ረፒ የደረቅ ቁሻሻ ኃይል ማመንጫ 50 ሜጋ ዋት ተፈራርመው፣ 25 ሜጋ ዋቱ አረገ! የወያኔ የትራንስፎርመር ነቀላና ተከላ ዘረፋ! ‹‹የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር››

ኢት-ኢኮኖሚ    /ET

ክፍል አራት ሚሊዮን ዘአማኑኤል

ረፒ  የደረቅ ቁሻሻ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት/ Waste to energy plant project

የወያኔ የኤሌትሪክ ትራንስፎርመር ነቀላና ተከላ፣ የባንክ ገንዘብና ወርቅ ዘረፋ፣ የጭነት መኪኖች ነጠቃ፣ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ዘረፋ እያደገ ሄዶ፣ የመርከቦች ሰረቃ፣ የአይሮፕላኖች ሌብነት ተሸጋገረ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የመከላከያ ሠራዊት ኃብት የሆነውን የጦር አይሮፕላኖች፣ ታንኮች፣ የጦር ግምጃ ቤት የሚገኙ ከባድ መሳሪያዎችና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ህወሓት ካልገዛ  ከትግራይ ክልል አይወጣም በማለት ዘርፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በሃል አይደለም!!!  የትግራይ ህዝብ ሌቦቹን እጃቸውን ጠፍሮ ለህግ አሳልፎ እንዲሰጣቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ይጠይቃል፡፡ የህወሓት የ27 አመታት አገዛዝ አንዱን ዜጋ ልጅ ሌላውን ዜጋ የእንጀራ ልጅ አድርጎ በዘረኝነት ከፋፍሎ በመግዛቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላው፣ጠመደው፣ጣለው፡፡

ረፒ  የደረቅ ቁሻሻ በኢትዮጵያ 50 ሜጋዋት ኃይል ለማመንጨት መሠረቱን በሃገረ-እንግሊዝ ያደረገ ካምብሪጅ ኢንዱስትሪስ  ሊሚትድ በኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ባለቤትነት ጋር በመዋዋል ግንባታው በ18 ወራት ሲጠናቀቅ ለመቶ ሰዎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ነበር፡፡ ኮርፖሬሽኑ ሥራ አስኪያጅ አቶ ምህረት ደበበና የካምብሪጅ ጀነራል ማናጀር ሮበርት ሲብሩክ የ120 ሚሊዮን ዶላር የግንባታ ወጪ የከተማዋን 500 ቶን ደረቅ ቆሻሻ በመጠቀም 50 ሜጋዋት የኤሌትሪክ ኃይል ለማመንጨት የስምምነት ፊርማቸውን በ23 ጀነዋሪ 2013 አኑረው ነበር፡፡ ረፒ  የደረቅ ቁሻሻን ወደ ኤሌትሪክ ኃይል በመቀየር 50 ሜጋ ዋት ኃይል ለማመንጨት 2.3 ቢሊዩን ብር ወጪ በ2005 መገንባት ተጀምሮ በ2011 ዓ/ም ሥራው ተጠናቆል፡፡ ፕሮጀክቱ በአንድ አመት ከስድስት ወራት ይጠናቀቃል ተብሎ በስድስት አመት ተጠናቆል በዚህ ላይ ስምምነቱ 50 ሜጋ ዋት የነበረ ሲሆን በ25 ሜጋዋት የኤሌትሪክ ኃይል በማመንጨት  ተጠናቆል፡፡ በዚህ ደሃ ህብረተስብን ደሙን የሚመጡ የነቀዙ ሹማምንት ከያንዳንዱ ፕሮጀክት የሚዘረፈው የህዝብ ኃብትና ንብረት በህግ ጠያቂ የህዝብ ልጆች ስለሌሉ እናት ሃገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደህየች መሄዱ ግድ ብሎታል፡፡ “The 50 MW waste to energy plant to be built in Ethiopia by UK based Cambridge Industries is to be located in Repe (Koshe) and could be the first of 35, according to a report by Capital Ethiopia. The report said that the facility will be owned by the state power utility company EEPCo and will provide around 100 skilled jobs in the area.„1

ረፒ  የደረቅ ቁሻሻ 25 ሜጋዋት የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት ብቻ እንደሚችል የካምብሪጅ ኢንደስትሪስ ሊሚትድ ካንፓኒ ሲያስታውቅ ደንበኛው የሆነው የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት መኃል አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር፡፡ በምረቃው ሥነ ሥርዓት ፕሬዜዳንት ሙላቱ ተሸመ ተገኝተው ሲመርቁ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ አዜብ አስናቀ  25 ሜጋ ዋት ሳይሆን 50 ሜጋ ዋት በመሆኑ የዛቀን የሰሙ ይመስል ፣ የሠራውን ካንፓኒ እንደሚከሡ ለሚዲያ የኤልፓ ድራማ ሲተውኑ ተስተውለዋል፡፡ ዶክተር ደብረፂዎን ወይዘሮ አዜብን አስናቀን የኤልፓ ሥራ አስኪያጅ አደርገው መሾማቸው ልብ ይበሉ፡፡ የሜቴኩ ክንፈ ዳኘው የመብራት ኃይል የቦርድ አባል ሆነው በዶክተር ደብረፂዎን ሲሾሙ  የተቃወሙት አቶ ምህረት ደበበ የሜቴክ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ ጋር በተያያዘ የጥቅም ግጭት ይፈጠራል ብለው ለማስረዳት በመሞከራቸው ስልጣናቸውን አጥተዋል፡፡ ረፒ  የደረቅ ቁሻሻ ሃምሳው ወደ 25 ሜጋዋት የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫነት መቀየር የወያኔ የሌብነት እጅ እንዳለበት ጊዜ ያወጣዋል እንላለን፡፡ በዚህ ጉዳይ  በአሜሪካ ኢንባሲ ዳኝነት ሁለቱ ውል ተዋዋዬች ሲዳኙ ቆይተዋል፡፡ የረጲ የሌብት ወንጀል ለህዝብ ይፋ መሆን አለበት እንላለን፡፡  የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች የሚያውቁትን ማጋለጥ አለባቸው፡፡

Ethiopia Inaugurates waste to energy Facility Amid Diplomatic Row By Staff Reporter August 19, 2018 – The 25-megawatt (MW) Reppie waste to energy facility project, which Ethiopia claims to be the first of its kind in Africa, was inaugurated on Sunday despite continuing disagreement between the contractor Cambridge Industries Ltd (CIL) and its client Ethiopian Electric Power (EEP). According to the agreement reached by the parties four years ago, the Reppie waste -to- energy project was designed to produce 50 Mega Watt (MW)  of elecrity by Cambridge Industries Ltd from dry waste at Ethiopia’s largest landfill site commonly called “Koshe” in Addis Ababa. After the necessary machines with the capacity of generating 50 (MW) of electricity had been installed, the contractor announced that the facility will have annual production capacity of 185 GWH of electricity which is equivalent to 25 (MW). 2

በኒው ቢዝነስ መረጃ መሠረት ኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት በአዲስ አበባ አካባቢ በ37 ሄክታር መሬት ላይ  በሚገኝ የረፒ የደረቅ ቁሻሻ 25 ሜጋዋት የኤሌትሪክ ኃይል በ95 ሚሊዮን ዶላር ማመንጨቶ ተገልፆ እቅዱ ግን 50 ሜጋ ዋት ለማመንጨት እንደነበር ተገልፆል፡፡ ሃገሪቱ ከታዳሽ የኢነርጂ ኃይል የከተማውን 350 ሽህ ቶን በአመት ደረቅ ቁሻሻ ሃብት ይከማቻል፡፡ ከዚህ ውስጥ በየቀኑ 1400 ቶን ደረቅ ቁሻሻ፣ወደ ቁሻሻ ማስቀመጫ ቻንበር ቆት ውስጥ ተከቶ ቁሻሻው ሲቃጠል በሚፈጠረው ከፍተኛ ሙቀት ከላይ ያለውን የውኃው ታንከር ውስጥ ያለውን ውሃ በማፍላት፣ ውኃው ተፍለቅልቆ  በሙቀት እየተነነ ወደ እንፋሎትነት ተቀይሮ ከአጠገቡ ያለውን የጀነሬተር ተረባይኖችን/ውልብልቢቶቹን  በሽከረከር ጊዜ የኤሌትሪክ ኃይል ይፈጥራል፡፡ የደረቅ ቁሻሻ ወደ ኤሌትሪክ ኃይል የሚቀይረው ቴክኖሎጂ ዘመናዊ ነው፡፡ የጀነሬተሩን ተረባይን/ ውልብልቢት ከፍተኛ የፍጥነት እሽክርክሪት 185 ጊጋዋት ሰዓት የኤሌትሪክ ኃይል በአመት ያመነጫል፡፡ ከዚህም የተገኘው የኤሌትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የኤሌትሪክ ቆት ጋር ተገናኝቶ ተጨማሪ ኤሌትሪክ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ Ethiopia  has started production of 25 Megawatts of energy from waste at one of its first waste to energy convertor plant located in Addis Ababa. Reppie waste -to- energy project, which was planned to generate 50 megawatts initially, is built at the cost of $95 million.In waste -to- energy incineration plants, rubbish is burned in a combustion chamber and the resulting heat is used to boil water until it turns to steam, which drives a turbine generator that produces electricity. The facility is expected to produce 185GWH of electricity annually that will be siphoned to the Ethiopian national grid and will incinerate over 1,400 tons of waste every day. Ethiopia invested $96 million in the plant which is constructed by British firm Cambridge Industries Limited and China National Electrical Engineering Company. It took nearly four years to complete the project which has begun generating 25 Megawatt and it will reach its potential in the coming years…. The project has created jobs for 1,300 Ethiopians and 286 expatriates. 3

‹‹በ2017 እኤአ የቆሼ ደረቅ ቁሻሻ ማጠራቀሚያ ተደርምሶ 140 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፣ የረፒ የደረቅ ቁሻሻ 50 ሜጋዋት የኤሌትሪክ ኃይል በ96 ሚሊዮን ዶላር በማመንጨት ከስምምነቱ ፊርማ ሳይደርቅ ከ50 ወደ 25 ሜጋ ዋት ዝቅ ማለቱ ሃገሪቱ ሁነኛ አዋቂና ተደራዳሪ እንደሌላት አልያም በሙስናና ሌብነት የተነሳ የተፈፀመ ወንጀል ሊሆን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ሹማምንት በህግ ሊጠየቁ ይገባል እንላለን፡፡›› Ethiopia launches 50 (MW) waste energy plant/ waste energy plant emerges on same landfill site that collapsed on nearby dwellers in 2017, killing some 140 people africa 19.08.2018 Ekip Ankara/  ‘’It is a significant project of garbage disposal, recycling and environmental protection,’’ he added. Ethiopia invested $96 million in the plant which is constructed by British firm Cambridge Industries Limited and China National Electrical Engineering Company. It took nearly four years to complete the project which has begun generating 25 Megawatt and it will reach its potential in the coming years.››4

እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ፣  በአፍሪካ ፋጣን የከተማ እድገት በሚቀጥለው ባለፈው 50 ዓመታት ውስጥ ከነበረበት 19 በመቶ ወደ 39 በመቶ የከተማው ህዝብ ብዛት እንደሚጨምር ማለትም 350 ሚሊዮን ህዝብ በ2030 እኤአ ከገጠር ወደ ከተማ እንደሚፈልስ ታውቆል፡፡ ሆኖም በከተማው ውስጥ ያለ የደረቅና ፈሳሽ ቁሻሻ መሠረተ ልማቶችና ማኔጅመንት ከፍተኛ ችግር መሆኑ ታውቆል፡፡ በኬኒያ ናይሮቢ ከተማ 2475 ቶን ቁሻሻ በየቀኑ በዳንዶራ የደረቅ ቁሻሻ ስፍራ ይደፋል፡፡ ካንፓላ ከተማ 1300 ቶን በቀን በኪቲዚ የደረቅ ቁሻሻ እንደሚጣል ታውቆል፡፡ በዳሬሰላም ከተማ 4600 ቶን በቀን  የደረቅ ቁሻሻ ቦታ ሲደፋ ቀሪው ግማሽ በከተማው ጎዳናዎች እንደሚጣል ታውቆል፡፡ According to the African Development Bank, rapid urbanisation has seen the urban share of Africa’s population double from 19 per cent to 39 per cent over the past 50 years, with some 350 million more people expected to move to urban areas by 2030. However, lack of a corresponding expansion of urban facilities including investments in waste management infrastructure, has seen most African cities choking in filth. In Nairobi, East Africa’s largest city, the 2,475 tonnes of waste produced every day are dumped in Dandora. ….. In Kampala, more than 1,300 tonnes of solid waste is generated daily, but the Kiteezi landfill. ….. In Dar es Salaam, the situation is no different. More than 4,600 tonnes of solid waste are generated per day but local estimates show that collection of waste in various cities in the country is below 50 per cent, and that the remaining 50 per cent is left to rot on streets.  በሃገረ ፈረንሳይ 126፣ በምድረ ጀርመን 121 እንዲሁም በምድረ ጣሊያን 40 የደረቅ ቁሻሻን ወደ ኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫነት የሚቀይሩ ፕላንቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ Bottom of Form

Ethiopia’s  waste-to-energy plant to be commissioned in December, November  8, 2018 — France alone has 126 waste-to-energy plants, while Germany has 121 and Italy 40.Like its European counterparts, the Reppie plant operates within the strict emission limits of the European Union. The plant adopts modern back-end flue gas treatment technology to drastically reduce the release of heavy metals and dioxins produced from the burning. The project is the result of a partnership between the Government of Ethiopia and a consortium of international companies: Cambridge Industries Limited (Singapore), China National Electric Engineering and Ramboll, a Danish engineering firm. 5

‹‹ አምራቾችና ላኪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ማሻሻያው በዝቶብናል አሉ  የታሪፉ መጠን እንዲከለስም ጠይቀዋል፣ ከመጪው ታኅሳስ ወር ጀምሮ ለአራት ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ይፋ ከተደረገ በኋላ፣ አምራቾችና ላኪዎች ታሪፉ በዝቶብናል ሲሉ ቅሬታቸውን ገለጹ፡፡ በየዓመቱ ከዝቅተኛው እርከን ከ30 እስከ 85 በመቶና ከዚያም በላይ የሚደርስ የታሪፍ ለውጥ በመደረጉ፣ በርካታ አምራቾችና ላኪዎች የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን ቢቀበሉም መጠኑ በዝቷል በማለት በድጋሚ እንዲስተካከል ሲጠይቁ ተደምጠዋል፡፡ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በጠራውና ሐሙስ ጥቅምት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በተካሄደው የምክክር መድረክ ወቅት የተብራራው የታሪፍ ማሻሻያ ላይ ቅሬታቸውን ያቀረቡት የአምራችና የላኪዎች ድርጅቶች ተወካዮች፣ ታሪፉ የወጣው ለበርካታ ዓመታት ሳይሻሻል ቆይቶ ድንገት መሆኑ አግባብ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር ዘርፍ አቶ ፀጋዬ አበበ እንደገለጹት፣ ላለፉት 12 ዓመታት የታሪፍ ለውጥ አልተደረገም በሚል ምክንያት በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ለውጥ ማድረግ ለዘርፉ ህልውና ሥጋት ነው፡፡ አቶ ፀጋዬን ጨምሮ የአብዛኞቹ ጥያቄ ያጠነጠነው የታሪፍ ለውጡን ተከትሎ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ጥራት ላይ የተመሠረተ ነበር፡፡ ከሚያስፈልጋቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ ግማሽ ብቻ እያገኙ ባሉበት፣ አብዛኛውን ጊዜ በሚቆራረጠው ኃይል አቅርቦት ሳቢያ በርካታ የምርት ብክነትና ኪሳራ እንደሚያጋጥማቸው የጠቆሙት አምራቾች፣ ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔ ሳይሰጥ ታሪፍ መጨመሩ አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ በዋጋ ጭማሪ ብቻ ችግሩ አይፈታም ያሉት አቶ ፀጋዬ፣ ሚኒስቴሩም ሆነ በሥሩ የሚተዳደሩት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኩባንያዎች በሰው ኃይላቸው ላይም ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡ በርካቶችም በየድርጅቶቻቸው ላይ ስለሚገጥማቸው ችግርና ውዝፍ ክፈሉ ተብለው ስለሚጠየቁባቸው ጉዳዮች ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ይህ ይባል እንጂ ሚኒስትር ዴኤታው ፍሬሕይወት ወልደሃና (ዶ/ር)፣ የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ትክክለኛውን የኃይል አቅርቦት ዋጋ እንደማያንፀባርቅ፣ ነገር ግን የተቋሙን የኦፕሬሽን ወጪዎች ለመቀነስ እንዲያግዝ ተብሎ የወተሰደ ዕርምጃ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የሚታየው የኃይል መቆራረጥና የጥራት ችግርም በተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ሳቢያ በአንድ ጊዜ ይፈታል ማለት እንዳልሆነም አክለዋል፡፡ በመኖሪያ ቤት ተጠቃሚዎችና በኢንዱስትሪ ተጠቃሚዎች ላይ የተደረገው ማሻሻያ ከታኅሳስ ወር ጀምሮ በየዓመቱ እየተተገበረ ለአራት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን፣ ከአራት ዓመታት በኋላ ዳግመኛ እንደሚከለስ ይጠበቃል፡፡ ለመኖሪያ ቤት ተጠቃሚዎች ምንም የታሪፍ ለውጥ ያልተደረገበትን በሰዓት የ50 ኪሎ ዋት ወርኃዊ ፍጆታ ሳያካትት፣ ከ100 ኪሎ ዋት እስከ 500 ኪሎ ዋትና ከዚያም በላይ በሚጠቀሙት ላይ እንደየፍጆታቸው መጠን ከ30 እስከ 85 በመቶ የሚደርስ የታሪፍ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡ በአንፃሩ ለኢንዱስትሪ ተጠቃሚዎች ወጥነት ያለው የታሪፍ ማስከፈያ በመተግበር ከዚህ ቀደም በከፍተኛና በዝቅተኛ የኃይል ጭነት ልክ ለማስከፈል ታቅዶ ተግባራዊ ሳይደረግ የቆየውን አሠራር በመተካት ከዚህ ቀደም ድጎማ የታከለበት ታሪፍ መቅረቱም ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም በታኅሳስ 2011 ዓ.ም. በአንድ ኪሎ ዋት የሚታሰበው ታሪፍ 1.0352 ብር ሆኗል፡፡ ወርኃዊ የቅድመና ድኅረ አገልግሎት ክፍያ እንደሚታከልበትም ተብራርቷል፡፡ በመሆኑም የቮልቴጅ መጠናቸው (ከ220 እስከ 380) ዝቅተኛ ቮልቴጅ፣ እንዲሁም ከ15 ኪሎ ቮልት እስከ 33 ኪሎ ቮልት ብሎም ከ66 ኪሎ ቮልት በላይ ኃይል በሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች ላይ በወጥ ታሪፍና በከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚነት ሥሌት መሠረት (ዲማንድ ቻርጅ) እንዲክፍሉ የሚደረጉባቸው ታሪፎች ይፋ ተደርገዋል፡፡›› 6

የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን አዲስ የዋጋ ታሪፍ ጭማሪ ማስተካከያ ከፍተኛ የኤሌትሪክ ፍጆታ ተጠቃሚዎች በአዲሱ ተመን እስከ 350 በመቶ ጭማሪ ክፍያ ይጠየቃሉ። ድርጅቱ እዚህ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ አስቀድሞ ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት (EEU)፣ ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ፓወር (EEP)፤ ከውሃ፣ መስኖ እና ኤሌትሪክ ባለስልጣን መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን ጥናቱን ማድረጉን አስታውቋል። በአዲሱ የዋጋ ማስተካከያ መሰረትም በፊት ድርጅቱ ከሚያገኘው ከ7 እስከ 10 ቢሊዮን ብር ገቢ ወደ 35 ቢሊዮን ብር ያስገባል ተብሎ ታቅዷል። የዋጋ ማስተካከያው ከ13 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መደረጉን ታውቆል። በአጠቃላይ 2.5 ሚሊዮን ደንበኞች አሉን። ከእነዚህ ውስጥ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑት ከ50 ኪሎ ዋት በታች ተጠቃሚዎች ናቸው። በዚህ ጥናት መሰረትም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ታሳቢ ያደረገ ነው። ለከፍተኛ የኤሌትሪክ ፍጆታ ተጠቃሚዎች ለሆኑት በፊት በአንድ ኪሎ ዋት በዶላር 7 ሳንቲም የነበረው ወደ 1.8 የአሜሪካ ዶላር ከፍ ይላል። የዋጋ ተመኑ በዓለም ላይ ዝቅተኛ ክፍያ ዝቅተኛ መሆኑ ታውቆል።

ለአዋሽኮምቦልቻ ሃራ ገበያ የኤሌትሪክ ኃይል ማቅረብ አልቻለም፣ የመጀመሪው ከመቐለ እስከ ወልዲያ (ሃራ ገበያ) የሚገነባው 368 ኪሎ ሜትር የባቡር መሥመር በቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (ሲሲሲሲ) የግንባታ ሥራ ተከናውኖል፡፡የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት፣ ለአዋሽ- ኮምቦልቻ ሃራ ገበያ 2007 ዓ/ም የኤሌትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ፣ የሚያስፈልጉ ሰባት የኤሌትሪክ ስብ ስቴሽን እንዲሁም 345 ኪሎ ሜትር የኤሌትሪክ መሰመር መዘርጋት አልቻለም፡፡ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን  የፋይናንስ ምንጭ አልተገኘም ብድር በማፈላለግ ላይ ነን ይላሉ፡፡ በዚህም የተነሳ በ2007 ዓ/ም ተጀምሮ በ2012 ዓ/ም ይጠናቀቃል ቢባልም እስካሁን የብድር የገንዘብ ምንጭ ባለመገኘቱ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይልና የምድር ባቡር ተናቦ መስራት አልቻሉም፡፡ ከመቐለታጁራ ወደብ ባቡር፣ የመቐሌ-ወልዲያ-ሀራ ገበያ ባቡር መስመር ልማት ግንባታ፣ አንዱ የሆነው አዋሽ-ኮምቦልቻ-ሃራ ገበያ ሲሆን 375 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው፡፡ የትግራይ ክልላዊ መንግስት እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ (2015/16 – 2019/20) ሁለተኛው የአምስት አመት እቅድ መሠረት፣ የኢትዩጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ከመቐለ-ታጁራ ወደብ በ3.2 ቢሊዩን ዶላር ለሚገነባው ባቡር መስመር የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦል፡፡757 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በሁለት ክፍል ተከፍሎ የሚካሄድ ነው፡፡ የመጀመሪው ከመቐለ እስከ ወልዲያ (ሃራ ገበያ) የሚገነባው 368 ኪሎ ሜትር የባቡር መሥመር በቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (ሲሲሲሲ) የግንባታ ሥራ ተከናውኖል፡፡ ይህ ግንባታ 1.6 ቢሊዩን ዶላር ሲሆን ከቻይና ኤግዚም ባንክ ብድር ተገኝቶል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ 389 ኪሎ ሜትር የባቡር ሃዲድ መሥመር በቱርክ ኩባንያ ያፒ ማርከንዚ  ኮንስትራክሽን ካምፓኒ በ1.7 ቢሊዩን ዶላር የግንባታ ወጪ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ብድሩ በቱርክ መንግስትና ከክሬዲት ስዊስ እንደተገኘ ቢገለጽም ብድሩ አልተሳካም፣ የቻይና መንግስትም የአዋጭነት ጥናቱ ደካማ በመሆኑ ምክንያት ለማበደር አልተስማሙም፣ ማለትም የኤሌትሪክ ባቡሩ ምን ጭኖ ሄዶ ምን ጭኖ ይመለሳል፣ የጥናቱ የአዋጨጭነት የገቢው ምንጭ እዳውን ለመክፈል አይቻለውም በማለት ውድቅ አድርገውታል፡፡

ለማጠቃለል የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል 5 ቢሊዩን 490 ሚሊዬን ዩኤስ ዶላር ብድር እንዳለበት ጥናቶች በዝርዝር ያሳያሉ፡፡ የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል 1.2 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ከኢትዬጵያ መንግስት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር IFIs/ Government to Sector Institutions on-lending የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ሹማምንት ጋር ከተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ተቆማቶች መኃል (የዓለም ባንክ ዓለም ዓቀፍ ልማት ትብብር   ( International Development Association (IDA)፣ የአፍሪካ የልማት ባንክ African Development Bank (AfDB)፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ European Investment Bank (EIB) etc.) ኮንሴሽናል ብድር (Concessionary loans) ለኤሌትሪክ አገልግሎት ዘርፉ አበድረዋል፡፡ኮንሴሽናል ብድር ዋንኛ ገፅታዎች አንደኛ ብድሩ የመካከለኛና የረጅም ግዜ ብድሮችን ሲያካትት፣ የብድሩ ግዜ ለሃያ ዓመታት መሆኑ፡፡ ሁለተኛ የብድሩ የእፎይታ ግዜ (grace period) አምስት ዓመታት መሆኑና፡፡ በእፎይታ ግዜት ተበዳሪው መንግስት ወለዱን ብቻ እንጂ ዋናውን ገንዘብ (principal) መክፈል አይችልም፡፡ ሦስተኛ ተበዳሪዉ መንግስት የተበደረውን ገንዘብ በአነስተኛ ወለድ ከ3 እስከ 6 በመቶ ጨምሮ የመክፈል ግዴታ ይጠበቅበታል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ኮርፖሬሽን ያለ አንዳች ጥናት በአንድ ጊዜ ከሦስት እጥፍ በላይ ጭማሪ ማድረግ በህዝቡና በንግዱ ህብረተብ ላይ የድርጅቱን የእዳ ጫና ለማቃለል፣ እነሱ በሙስናና ሌብነት ሃገሪቱን መቀመቅ ከተው ህዝብ ብድሩን እንዲከፍልላቸው ይሻሉ፡፡ መሆን ያለበት የመስኞችና ሌቦቹን ንብረት በህግ ተሸጦ የሃገሪቱ እዳ መከፈል አለበት እንላለን፡፡ በአዲሱ የዋጋ ማስተካከያ መሰረትም በፊት ድርጅቱ በአመት የሚያገኘው ከ7 እስከ 10 ቢሊዮን ብር ገቢ በአንድ ጊዜ ወደ 35 ቢሊዮን ብር በአመት ያስገባል ብሎ ማቀድ ‹‹ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል›› እንዳይሆን አስቡበት፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ደንበኞች 2.5 ሚሊዮን ህዝብ ከ107 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ብቻ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡  ከ10 ወደ 35 ቢሊዮን ብር ገቢ መመኘት ምንም ትምህርት የሌላቸው በትምህርትና በጥናት ያልታገዘ የኤሌትሪክ ገቢ በመሆኑ በአዋቂዎች አስጠኑት እንላለን፡፡ ሌላው የኢትዮጵያ ግብር ከፋይ ህዝብ በቅድሚያ የኤሌትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሳይሆን ለጎረቤት አገራት መሸጥ አንዱን ልጅ አንዱን የእንጀራ ልጅ ማድረግ ነው እንላለን፡፡ የጎረቤት አገራት የኤሌትሪክ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉት ግብር ከፋዩ ህዝብ ከተዳረሰ በኃላ መሆን አለበት እንላለን፡፡ እስከዛው የውጭ ምንዛሪ ገቢን ለማሳደግ በህብረት እንረባረብ እንላለን፡፡

የሜቴክ የሌብነት ወንጀለኞች ተጠናክሮ ይቀጥል!!! የትግራይ ህዝብ ሌቦቹን አሳልፎ መስጠት ይጠበቅበታል!!!

የህግ ሉዕላዊነት ይከበር!!!  ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው!!!

ምንጭ፣

(1) Ethiopia’s 50MW Waste to Energy Plant Could be First of Many 18.01.2013 12:25  Waste to Energy Markets & Policy

(2) Xinhua| 2017-08-31 22:37:04|Editor: yan / Video PlayerClose

ADDIS ABABA, Aug. 31 (Xinhua)

(3) Environment August 18, 2018August 18, 2018 newbusiness

(4) Anadolu Agency

(5) Xinhua| 2017-08-31 22:37:04|Editor: yan   Video PlayerClose

ADDIS ABABA, Aug. 31 (Xinhua)

(6) ሪፖርተር ጋዜጣ 11 November 2018 ብርሃኑ ፈቃደ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.