አማራ በመሆናችን ነግደን መኖር አልቻልንም- ከወልቃይት ጠገዴ ተፈናቅለው አዲስ አበባ አቤቱታ ለማቅረብ ከመጡት ወጣቶች መካከል

ጌታቸው ሽፈራው

አማራ በመሆናችን ነግደን መኖር አልቻልንም- ከወልቃይት ጠገዴ ተፈናቅለው አዲስ አበባ አቤቱታ ለማቅረብ ከመጡት ወጣቶች መካከል

"ትልቋ ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራት አዲስ አበባም አፈና አለ፣ ፖሊሶቹም ሽብር እየፈጠሩ ነው" ከወልቃይት ጠገዴ ተፈናቅለው አቤቱታቸውን ለማሰማት ወደ አዲስ አበባ ከመጡት መካከል

Posted by Getachew Shiferaw on Tuesday, October 30, 2018

“ትልቋ ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራት አዲስ አበባም አፈና አለ፣ ፖሊሶቹም ሽብር እየፈጠሩ ነው”

ከወልቃይት ጠገዴ ተፈናቅለው አቤቱታቸውን ለማሰማት ወደ አዲስ አበባ ከመጡት መካከል

"አማራ ሆነን በሀገራችን መኖር አልቻልንም። አማራ በመሆናቸው መማር አልቻልንም። አማራ በመሆናችን ነግደን መኖር አልቻልንም።"ከወልቃይት ጠገዴ ተፈናቅለው አዲስ አበባ አቤቱታ ለማቅረብ ከመጡት ወጣቶች መካከል

Posted by Getachew Shiferaw on Wednesday, October 31, 2018

የወልቃይት ሴቶች ስቃይ!

ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉትን ወገኖች ለማየት ወደ አብን ቢሮ ባቀናሁበት ወቅት ወንዶቹን ሳናግር ከተፈናቃዮቹ መካከል አንደኛው “ኧረ እህቶቻችን አሉ። አናግራቸው።” አለኝ። በየቦታው የሚታዩት ወንዶች ናቸው። “የት አሉ?” አልኩት። “ቤት ውስጥ ናቸው። አይወጡም። ከዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ናቸው” ሲል አጫወተኝ። ወደ አንዲት ጠባብ ቤት ወሰደኝ። የዘበኛው ቤት መሰለችኝ። ሁለት ሴቶች ከአንዲት አነስተኛ አልጋ ላይ ቁጭ ብለዋል።

ውጭ የተቀመጡት በሙሉ ወንዶች ስለሆኑ ቤት ውስጥ መቀመጥን መርጠዋል። ስቃይ ደርሶባቸው ከተፈናቀሉት ወንድሞቻቸው ጋር እንኳን አብረው መሆን ያቃታቸው የቤት ልጆች ከወልቃይት አዲስ አበባ ድረስ ያመጣቸው ምን ያህል ስቃይ ቢደርስባቸው እንደሆነ መገመት ቀላል ነው። ቦታው ትህነግ/ህወሓት በቅኝ ግዛት መልክ የተቆጣጠረው ወልቃይት ነው። የትህነግ/ህወሓት ሰዎች በግልፅ “ወልቃይትን የምንፈልገው መሬቱንና ሴቶቹን ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። በየትምህርት ቤቱ ከትግራይ የመጡ መምህራን የወልቃይትን ተማሪዎች ደፍረው፣ በግድ ሲያገቡና ሲያስወልዷቸው ሕግ አይጠይቃቸውም። ሱራፌል የሚባል ከአድዋ የመጣ ፖሊስ ባሏን ቀጥቅጦ ገድሎ የደፈራት ሴት የሟቹንም የገዳዩንም ልጆች ታሳድጋለች። ወልቃይት ከወንዶች በከፋ ለሴቶች የስቃይ ምድር ነች።

ከወልቃይት ጠገዴ ከተፈናቀሉት መካከል ወጣቶች በፎቶው የሚታዩት እህቶችም ይገኙበታል። ከዩኒቨርሲቱ ተመርቀዋል። ሆኖም ግን የስራ ቅጥር ሲወጣ “አማራ ነን ትላላችሁ!” ብለው ሰድበው ይመልሷቸዋል። ስራ ሲወጣ ከወልቃይት አማራዎች ይልቅ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢ መጥተው በትግራይ መንግስት እቅድ ለሰፈሩት ቅድሚያ ይሰጣል። በመሆኑም በተወለዱበት ምድር አማራ በመሆናቸው ምክንያት ከስራ ገበታ የተገለሉ ሲሆን የወልቃይት አማራ በመሆናቸው ድብደባና ዘለፋ ሲደርስባቸው እንደነበር አጫውተውኛል። ሌላውን መከራና ስቃይ ለእለቱ ባይነግሩኝም ከዛች ጠባብ ቤት መውጣት ያልደፈሩ ምስኪኖች ከወልቃይት አዲስ አበባ ምን እንዳስመጣቸው ለመገመት ቀላል ነው።

እነዚህ ሁለት ምስኪን ልጆች ከ180 በላይ ከሚሆኑ ተፈናቃይ ወጣቶች ጋር ባልተመቸ ግቢ ይገኛሉ። እነዚህ ጥቃት ከቀያቸው ያፈናቀላቸው እህቶች ቢያንስ እስኪመለሱ ድረስ የተሻለ መጠለያ ቢፈለግላቸው መልካም ነው።

"በጠዋት ተነስቼ ቤተ ክርስትያን መሄድ አልችልም። የሚገጥመኝ ብዙ ነገር አለ። ማታም የምፈልገው ነገር ቢኖር ወጥቼ መግዛት አልችልም።"ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀለች ወጣት የተናገረችው

Posted by Getachew Shiferaw on Tuesday, October 30, 2018

 

ዶክተር አብይ አህመድ ስለ ሴቶች ብዙ ብለዋል። ስለ እህቶቻችን፣ ስለ እናቶች መልካም መልካሙን ሲናገሩ ሰምተናል። ብዙ አድናቆትም አግንተውበታል። እስኪ የምር ከሆነ የወልቃይትን ሴቶችም በማንነታቸው የሚደርስባቸውን ያዳምጡ! ከወልቃይት አዲስ አበባ ድረስ አቤቱታቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለመንግስታቸው ለማቅረብ መጥተዋል! እስኪ ያዳምጧቸው፣ መፍትሄም ይስጧቸው!

Posted by Getachew Shiferaw on Tuesday, October 30, 2018

 

ሲሳይ አወቀ ራደ ይባላል። ከወልቃይት አዲረመጥ ተፈናቅሎ አቤቱታ ሊያቀርብ አዲስ አበባ ይገኛል። “አማርኛ ለምን ተናገርክ? ለምን ትግርኛ አትናገርም?” ተብሎ ብዙ በደል ደርሶበታል። አማርኛ ለምን ትናገራለህ ተብሎ ከ8ኛ ክፍል ተባርሯል።

ሊስትሮ ሰርቶ ይኖር የነበረው ሲሳይ አወቀ የዶክተር አብይ ፎቶ የታተመበትን ቲሸርት በመልበሱና ሊስትሮው እቃ ላይ የፋሲል ከነማን አርማ በመለጠፉ ተደብድቧል። 45 ቀን ታስሯል። በማንነቱ በሚደርስበት በደል ከወልቃይት ተፈናቅሎ መጥቷል።

ሲሳይ አወቀ ራደ ይባላል። ከወልቃይት አዲረመጥ ተፈናቅሎ አቤቱታ ሊያቀርብ አዲስ አበባ ይገኛል። "አማርኛ ለምን ተናገርክ? ለምን ትግርኛ አትናገርም?" ተብሎ ብዙ በደል ደርሶበታል። አማርኛ ለምን ትናገራለህ ተብሎ ከ8ኛ ክፍል ተባርሯል። ሊስትሮ ሰርቶ ይኖር የነበረው ሲሳይ አወቀ የዶክተር አብይ ፎቶ የታተመበትን ቲሸርት በመልበሱና ሊስትሮው እቃ ላይ የፋሲል ከነማን አርማ በመለጠፉ ተደብድቧል። 45 ቀን ታስሯል። በማንነቱ በሚደርስበት በደል ከወልቃይት ተፈናቅሎ መጥቷል።

Posted by Getachew Shiferaw on Tuesday, October 30, 2018

ከወልቃይት ጠገዴ የተፈናቀሉ ወጣቶች በዚህ መልክ አብን ቢሮ ይገኛሉ። ወጣቶቹ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ፍትህ እናገኛለን ብለው ነበር። ሆኖም የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የአብንን ቢሮ ከብቦ ወጥተው አቤቱታቸውን እንዳያሰሙ አግዷቸዋል። “ከወጡ እንተኩሳለን” እያለ መዛቱ ተገልፆአል።

ለወጣቶቹ ተራ ጀሮ ጠቢና ፖሊስ መላኩ አይደለም የሚገርመው። አንድ ከሰራዊቱ የወጣና በየጋዜጣው “ሪፎርም ያስፈልጋል” ሲል የምናውቀው ጀኔራልም ሁኔታውን ለማየት በቢሮው በኩል ሲያልፍ ተመልከቻለሁ። እንግዲህ የትህነግን ሰላዮች ስምሪት የሚቆጣጠረውና ወደ መቀሌ ሪፖርት የሚያጠናቅረው ይህ ጀኔራል ይሆናል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.