ይድረስ  ለ ክቡር ከንቲባ ታከለ ኡማ – ሸገር መሃል  (አባዊርቱ)

በመጀመሪያ ከፍ ያለ የአድናቆትና የክብር ደብዳቤዬ ይድረስህ። በቀጥታ ወደመጣሁበት ጉዳይ እገባለሁ

በስልጣን ከተሾምክበት ቀንና ወር ጀምሮ ስራዎችህን በደንብ እከታተል ነበር። ሁሌ የሚገርመኝና የሚደንቀኝ የምትሰራው መልካምና ምስጉን ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዳር እስከዳር የተነሱብህን ተቃዋሚ አትላቸው ተቺዎች በጭራሽ ከምረዳው በላይ ሆኖብኝ ቆይቶ ነበር። የቅርቡን ሃርድቶክ ኢንተርቪውን በደንብ ካየሁ በሁዋላ ለምን እንደዚህ አጥብቀው እንደሚተቹህ ግልጽ ሆነልኝ። ይህውም እንዲህ ነው። በዚህ አጋጣሚ ያንን ኢንተርቪው እስቲ እንደገና በዪቱብ በደንብ ተመልከተው ወንድሜ። ምክንያቱን በደንብ ትረዳዋለህ። ይህንን ስል ጠያቂው በደንብ መጠየⷅ የሚገባውን ሁሉ በማድረጉ አደንቀዋለሁ። ምንም እንከንም አላወጣለትም። እስቲ ወደ አንተው ስብና ሳልገመግም ስራዎችህን እንመልከት ከተሰየምክበት ጥቂት ወራት ወዲህ ያረካቸውን ነገሮች በመዳሰስ። ህዝቡ ይህን ሳያውቀው ቀርቶ ሳይሆን እንደው በጥቅሉ ለማስታወሻና ለህሊናም ብዬ እንጂ።

የሸገርን ወጣቶች በከፊልም ቢሆን ስራ እንድይዙ በማድረግ። ለደሃ የሸገር ነዋሪዎች የተዘጉ ቤቶችን እየከፈትክ በማሳደርና በማኖር፡ የከተማዋን ጽዳት በልዩ ትኩረት አይቶ ህዝቡን ማስተባበር፡ እንደመልካሙ መሪያችን ተምሳሌት ሆነህ ታች ወርደህ ዝቅ ብለህ ህዝቡን በማስተናገድ፡ ከስራባልደረባዎችህ ጋር አንድ ላይ በመሆን የአጭርና ረጂም ጊዜ የከተማ እቅድ አውጥቶ ያንን ለመተገበር ሌት ተቀን መስራት፡ የተራቡና የተጠሙትን ተፈናቃዮች በጊዜው ደርሶ አለሁላችሁ ማለት፡ ስንቱን ቆጥሬው ስንቱን እዘልቀዋለሁ። የኢትዮጵያ አምላክ ብቻ ብርታትና ጥንካሬውን ይስጥህ እንጂ አንተስ መልካሙን ለከተማው ህዝብ እያረክ ነው። እናም በዚሁ ቀጥልበት። ከሁሉ በላይ ሰው እያወቀም ይሁን ሳያውቀው ወይም እንዲረዳው ያልፈለገው ነገር ቢኖር የሸገር የየክፍለከተማው የመሬት ይዞታን የመሰለ የተጨማለቀ መስሪያቤቶችን እያጸዳህና ወደፊት እያስገሰገስክ ባለበት ጊዜ አፋቸውን ሞልተው አንተን የሚተቹ ግለሰቦችም ይሁኑ ድርጅቶች ምክንያታቸው ግልጽ ባይሆንም የኔ ጥርጣሬ አዲሳበቤ አይደለህም ከሚል ይመስለኛል። ጠያቂውም ነካክቶ አልፎታል። ያንተ መልስ ግን ትህትና ያዘለ ቢሆንም አስረግጠህ አንተ አዲሳበቤ መሆንህን ፪፭ አመታትም ኑር ፭ አመታት ቁጥሩ ሳይሆን የነዋሪነት ግዴታህንና ብቃትህን እንዲህ በግልጽ እያስመሰከርክ ማለትህአኩርቶኛል:: ተቺዎችህ ግን ምን ሆነህ እንድትቀርብላቸው ግልጽ ባለመሆኑ መላ ለመምታት ያስቸግራል። ግልጹ ነገር ግን የሰራሃቸው ስራዎች ለብዙ አመታት የከንቲባነትን ስልጣን ይዘው ይንደፋደፉ ከነበሩት በሙሉ የመጀመሪያውን ይይዛል በኔ ግምት። እመነኝ ወንድሜ። ወደፊት እንደዚህ አይነት ጥያቄ ሲቀርብልህ ቀጥ ብለህ ደረትህን ነፍተህ በመለማመጥ ሳይሆን በግልጽ በጥቂት ወራት ውስጥ ስራህ የሚመሰክረውን እያሰመርክበት አስረዳ። ለትህትና ገና አልታደልንም። የአቢይን ትህትናና ቅንነት ያየ ባሁን ጊዜ አቢይይን ያንጉዋጥጣል ሰው ብሎ መገመት በከበደ ነበር። እናም ይቺን አጭር ማስታወሻ እንድጽፍልህ ያበቃኝ ምንም ተስፋ ሳትቆርጥና የያዝከውን መስመር ሳትስት ስራህ ላይ ብቻ አተኩር። ዶር አቢይ ከሰሩት ነገር በሙሉ ያንተን ለዛ ቦታ መሾም ከዋነኞቹ አንዱ ነው። በስራ እያስመሰከርክ ነውና። አዲሳበቤ አይደለህም ለሚሉ በሙሉ መልስህ እንዲህ መሆን ነበረበት “ እኔ አዲሳበቤ ካልሆንኩ ማንስ ሊሆን ይችላል በፈለጋችሁት መስፈርት? “ ብለህ ካበቃህ በሁዋላ እንዲህ ብለህ በልብህ ደግሞ ተርትባቸው፡ ” ሰንጋ ፈረሰኞቹ እየጋለቡ ነው ውሾቹ ግን ከሁዋላ ጩሀታቸውን አላቁዋረጡም” :: በዚህ አጋጣሚ የቅርብ ዘመድህ ሊቁ ጸጋዬ ገ/መድህን በህየወት ቢኖር ምነኛ በኮራብህ ነበር። ካለበትም ያይሃልና አደራ በርታ። ተስፋም አትቁረጥ። ሌላው በግድ ሊግቱን የሚሞክሩት ነገር ግልጹ ነገር ባደባባይ እየታየና እየተዳሰሰ “ ለቄሮዎች ቦታ አድለሃል” ነው።  ገና ብዙም ትባላለህ። ስብናህን ስገመግመው ግን ለንዲህ አይነት ከንቱ ትችት የማትበገር መሆንህን ነውና አደራ ተስፋ አትቁረጥ። ስራህ እየመሰከረ ነው። የሸገርን የመሬት አስተዳደር ጉዳጉድ በየክፍለከተማው መደርመስ ስትጀምር ገና ብዙ ቅጥረኛ ተቺዎች ያላኩብሃልና በተጠንቀቅ ጠብቃቸውና ስራህ ላይ ብቻ በርታ። የመሬት አስተዳደር ጉድ በቀላሉ የሚፈታ ስላልሆነ በቀላሉ እንዳትሸነፍ። እስካሁን የሰራሃቸውን ያየ ሲሆን ኒሻን የሚያሰጥህ ነበር። ገና ብዙ አውሬዎች ከየምሽጉ ይላኩብሃልና በስራት መክታቸው። ፈጣሪ አብሮህ ይሁን። ለከተማው ያለህ ምኞትና ትልም እጅግ የሚደነቅ ነው። ከዚህ በላይ አዲሳቤነትና ኢትዮጵያዊነት ምን ሊሆን ይችላል? የሚገርመኝ ባለፈው ስራት የተለየ ካድሬ የሆንክ ይመስል ጥላሸት የሚቀቡህ ነፈዞች ለዛማ ከአቢይና ለማስ በላይ የቅርብ ወዳጆች ነበሩ እንዴ ብለን እንድናስታውሳቸው ግድ ይለናል። ያውም የመረጃ አካል አልነበሩም እንዴ? ፈጣሪ የኢትዮጵያን መከራ በቃ ብሎ ወደህሊናቸው መልሶ እንዲህ የሚያስደምም ለውጥ በማምጣት ተባበሩን እንጂ ወዴት እንደምንሄድ ማን ያውቅ ነበር? ሁሉ ለራሱ ቀረብኝ የሚል እንደ አሸን በፈላበት አገር አንተና የነቲም ለማ የሰላምና ያገር እድገት ጉዞን ለመገንዘብና አፕሪሼት ለማድረግ ሁሉም በእኩል ላይታደል ይችላልና በርታ። ህዝባችን ዛሬ ያወድስና ነገ የሚከዳ ነው ባብዛኛው። ለአጋጉል ተቺዎች ቦታ አትስጥ!! ይህው ነው መልክቴ። በዚች ኦሮሚፋ ግጥም ልለይህ።

ለሚሌ ፋካቴ ጀሪቲ ፋርሲናን

ጋማና ዳባቴ ኦልኬሳ ቡራቅናን

ማቃ ኦሮሞቲን ሁንዳ ጢሬፋዋን

ጀሪቲን ዋልኬሳ  ኢልማን ቢኔንሳዋን!!!!

ሸገር ከንኬ ሚቲ ዮጋ ሲንጄዳኒ

ገዴን ገዴዱማ ዲሲ ሃጢባራኒ።

ጃባዱ ኮርሜቶ ጂሩኬቲ ጪሚ

ሴራን ቡሉ ታና ሲሪቲ ናሂሚ!!

ኦሌ ቡላ ማሌ ዱጋን ሂንዶካቱ

ጋቲራን ጉባናን ቢዪስ ቢያ ሂንታቱ።

ቃማጤን  ባዳቴ ኢጃን ዮጋአርጋኒ

ዋን ጄዳን ዳብናን ኮርማን ሃሞርካኒ??

አቺዱፋን ታኬ ዋራ ሴራን ቡሉ

ማታ ጋዲቃብናን አራብሶን ሲን ዖሉ

ቱፋዱ ናዲሲ ዋራ ጋራፍ ቡሉ።

ጋሩ ናማዲንቃ ሸገር ካንኬሚቲን

ዋራቤሳ ገዲ ኬሱማ ጀሪቲን

ደንደኢ አካ ታዬ ሜ ሃቡልቱ ዱቢን

ጄዴን ሲቲዳማ ኤታማዦር ዊርቱን

አባዊርቱ

2 COMMENTS

 1. Your short poem would have been more beautiful had you used Qube as follows. My message: It is not late nor hard to learn!
  Nagaatti!

  Lammiilee fakkaatte jaratii faarsinaan;
  Gamana dhaabattee ol keessa burraaqnaan;
  Maqaa Oromootiin hundaa xireeffawan?
  Jarattiin walkeessa ilmaan bineensawan!
  Shaggar kan kee miti yoggaa siin jedhan;
  Gadheen gadheedhuma, dhiisi haa xibaaran;
  Jabadhu kormee too? jiruu keetti cimi;
  Seeraan buluu tana sirriitti naa himi;
  Oolee bula malee dhugaan hin dhokatu;
  Gaattiraan gubannaan biyyis biyya hin taatu;
  Qamaaxeen? badhaatee ijaan yoo argani;
  Waan jedhan dhabnaan, kormaan haa morkanii?
  Ati dhufnaan Taakke? warra seeraan bulu;
  Mataa gad-qabannaan arrabsoon hin oolu;
  Tuffadhuu naa dhiisi warra garaaf bulu.
  Garuu nama dinqa Shaggar kan kee mitiin;
  Waraabessaa gadi, keesumaa jarattiin;
  Danda’i akka Taayyee mee haa bultu dubbiin;
  Jedheen sitti dhaama, ኤታማዦር ዊርቱn

 2. አባዊርቱ ለኢንጅነር ታከለ ሁማ ብለህ ባወጣኸዉ ጽሁፍ ያቀረብከዉ አስተያየትህ ምርጥ ከመሆኑም በላይ ከስሜት ወጥቶ በሰከነ ህሊና፣ ከእዉነት እና ከልብ የመነጨ መሆኑን ከመነሻዉ እስከ ፍጻሜዉ ጉራማይሌ የማይታይበት ወጥ መሆኑ ያረጋግጣል፡፡ በግሌ ሙሉ ለሙሉ እስማማበታለሁ፡፡ ሆኖም ኢንጂነር ታከለ ፊት ላይ የታየዉ ትህትናና ልስላሴ ግን ከተናገሯቸዉ ቃላት በላይ ቀናነቱን ያረጋገጡለት መሆን መገንዘብም ጥሩ ነዉ፡፡ ወንበር ላይ ተንፈላሶ፣ ዘና ብሎና ግርማ ሞገስን አድምቆ ቆየራጥ ንግግር መናገር ይቻላል፡፡ በዚህ ስልት ግን የቀድሞዎች 32ቱ ከንቲባዎች ቀና መሪ ሆነዉ በህዝቡ አንዲታሰቡና በፍቅር አንዲዘከሩ አላስቻለቸዉም፡፡ የኢ/ታከለ ቀለል ማለቱ፣ ልስላሴዉና ፈገግታዉ ከወሬዎቹ በላይ የሕዝብ ፍቅርን እያስገኙለት እንደሆነና ከተሜዉ ልብ ዉስጥ ስፍራ እያስገኘለት ስለመሆኑ አልጠራጠርም፤ እኔንም ፊቱ የሚነበበዉ ቀናነት ማርኮኛል፡፡ የፈለከዉን ሰርተህ ቀና ካልሆንክ የሚፈጥረዉን ዘመን የማይሽረዉ ጥላቻ ከድሮዉ ድሮዉ ጠ/ሚ መማር ይሻላል፡፡ ኢ/ታከለ ስብእናዉ ስልት 180º ከአሊ አብዶ ተቃራኒ ሲሆን ፍቅር ለሚያሸንፍበት ዘመን ስለሚመጥንም ነዉ ልቤን የገዛዉ፡፡ ቀና ሰዉ በምንነም ምክንያት መጥፎ ፍሬን ስለማያበቅል የኢ/ታከለ ተግባሩ አያሳስበኝም፤ የላቀ ስራ እንደሚሠራ አልጠራጠርም፡፡ ጠያቂ ጋዜጠኛዉን እርሳዉ መነሻዉ እዉነት ሳይሆን ከኢቲቪ አድጎ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ቃል አቀባይ ኃላፊ የሆነዉ ሰዉዬ ስልጣን ያገኘበትን መንገድ እንደተሞክሮ(የካድሬ ቃል) እየወሰዱ እንደሆነ እናስብ፡፡
  ግራ እየገባኝ ያለዉ ግን አዲስ አበባ የአሜሪካ ህገመንግስት ነዉ እንዴ ያላት? በከተማዉ መወለድ የከንቲባ መስፈርት የሆነዉ? 5፣ 10፣20፣30..አመት በከተማዉ መኖር ከንቲባነትን የሚከለክለዉ የትኛዉ ህግ ነዉ የሚከለክለዉ? የለንደን፣ የፓሪስ፣ የጆሃንስበርግ ከንቲባ የት ነዉ የተወለዱት? ጋዜጠኛስ ይህን ሲጠይቅ መነሻዉ ምንድ ነዉ? ወይስ ምናልናት እሱ እዚህ ስለተወለደ ወንበሩን ከጅሎ ይሆን? ኧረ ከየት ያገኘነዉ ምሳሌና ህግጋት ነዉ ዛሬ ቅን ሰዉ ስናይ ‘አዲስ አበባ በአዲስ አበቤ’ የሚል መዝሙር የመጣዉ? አዲስ አበቤ ማለትስ መወለድ ነዉ ያለዉ ማነዉ? 50 አመት አዲስ አበባ የኖረ የ60 አመት እድሜ ባለጸጋ አዲስ አበቤ አይባልም? 10 አመት የኖረ የ20 አመት ወጣት አዲስ አበቤ አይባልም? 5 አመት አዲስ አበባ የኖረ የ6 አመት ህጻንስ?

  ከኢ/ር ታከለ ይልቅ እያሳሰበኝ ያለዉ ግን ጠ/ሚሩ አብይ ቀሚስ ማብዛታቸዉ እርገጠኛ ነኝ ነገ…ከነገ ወዲያ የአንባገነንነት ዝንባሌ ተደርጎ እንደማይወሰድባአዉ እርግጠና አይደለሁም፡፡ የዛሬ ዉዳሴ መብዛት እንደመልካም ስራ መዉሰድ የለብንም፡፡ 30 አመት ሙሉ ያለተቀናቃኝ ስልጣን ላይ የተቀመጠዉን የሩዋንዳዉ ካጋሜ ምሳሌ አድርጎ ዛሬ ለመጀመሪያ ግዜ እኩል ሴት ያቀፈ ምርጥ ካቢኔ ብሎ ያወደሱት ነገ ሌላ ታሪክ ይዘዉ አይመቱም ብሎ አለመጠራጠር የዋህነት ነዉ፡፡ አባዊርቱ ግድ የለህም ጠቅላዩን ከወደድክ በግዜ አርማቸዉ፡፡ ጠንካራ መሪ መሆን የሚችልቱ እና ራእያቸዉን መፈጸም የሚችሉት በሃሳብ የሚቀናቀኗቸዉን ሆኖም ግን ሌባ ያልሆኑ ጠንካሮችን ሲያቅፉ ነዉ…የአርከበ አይነቱን ማለቴ አይደለም፡፡ ኧረ የቀድሞዎችም ቅርቦች ያዉም ክፍዎችና መሠሪዎች በጠ/ቅዩ ቅርብ ሰዎች ምልጃ በእንሰት ምጣኔ ጠቅላዩ ዘርዝረዉ የሚልኩት ወረቀት ላይ እየታዩ ነዉ፡፡ ሴቶቹም እኮታማኝና በገንዘብ ይደለላሉ ተብሎ ባይጠበቅም ተኩሎቹ በሌላ ደካማ ጎን ሊነድፏባቸዉ ይችላል፤ አንሸወድ፡፡ ስለዚህ ከኢ/ታከለ ዉጤታማ ልስላሴ ይልቅ የጠቅላዩ ሊበጠስ በሚችል የቀሚስ ገመድ እየተገመደ ያለ ወንበራቸዉ ያሳስበኛል!!!!!!!

  ቱርቦ ቱሞ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.