በወልቃይት ሴቶች ላይ የሚፈፀም ግፍ! (ጌታቸው ሽፈራው)

በወልቃይት ሴቶች ላይ የሚፈፀም ግፍ! (ጌታቸው ሽፈራው) 1~”ወንዶች ጥርግ ብላችሁ ጥፉ። እኛ የምንፈልገው መሬታችሁን፣ ሚስቶቻችሁን እና ሴት ልጆቻችሁን ነው” የትግራይ ባለስልጣናት ለወልቃይት ተወላጆች

ወልቃይትን የሚፈልጉት መሬትና ሴቶችን እንደሆነ የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በአባላቱ ፊርማ ታህሳስ 7/2008 ዓም ለተለያዩ የመንግስት ተቋማት ያቀረበው አቤቱታ በግልፅ ያሳያል። ከሚቴው በአቤቱታው እንደሚከተለው አቅርቧል።

1ኛ አቶ ካልአዩ አሰፋ የተባለ የወልቃይት ዋና አስተዳዳሪ የሆኑ የአቶ ብርሃኑ ካህሳይ ባለቤት ወይዘሮ ትግስት መለሰን አስገድዶ ወልዶባት፣ ከትዳሯ ተፋትታለች።

2ኛ አቶ ሰለሞን የተባለ የወልቃይት ፖሊስ አዛዥ አቶ አለማው ጉዕይን አስሮ ባለቤቱን ወይዘሮ አዜብ አዛናውን አስገድዶ ወልዶባታል።

3ኛ በትምህርት ቤት ብዙ መምህራን ብዙ የወልቃይት ወጣት ሴቶ ተማሪዎችን አስገድደው ክብረ ንፅህና በመገርሰስ እና በመድፈር በሕግ ቢጠየቁም “ደግ አደረጉ” የሚል መልስ ከሚመለከተው አካል በማግኘታቸው አስገድዶ መድፈርን እየቀጠሉበት ይገኛሉ። ይህ ድርጊት በአንድ ወቅት አቶ ማዕረግ “ወልቃይት የትግራይ ናት፣ እመኑ!” ብሎ በጠየቀበት ወቅት ሕዝብ “አናምንም” ብሎ ቢቃወም “ወንዶች ጥርግ ብላችሁ ጥፉ። እኛ የምንፈልገው መሬታችሁን፣ ሚስቶቻችሁን እና ሴት ልጆቻችሁን ነው” ብሎ ሲናገር አለቃ ፀጋዬ (የቀድሞው የትግራይ ርዕሰ መስተዳደር) ነበሩ። ይህ በአሁኑ ወቅት በተግባር እየተገፀመ ነው። ይህ ተጨባጭ መረጃ ሲሆን በቀጣይ ፍትህ እስክናገኝ የደረሱትን በደሎች ለሕዝብ እናደርሳለን!

(መረጃው የወልቃይት ጠገዴ ኮሚቴ ለተለያዩ ተቋማት ታህሳስ 7/2008 ካስገባው ማመልከቻ የተወሰደ ነው)

 

1 COMMENT

 1. Comment:ነገር ሲያልቅብህ ያረጀ ዶሴ ከመዝገብ ቤት እያራገፍክ ትተርክ ያዝክ? አይ አንተ ልጅ? አንተ ይህን ስትል እኔ ደግሞ እንዳንተ ወደ ልጅነቴ ወርጄ እንዲህ ልጠይቅህ ባንተ ፣በግርማ ካሳና ፣ በአጠቃላይ የአብን አባላት ትርክት አማራ የሰው ውሃ ልክ ነው ብላችሁ እንደመቃዥታችሁ (ሁሌ እንደምለው ያን መከረኛ እና ግን ደግሞ ጀግና እና ጨዋ ሕዝብ የማትወክሉ ቁጫጮች መሆናችሁ ይታወቃል ህዝቡን የውርደት ማቅ ለማልበስ ዘመን የወለዳችሁ እፉኝቶችም ናችሁ ) ሴቶቹ ማንገራገር አልፈጠረባቸውም እንዴ? ተኙ ሲባሉ እሺ ውለዱ እሺ ነው እንዴ?

  ቤቢ ሆይ እንዲህ ያለው ነገር ሚዲያ ላይ አይውልም እንኳንስ ይሄ ….ባንድ ወቅት(ከለውጡ ቀደም ብሎ) ከኦሮሚያ በአንዷ ከተማ ዩኒቨርሲቲ የምትማር አንዲት ጉብል የፊቼ ልጅን የመከላከያ አባላት ሰላም ለማስከበር ቢላኩ ግርግሩን ተጠቅመው ብቻዋን ያገኟትን ያቺን ተማሪ ጠብመንጃ ደግነውባት ምኞታቸውን ቢፈጽሙባት ልጅት አንዱን በደምብ አድርጋ እጁን በመንከስ በሌላኛው ስልክ ወደራሷ ስልክ በመደወል እና ቁጥሩን በማስቀረት ሁለቱንም በህግ ፊት አቁማ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ አስችላለች ፤

  ኢትዮጵያውያን አንስት ብዙ ተጋድሎ ያላቸው ናቸው አንተ የምታወራን ሴቶች እንዲያው ገራገሮች ይሆኑ?ልክ የስፖርት መምህር እንዲህ ሁኑ ዘርጉ እጠፉ ሩጡ ታጠፉ ተዘርጉ ሲላቸው እንደሚታዘዙ ዓይነት? ዳሩ አንገታችሁን ቀብራችሁ የኖራችሁትን እናንተን የሚዲያ አንበሶችን አብነት አርገው ይሆናል እንጂ ሌላ ምን ይባላል?

  የሰላም ወረዳ ነብሮች እናንተ የአህያ ባል ናችሁ ከጅብ የማታስጥሉ ፤ ምላሳችሁ መለኪያ የለው ረዥም … ኮሽ ሲል ግን ፈሪ ለእናቱ ቶሎ ወደየ ማጀት ክትት … ሰላም ሲሆን ጎራው ና ን የምትሸልሉ ፣ ኧረ ጥራኝ ጫካውን የምታዜሙ…

  ሰላም ሲደፈርስ በየጎሬው ውሽቅ ብላችሁ “ለሰውልጆች ፍቅር ለሰው ልጆች ሰላም “ስትሉ እምትውሉ ጀግና በዋለበት እማትውሉ አልቦ ታሪክ (ታሪክ አልባዎች) የመንደር እና የሴተኛ አዳሪ ወሬ እምታራግቡ አጠይማችሁም ፖለቲካ ማድረግ እሚዳዳችሁ ፤

  ሰሞኑን የተዘጋው የራያ አላማጣው መንገድ ከተከፈተ ፀሐይ አትጠልቅም ዓይነት ሽለላ እንዳልሸለላችሁ የተዘጋው መንገድ በመከላከያ ጣልቃ ገብነት እንዲከፈት ሲደረግ ትኩስ ወሬ ቢነጥፍባችሁ የ3ዓመት ዶሴ በመምዘዝ አዋራውን አራግፋችሁ መለጣጠፍ ያዛችሁ ፤

  ለመካሪ ያስቸገረን መከራ ይመክረዋልና ሁሉንም ጊዜ ያሳየናል!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.