አንባሰል ንግድ ስራዎች የማን ነው?

ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ሀያ ስምንት ሰራተኞችን አባረረ

በኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ውስጥ ከዩኒቨርስቲ እና ከኮሌጅ ተመርቀው በዝቅተኛ ስራ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ ከ አስራ አምስት በላይ ሴት ወጣቶች እና ወጣት ወንዶች ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከስራ ተባረዋል፡፡ የተባረሩበትም ምክንያት በድርጅቱ ውስጥ እየተቀጣጠለ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ ያሰጋቸው አቶ ሙስጠፋ ጀማል የድርጅቱ ዋና ስራአስኪያጅ እና አቶ አሰፋ ይመር የድርጅቱ የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ስራአስኪያጅ በሰራተኛው እየተነሳ ያለውን የለውጥ ጥያቄ እንዲሁም  የሙስና እና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ወደ ከፍተኛ ደረጃ ከመድረሱ በፊት ለማፈን በመፈለጋቸው ነው፡፡ይህ ተግባርም መንግስት በሁለተኛው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ አካቶ ከያዘው የስራ እድል ፈጠራ እና እና የስራ አጥ ቁጥር መቀነስ ከሚለው መርህ በተፃራሪ እና በማን አለብነኝነት የተፈፀመ ድርጊት ነው፡፡እንዲሁም የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትም ይህን ነገር ፈፅሞ የሚያወግዘው እና በችልታ የማይመለከተው ድርጊት መሆን አለበት፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥም አስተዳደራዊ ውሳኔ በመስጠት መፍትሄ ያበጅለታል ብዩ አምናለሁ፡፡

ይህም የታሰበበት ምክንያት በዋነኝነት የድርጅቱ ሰራተኞች ምንም አይነት ጥያቄ ቢያነሱ የማባረር መብት እና ስልጣን እንዳላቸው እና አርፎ ስራውን እንዲሰራ ለማስፈራራት ሲሆን ወጣቶቹ በድርጅቱ ውስጥ ከቆዩ የደሞዝ እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ እንዳያነሱ እና በሰራተኛው የውስጥ ለውስጥ  የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ይሳተፋሉ ብለው በመስጋታቸው ነው፡፡

ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ከተመሰረተ በርካታ አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የመንግስት የልማት ድርጅት ከነበረበት ወቅት ጀምሮ እስከ ቅርቡ በጥረት ኮርፖሬት መተዳደር እስከጀመረበት ወቀት ድረስ በነ በረከት ስምኦን እና አህመድ አብተው ተዘርግቶ በነበረው የዝርፊያ እና የሙስና ሰንሰለት ያለምንም የመዋቅር ለውጥ እና ሹም ሽር የሀገሪቱን ሀብት ሲያዘርፉ እና ሲዘርፉ የነበሩ የድርጅቱ ስራአስኪያጅ እና የማናጅመንት ቡድን እንዲመራ በቦርድ ሀላፈው እና በጥረት ኮርፖሬት ሀላፊዎች ትእዛዝ በመተላለፉ ነው፡፡

በተከታታይ እንደ አንድ ሀገሩዋን እንደምትወድ ሴት እና ያለፍትህ ከስራዋ የተባረረች ሴት ጉዳዩ የመንግስት አካል እስኪደርስ ድረስ የምታገል መሆኑን እና የተለያዩ የድርጅቱን የውስጥ አሰራር ሚስጥሮች ለመንግስት እና ለህዝብ ይፋ የማደርግ መሆኑን ለማሳወቅ እፈልጋለሁ፡፡ይህንንም መረጃ በሶሻል ሚዲያ በማስተላለፍ እንድትተባበሩኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

ከሰላምታ ጋር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.