ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

 

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ናቸው ተሿሚዋን ተሰናባቹን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዳኜ መላኩ ተክተው እንዲሰሩ በእጩነት ያቀረቧቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወ/ሮ መዓዛ ባላቸው የዳበረ ልምድ ምክንያት የአገሪቱን የፍትህ ስርዓቱ ወፊት ያራምዱታል በሚል በእጩነት እንዳቀረቧቸው ለምክር ቤቱ ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ይሁንታውን ሰጥቷቸዋል፡፡

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በህግ የዳበረ ልምድ ያላቸው ፣ በተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ከፍተኛ ተቋማት ውስጥ በማገልገል አንቱታን አትረፈዋል፡፡
ከህገ መንግስት አርቃቂ ከሚሽን አባልነት በግላቸው ለሴቶች ከለላ የሚሆን ድርጅት እስከማቋቋምም ደረሰዋል፡፡

በመሆኑም በዛሬው ዕለት የተሰጣቸው የጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዝዳንትነት ሹመት በፍርድ ቤቱ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ያደርጋቸዋል፡፡

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊም ቃለ መሃላ ፈፅመው በህዝብና በመንግስት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡

ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ ከተሾሙ በኋላ የተናገሩት

Posted by Zehabesha on Thursday, November 1, 2018

አቶ ሰለሞን አረዳ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት አቶ ሰለሞን አረዳ ግለ- ታሪክ

የትምህርት ዝግጅት

• በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

• በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሕግ ማስተርስ ዲግሪ ከአምስተርዳም ዩኒቨርሲቲ

• በህዝብ አስተዳደር ማስተርስ ዲግሪ ከሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ

• በሕግ የማስተርስ ዲግሪ ከሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ውጤት የተመረቁ

የስራ ልምድ

• በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለረጅም ጊዜ በዳኝነት ያገለገሉ

• በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዳኝነት እንዲሁም ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉ

• በአሁኑ ወቅት ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር ስመ ጥር ኩባንያዎች የማማከር አገልግሎት የሚሰጡ፣ በመላው አፍሪካ በመንቀሳቀስ በዚሁ ሙያቸው እያገለገሉ ያሉ

• በተጨማሪም ዘሄግ ዓለም አቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት (Permanent Court of Arbitration) በገላጋይ ዳኝነት በመስራት ላይ የሚገኙና ባለፉት 21 ዓመታት በመስኩ የዳበረ ልምድ ያካበቱና ብቁ የትምህርት ዝግጅትና ጥሩ ስነ ምግባር ያላቸው፣ በብዙ ዓለም አቀፍና አገር በቀል ተቋማት የተመሰከረላቸው ናቸው፡፡

EBC

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዙር 4ኛ የስራ ዘመን 4ተኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

Posted by Ethiopian Broadcasting Corporation on Wednesday, October 31, 2018

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.