የአማራ ክልል ምክር ቤት አዳዲስ የካቢኔ አባላትን ሹመት አጸደቀ

ጥቅምት 24 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት አዳዲስ የካቢኔ አባላትን ሹመት አጸደቀ።

ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ ለክልሉ የተለያዩ ቢሮዎች በእጩነት የቀረቡ ሃላፊዎችን ሹመት አጽድቋል።

በዚህም መሰረት

አቶ ላቀ አያሌው – ምክትል ርዕሰ መስተዳድር

አቶ መላኩ አለበል – በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደረጃ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ

ዶክተር ቦሰና ተገኘ – የግብርና ቢሮ ሃላፊ

አቶ ሻምበል ከበደ – የቴክኒክና ሙያ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሃላፊ –

ወይዘሮ ብዙአየሁ ቢያዝን – የገቢዎች ቢሮ ሀላፊ

አቶ ፍርዴ ቸሩ – ጠቅላይ አቃቤ ህግ

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ – የሰላም ግንባታና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ

አቶ ንጉሱ ጥላሁን – በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደረጃ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ

ዶክተር ሙሉነሽ አበበ – የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ

ወይዘሮ አስናቁ ድረስ – የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ

 

በነብዩ ዮሃንስ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.