ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴዎቹ ቁጥር ወደ 10 ዝቅ እንዲል ወሰነ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የቋሚ ኮሚቴዎቹ ቁጥር ወደ 10 ዝቅ እንዲል ውሳኔ አሳለፈ።

ምክር ቤቱ ይህን የወሰነው ዛሬ ባካሄደው የ5ኛ ዓመት፣ 4ኛ የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባው ነው።

ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም 20 ቋሚና 1 ልዩ ኮሚቴዎች የነበሩት ሲሆን ኮሚቴዎቹ ባላቸው ተዛማጅ ተልዕኮ ተጠጋግተው በ10 እንዲጠቃለሉ ይደረጋል። እያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴ ከ20 እስከ 45 አባላትን ይዟል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቋሚ ኮሚቴዎቹ አማካይነት በአስፈጻሚ አካላት ላይ የክትትልና ቁጥጥር ስራ እንደሚያከናውን ይታወቃል።

ምንጭ፡- ኢዜአ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.