ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን በጎበኙበት ወቅት ያደረጉት ንግግር

* እኛስ ምን እያደረግን ነው ብለን እንጠይቅ !!!

የተከፋፈለውን ፣ የተበታተነውን እየሰበሰበ ፣ የራቀውን እያቀረበ ፣ የተገፋውን ዝቅ በሎ እየጎበኘና እየዳሰሰ ፣ ጥሩ ተጫዋች በሌለበት የሀገሬ የብሽሽቅ ዘባተሎ ፖለቲካ እያለፈ የማይታክተው ንጉሱ ዶር አብይ ዛሬ ረፋዱ ላይ ሜቅዶንያ ተከስቷል ! ሜቄዶንያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን መረዳጃ ማዕከል ነው ።

ንጉሱ ዶር አብይና ደርባባዋ ባለቤቱ ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እሁድን ለመልካም ምግባር ምሳሌ ሊሆኑን ከሜቅዶንያ አቅመ ደካሞችና የአዕምሮ ህሙማንን መንደር ተገኝተዋል ። አይታክቴው ንጉሱ የእሁድ እረፍቱን የግል ቅንጦት እረፍቱን ትቶ ሜቅዶንያን ሲጎበኝ እኛስ ምን እያደረግን ነው ? ብለን እንጠይቅ !!

ወሳኙ ሰው ፣ ተስፋ የማይቆረጥበት ንጉሱ ዶር አብይ ዛሬ ከምንዱባኑ ጋር ሰንበትን እያሳለፈ ስመለከት ደስታ በውስጤ ናኘ…ንጉሱ ድፍን 8 ወር በአስገራሚ አስደሳች ክስተት በአይበገሬነት የሚጓዝበት አነቃቃቂ የብሩህ ተስፋ ጉዞን አለማድነቅ ግብዝነት ነው ባይ ነኝ ። ተሳሳትኩ ይሆን ?

ለማንኛውም ከጎልማሳው የልብ አዋቂ ንጉስ ስራ እንማር ! ለመልካምና በጎ ምግባር የተጋ ልቦና ይስጠን !

ሰናይ እለተ ሰንበት !

ነቢዩ ሲራክ

#EBC ኢቲቪ አማርኛ ምሽት 2 ሰዓት ዜና በቀጥታ ይከታተሉ…

#EBC ኢቲቪ አማርኛ ምሽት 2 ሰዓት ዜና በቀጥታ ይከታተሉ…

Posted by Ethiopian Broadcasting Corporation on Sunday, November 4, 2018

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.