አሳዛኙ ታሪክ በደሴ ከተማ: ሳላይሽ አካባቢ አንዲት የ7 አመት ህጻን ተገድላ ተገኘች

ደሴሚዲያ እንደገለጸው “ህጻኗ ተገላ የተገኘቸው ማክሰኞ ጥቅምት 27/2011 ዓ.ም ሳላይሽ አካባቢ አስከሬንዋ በኬሻ ተቆጥሮ መሆኑን የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
የህጻኟ ወላጅ እናት ወ/ሮ አባባ ሙህየ ሟች ልጇ ከቅዳሜ ጥቅምት 24 አራት ሰዓት ጀምሮ በመጥፋትዋ በፖሊስና በአካቢው ነዋሪዎ ስትፈለግ ብትቆይም በህይወት ሳይሆን ተገላ መገኘትዋን ትናገራለች፡፡
ጎረቤትቿም በድርጊቱ በጣም እንደተቆጡና ወንጀለኛው እንጀራ አባቷን እንደሚጠረጥሩ ተናግዋል፡፤
የደሴ ከተማ አስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ወንደሰን ጸጋዬ ድርጊቱ በጣም አሳዛኝ ነው፤ ፖሊስም ድርጊቱ እንደተሰማ ወዲያውኑ አጣሪ ግብረ ሃይል በማቋቋም ዋና ተጠርጣሪ የተባውን ግለሰብና ሁለት ግብረ አበሮችን መያዙን ገልጸው የምርመራውን ሂደት ወደፊት ይፋ ይደረጋል፤ ህብረተሰቡም ለምርመራ መሳካት እንዲረጋጋ ጠይቀዋል፡፡
በርካታ የአካቢውና የከተማው ነዋሪ አደባባይ በመውጣት ቁጣቸውን ሲገልጹ ውለዋዋል።”
———
አሳዛኙ ታሪክ ይሄው ነው!!

Yasin Mohamed Ali

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.