“የወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም መግለጫ ከህወሓት አሻጥርና ተንኮል የራቀና የፀዳ አይደለም” የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ መግለጫ

ቀን 24/02/ 2011 ዓም

የፌደሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤ በ23/02/ 2011 ዓም የሰጡትን መግለጫ በመቃወም ከወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

1) የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ገለልተኛ ሳይሆኑ የሚያዋቀሩት የፌደራል አጣሪ ቡድን ተቀባይነት የለውም

2) ከነዋሪ ሕዝቡ ከመቶ አምስት ፐርሰንት ፊርማና ስም ዝርዝር ያሉትን ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም ሕገ መንግስቱ ማንኛውም ማሕበረሰብ ከአምስት ሺህ በላይ ስምና ፊርማ ከመሰባሰቡ የማንነት ጥያቄ ማንሳት ይቻላል ስለሚል።

3) የሕዝብ ኮሚቴ የሚባል በአካባቢ ላይ አስተዳደር ፊርማና ማህተም ያለበት ማረጋገጫ ፈቃድ ያለው አሁን ከሕዝቡ ጋር አብሮ የሚኖር ከሆነ ኮሚቴውን ማነጋገር ይቻላል ብለዋል። ወይዘሮዋ ይህን በፍፁም የሌላውና የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ያገለለ ነው።

4) የትግራይ ፀጥታ ሀይል ከወልቃይት ጠገዴ ሳይነሳ ሕዝቡ መጀመርያ ነፃነት ሳይሰጠው ህወሓት ያሳደደው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ወደ ተወለደበት ቦታ ሳይመለስ የሚደረግ የማንነት ማጣራት ተቀባይነት የለውም።

ስለሆነም የወልቃይት ጠገዴ የራያ ማንነት ጥያቄ የሚያጣራ ቡድን ይገባል የሚል የወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም መግለጫ ከህወሓት አሻጥርና ተንኮል የራቀና የፀዳ ስላልሆነ መላ ህዝባችን ገለልተኛ ፌደሬሽን ምክር ቤት ኑሮ ትክክለኛ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን እስከሚዋቀር እንዳትቀበሉ የሚል ጠንካራ ተቃውሞ አለን።

የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.