አቤቱታ!! ለክቡር የኢትዮጵያ ህዝብ !! ለክቡር የኢትዮጵያ ፌድራላዊ መንግሥት ጠ/ሚር አብይ አህመድ፡

ጉዳዩ፦ የህ.ወ.ሓ.ት.መስፋፋትና መሬት ነጠቃ!!

ገብረመድህን አርአያ
ገብረመድህን አርአያ

ክቡር የእትዮጵያ ህዝብ ሆይ ፤ ክቡር የእትዮጵያ ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ ፡ የማቀርበው አብዮቱታየ በኢትዩጵያ ህዝብና በርሶው አስተዋይ መሪነት የእልባት መፍትሄ እንደሚያገኝ በመተማመን ነው ።

ክቡራን!! ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ፡በየካቲት ወር 1967 ዓ.ም ደደቢት በረሃ ከመውረዱ ጥቂት ቀደም ብሎ አዲስ አበባ ውስጥ ሆኖ በንድፈ ሃሳብ ያዘጋጀው ማኒፈስቶው ( የትግል ፕሮግራሙ ) ጥር ወር 1967 ዓ.ም. ኤርትራ ሳሕል በረሃ ወርደው የአንድ ወር ወታደራዊ ትምህርታቸው ያጠናቀቁ ቁልፍ አመራረቹ የሚሰጣቸው ትምህርት ጨርሰው የካቲት ወር 1967 ዓ.ም. ደደቢት በረሃ እንደገቡ ፡ተሰባስበው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት በሚል የዛሬው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መሰረቱ ።በዚሁ እንዳሉም ይዘዉት የመጡ ፀረ ኢትይዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ፤ ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ፕሮግራማቸው እጅግ አጠናክረው በመፃፍ አዘጋጅተው ጨረሱ።ይህ የአቋም ፖሊሲ ፕሮግራም፤በወቅቱ የነበሩ አመራሮች የማ.ገ.ብ.ት ወይም የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት የዛሬው ህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራሙ ኢትዮጵያ ዳግም ተመልሳ ሂወት እንዳትዘራ ሃገራዊ አንድነትዋ ፤የህዝብዋ አንድነትና ኢትዮጵያዊነቱ እንዲከስም እንዲጠፋ ተደርጎ የተዘጋጀ ፕሮግራም ፤ከየካቲት ወር 1967 ዓ.ም. እስከ ጥር ወር 1968 ዓ.ም.ጊዜ በመውሰድ የአንድ ዓመት ጥናትና እርምት ፈጀ ፤ተጠናቆ በመዝጋጀት በመጨረሻ በመፅሓፍ መልክ ተሰናድቶ ፤የካቲት ወር 1968 ዓ.ም 1 በትግርኛ 2 በአማርኛ 3 በእንግሊዝኛ ተባዝቶ ተጠርዞ በየአስፈላጊነቱ ተሰራጨ።ይህ የህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም በብዙ ኢትዮጵያዊ እጅ ስለሚገኝ ዝርዝር መረጃው አላነሳውም ፤ ለአብዮቱታየ መነሻ ሁለት ነጥቦች አቀርባለሁ ።

—[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—–

GDE Error: Unable to load requested profile.

 


LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.