በሞቃደሾ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሞቃደሾ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል። በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ዛሬ ከሰዓት ከተከሰተ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ቢያስ 10 ሰዎች ይህወት ማለፉን የሀገሪቱን ፓሊስ ጠቅሰው የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።በከተማዋ ታዋቂ በሆነው ሻፊ ሆቴል አካባቢ ሁለት መኪናዎች ላይ የተጠመዱ ከባድ ፍንዳታዎች መከሰታቸው ተነግሯል።

ከዚህም ሌላ እግረኞች እና ተሽከርካሪዎች በተጨናነቁበት የከተማዋ አውራ ጎዳና ላይ 3ኛ ፍንዳታ መከሰቱን ነው ዘገባው የሚያመላክተው። ክፍንዳታው ጋር በተያያዘ ም አካበቢው በጭስ የተሸፈነ እና የተኩድ ድምጽ መሰማቱም ነው የተገለጸው። የአይን እማኞች በከተማዋ ከተከሰተው ፍንዳታ እና ተኩስ ጋር በተያያዘ የማቾች ቁጥር ከ10 በላይ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል። ከማቾቹ መካከልም ንጹሃን ዜጎች እና የጸጥታ ሃይሎች እንደሚገኙበትም ታውቋል።አዶላስ የተባለውን የሬዲዮ ጣቢያ ዋቢ ጠቅሰው የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን አንደዘገቡትም የጥቃቱን ሃለፊነት አልሻበብ ወስዷል ተብሏል።

ምንጭ፦ aljazeera.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.