መታየት ያለበት…..የእስረኞች ሰቆቃ አስከፊው “የታራሚዎች” አያያዝ ከ እስራ ከተፈቱ በኋላ እስረኞች የደረሰባቸውን ግፍና በደል ለአማራ ቲቪ እንዲህ ተናግረዋል

መታየት ያለበት…..የእስረኞች ሰቆቃ አስከፊው “የታራሚዎች” አያያዝ ከ እስራ ከተፈቱ በኋላ እስረኞች የደረሰባቸውን ግፍና በደል ለአማራ ቲቪ እንዲህ ተናግረዋል

<<የአማራ ህዝብ እኔን ለማስፈታት ምን ያህል ዋጋ እንደከፈለ ስለማውቅ መንግስት ይቅርታ አደረገልኝ ልል አልችልም፤ ያስፈታኝ ህዝቤ ነው>> መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ

<<ታምሚያለው ነገር ግን የአማራ ህዝብ ያሳክመኛል፣ በህዝቤ እምነት አለኝ፤ እኔም እታገላለው>> አበበ ካሴ

<<ማንም ይምጣ ማን የእኛ መሬት ድንበር ተከዜ ነው፣ ራያ የአማራ ነው፣ የምንፈልገው መሬቱን ብቻ አይደለም። ሕዝቡንም ነው፣ ወልቃይትን የምንፈልገው መሬቱን አይደለም ሕዝቡን ነው፣ የሚሰማ ይስማ፣>>አበበ ካሴ
.
.
.
እነዚህ የእኛን የመላው አማራን ሁሉ ግፍ የተቀበሉ ወንድሞቻችን በህዝባቸው ያላቸው እምነት፣ ይህንን ያህል ተሰቃይተው በውስጣቸው ያረገዙት ቂም ሳይሆን ይቅር ባይነት ይገርማል።

የእስር ቤት ሰቆቃ ክፍል አንድና ሁለትን ተመለከትኩት።አሁንም የተሰማኝ ስሜት ለቅሶ አይደለም።ሳቃይና በደላቸውን በአክቲቪስቶችና በጋዜጠኞች ስለሰማውት ተላምጀው ይሁን መንፈሰ ጠንካራ እየሆንኩ ብቻ አላውቅም ሰዎች አንባው ወዘተ ሲሉ ራሴን እየታዘብኩ ነው ያየውት።ሌላ ሰው እንደ እንዴ የተሰማው ይኖር ይሆን?..

አንድ ነገር ግን አረጋግጦልኛል።ስንጮህላቸው የነበሩት አብዛኛዎቹ የእኛ ስሜት ያላቸው፣ በማንነታቸው ግፍ የደረሰባቸውና ወደፊትም ከእኛ በተሻለ መታገል የሚችሉ የራሳችን ሰዎች መሆናቸውን።

ክፍል ሶስትና የመጨረሻው ገራሚ ክፍል ደግሞ ዛሬ ምሽት ይቀርባል አሉ.

ንግግራቸውን ወደ ፅሁፍ ለመቀየር አስቤ ነበር።ግን ማበላሸት ይሆናልና ዝም ብላችሁ ተመልከቱት።

አበበ ካሴ ውስጥ የሚነበበው እልህ የሚታየው የበረሃ አይደፈሬነት፣ እንዲህ አሰቃይተውትም የሚንጠው የወልቃይት የራያ አማራነት ስሜት እኛንም ስቦ ወደፊት እንድንራመድ የሚያስፈነጥር የፈረስ ጉልበት ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.