“ኢትዮጵያ ማንም ተነስቶ እንደፈለገው የሚጋግራት የግል ርስት አይደለችም” – ጠ/ሚ አብይ አሕመድ

“ኢትዮጵያ ማንም ተነስቶ እንደፈለገው የሚጋግራት የግል ርስት ሳትሆን ዘመናትን ያስቆጠረች ታላቅ ሕዝብ የመሠረታት አገር ነች” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ፍራንክፈርት-ጀርመን ላይ ለተሰበሰቡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ባደረጉት ንግግር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን ተስፋና እምነት በዚሁ በአውሮፓ አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያ ለእርሣቸው ያላቸውን ድጋፍ ለመግለፅ ባሰናዱት የፍራንክፈርት የኮሜርስ ባንክ አሬና ስታዲየም ፕሮግራም ላይ ባሰሙት ንግግራቸው በድጋሚ አረጋግጠዋል።የኃይማኖት አባቶች በየእምነታቸው ፀልየዋል፤ የባሕል ትርዒት ቀርቧል። ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ብዙ ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ) – ጽዮን ግርማ /VOA

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.