቻቸትህ ነበር። የማያውቁህ ሊታልሉልህ ይችላሉ። አባባልህን በበጎ ሊወስዱልህ ይችላሉ። እኔን ግን አታታልለኝም። በደንብ ስለማውቅህ። ከቻልህ በአማራ ስም ስልጣን ጠቅልለው የያዙትን ወሎየወች ከጎንደር ከወሎና ከሸዋ አታጣሉን ብለህ መምከር ነበረብህ። በዚያ እንደቢምቢ በሚሰቀጥጠው ድምጽህ ለምን ጮኸህ አትገስጻቸውም። ያማራ ስራ አስፈጻሚ ሰሜን ወሎ አይደለም እንዴ? ይህም እየሆነ ያለው አሌላውን ለማስኮረፍ ነው። አማራው ተኮራርፎ እንዲበታተን በወያኔ የሚደገፍ ተንኮል ነው። በወሎ እየተገዛ አንድ ነን የሚል አማራ የሚኖር አይሆንም። ታዲያ ለምን ዘመዶችህን አትመክርም። ያማራ ኢንዱስትሪ ማእከል ያለው ኮንቦልቻ ነው። ባቡር የሚያልፈው በወሎ ነው። ስልጣን ሲኖርህ ወዳንተ ትስባለህ። ሸዋን በስልት ለማስጠቃት ማሰብህን አቁም።

 4. የሸዋ ጥያቄ የኩልነት እንጅ የበላይነት አይደለም። ሸዋ መገለሉ ልክ አይደለም። መሀመድ ግን እውነት ለምን እንዲ አልክ። ተንኮልማ አለክ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.