‹‹ ከአገር በቀል ወደ አገር ነቀል የሪል ስቴት ዲቭሎፕርነት!!! የመሬት ቅርምት ሚሊየነሮች!!!››   ‹‹የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር››  ሚሊዮን ዘአማኑኤል 

ኢት-ኢኮኖሚ      /ET- ECONOMY

በህወሓት/ ኢህአዴግ ምላሳዊው መንግሥት፣ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት በሪል ስቴት ልማትና የመሬት ቅርምት ሚሊየነሮች አፍርታለች፡፡ በኢትዮጵያ የፍርድ ሥርዓት የሚዘወረውና የሚሽከረከረው በከፍተኛ ደረጃ ባሉ የፖለቲካ ባለሥልጣኖች ነው፡፡ የሃገሪቱ ህገ መንግሥት ነፃ የፍርድ ሥርዓት መኖሩን ለይስሙላ ቢያረጋግጥም ሙስናና ሌብነት የተንሰራፋበት መንግስታዊ አገዛዝ እንደሆነ ህዝቡና የንግዱ ህብረተሰብ የአገዛዙ ሥርዓት አወቃቀር በሙስና ሠንሰለት የተሳሰረ በጉቦና  ኪራይ ሠብሳቢነት ሥርዓቱ ግንኙነት ድርና ማግ ግንኙነት ድርና ማግ ናቸው፡፡ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሙስናና ሌብነት የሚገለጽባቸው በሃገሪቱ ባለው {1} የፍርድ ሥርዓት፣{2} ፖሊስ፣ {3} የህዝብ አገልግሎቶች፣ {4} የመሬት አስተዳደር፣ {5} የታክስ አስተዳደር፣ {6} የካስተም/የጉምሩክ አስተዳደር፣ {7} የፐብሊክ ፕሮክሪመንት፣ግልፅ ጨረታ {8} የተፈጥሮ ኃብቶች፣ {9} የህግ አውጪ፣ እንዲሁም {10} ሲቪል ሶሳይቲ/ማህበራዊ ድርጁቶች ውስጥ ነው፡፡ የወያኔ የመሬት አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ መሬት በሪል ስቴት ልማት ስም የተደረገውን የመሬት ቅርምት የሙስናና ሌብነት ሥራን እንቃኛለን፡፡

የመሬት አስተዳደር (Land Administration) በኢትዮጵያ  የመሬት አስተዳደር ስራ በከፍተኛ የሙስና ይፈፀምበታል፡፡ የንግዱ ህብረተሰብ የግል ንብረትና ኃብት መብት በህግ የተጠበቀ አይደለም፡፡ ግማሽ የሚሆኑት የንግድ ድርጅቶች ባለቤቶች የግንባታ ፍቃድ በሚጠይቁበት ጊዜ ገፀ በረከት ስጦታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡  አንድ ሶስተኛ የንግዱ ህብረተሰብ ለመሬት አስተዳደር ጠራተኞች ጉቦ  ይሰጣሉ፡፡ በመሬት አስተዳደር የሥራ ዘረፍ ሙስናና የመሬት ቅርምት የተለመደ ነው፡፡ በመሬት አስተዳደር ዘርፍ በጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር ላይ የተገነባ ስላይደለ ግልፅነት ፣ ትክክለኛ ፖሊሲዎች፣ እና የማስፈፀም አቅምና ኃብት የላቸውም፡፡ የመሬት አስተዳደር ሠራተኞች በሃሰተኛ መረጃ/ ፎርጀሪ ህገወጥ የመሬት ባለቤትነት ፍቃድ  ለ15000 ሰዎች ሰጥተዋል፡፡  በዚህ ድርጊት ጥቂት ሠራተኞች ብቻ ተጠያቂ ሆነዋል፡፡   የግሉ ዘርፍ የመሬት ባለቤትነት መብት የላቸውም፣ ሁሉም መሬት የመንግስት ኃብት ነው፣ መንግስት መሬት በሊዝ ለ99 አመታት ይከራያል፡፡ መንግሥት የ3000 ኢንቨስተሮችን መሬት አላለማችሁምና አልሰራችሁበትም በማለት ነጥቆል፡፡ There is a high risk of corruption  in Ethiopia’s land administration. Businesses report that property rights are insufficiently protected in Ethiopia (GCR 2016-2017). Half of all companies expect to give gifts when applying for a construction permit (ES 2015). A third of Ethiopians report having paid a bribe to a land administration official (GCB 2013). Petty corruption and land-grabbing is common in the land administration sector (TI 2014). This is caused by the absence of strong institutions, transparency, clear policies, and a lack of resources (TI 2014). Officials have also engaged in forgery practices, thereby assigning themselves an estimated 15,000 titles illegally; only a few have been held accountable (TI 2014). There is no right to private ownership of land; all land is owned by the state and leased out for up to 99 years (ICS 2017). Expropriation may only happen when required by the public interest and with payment of adequate compensation (ICS 2017). The government revoked the leases of 3000 investors for “failing to develop the land” because they had not started production within the agreed-upon time frames (BTI 2016). Conflicts between international investors and local communities over land rights have occurred in the past; the government has been accused of performing land-grabs in favor of international investors (BTI 2016). Investors are advised to perform thorough due diligence on the attitude of local communities before making an investment (ICS 2017). Registering property in Ethiopia is slightly faster than the regional average, while the number of steps required is in line with regional averages (DB 2017).

የፐብሊክ ፕሮክሪመንት/ጨረታ፣ (Public Procurement) በኢትዮጵያ የፐብሊክ ፕሮክሪመንት፣በመንግሥታዊ ዘርፍ አሰራር ግልፅና ነፃ ጨረታ እንደሌለ ይህም አሰራር ለሙስናና ሌብነት ሥርዓቱን እንደዘፈቀው ይታወቃል፡፡ ከአምስት አንድ የንግድ ካንፓኒዎች የመንግስት የኮንትራት ሥራ ያለጨረታ ለማግኘት ጉቦ ይሰጣሉ፡፡ የንግድ ፍቃድና የኮንትራት ስራ ለማግኘት ጉቦ መስጠት የተለመደ ነው፡፡ መንግሥታዊ የጨረታ አስተዳደር ስለሌለ በሙስናና ሌብነት ጨረታ በማጭበርበር ይከናወናል፡፡ በህወሓት/ኢህአዴግ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች የሃገሪቱን ኢኮኖሚ በሁሉም ዘርፍ ይቆጣጠራል፡፡ እነዚህ ድርጅቶች ከባንክ ብድር የማግኘት ዕድል፣ ለኢፈርት፣ ሜቴክ፣ሜድሮክ የመሳሰሉ ድርጅቶች የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ የሚያበድረው ብድር አድሎ የተሞላበት ነው፡፡ ፋጣንና ቀልጣፋ የጉምሩክ አገልግሎት የማግኘት እድል፣  የውጭ ምንዛሪ በቅድሚያ የማግኘት እድል፣ የመንግስት ጨረታን ያለውድድር የማግኘት እድል፣ የሃገር ውስጥና የውጭ ገበያ የማግኘት እድል፣ የመሬት ጥያቄ ለመንግስትና ለግሉ ዘርፍ ለተሰማሩ አድሎ መኖር፣ የመንግስት ግብር አለመክፈል፣ በብሔራዊ ባጀት ‹የመንግስት የልማት ድርጁቶች› አጠቃላይ ባጀት ይገለፃል እንጂ የተናጥል ባጀታቸው ለህዝብ ይፋ አለመደረግ፣ እንዲሁም የኦዲት ሪፖርት አለማድረግ ወዘተ  እነዚህ ድርጅቶችን በቦርድ የሚያስተዳድሩት የህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ሹማምንቶች፣ የፖለቲካ ካድሬዎችና የጦር ጀነራል መኮንኖች ሲሆኑ በትምህርትና በእውቀት ነፃ ውድድር የተያዘ ሥራ ባለመሆኑ ብዙዎቹ ለኪሳራ ይዳረጋሉ፡፡ ከግሉ ዘርፍ የበለጠ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ግልፅ የጨረታ ሥርዓት አለመኖሩ ምክንያት ሜቴክ የተዘፈቀበትን ወንጀል ልብ ይበሉ፡፡ ‹‹ሜቴክ ያለ ህጋዊ የጨረታ ሂደት የ37 ቢሊየን ብር የውጭ ሃገር ግዥ ፈፅሞል፡፡ አዲስ አበባ፣ ህዳር 3 ቀን 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ)  ያለ ህጋዊ የጨረታ ሂደት  የ37 ቢሊየን ብር የውጭ ሃገር ግዥ መፈፀሙን የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ገለጸ፡፡….የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከ2004 እስከ 2010 ዓ/ም ድረስ ባከናወናቸው ግዥዎችና ተዛማጅ ጉዳዬች ላይ ምርመራ በማድረግ … በንብረት ግዥና ፋይናንስ ጋር በተያያዙ የግዥ ሂደቶች ላይ ከፍ ያለ የህግ ጥሰት መፈፀሙን አስረድተዋል፡፡…. ከሃላፊዎች ጋር የስጋ ዝምድና ያላቸው ግለሰቦችም እንደ ደላላ በመሆንና ተቆሙን ከተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ኩባንያዎች ጋር በማገናኘት ግዝው እንዲፈፀም ማድረጋቸውን ጠቅስው በዚህም በቢሊየን የሚቆጠር የሃገር ሃብትና ንብረት መመዝበሩን አንስተዋል፡፡ የንብረት ግዥው ከአንድ ኩባንያ በድግግሞሽ እንደሚፈፀም … በዚህ ሂደት ግዥው ላይ እስከ 400 ፕርስንት የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ግዥው ይፈፀም ነበር፡፡ ከዚህ ባለፈም ተቆሙ የሃገር ውስጥ ግዥን ሙሉ በሙሉ  ያለምንም ጨረታ ሂደት መፈፀሙንም አስረድተዋል፡፡››  Public Procurement/ There is a high risk of corruption in Ethiopia’s public procurement sector. One in five companies indicate expecting to give gifts in order to obtain government contracts (ES 2015). Likewise, irregular payments and bribes are common in the process of awarding public contracts and licenses (GCR 2015-2016). Companies complain of unlawful contract termination and non-transparent tender award processes, and report  favoritism towards vendors who provide concessional financing (ICS 2017). State-owned enterprises (SOEs) and companies owned by Ethiopia’s ruling party dominate major sectors of the economy (ICS 2017). SOEs have advantages over private companies, including easier access to credit and easier customs clearance (ICS 2017). Foreign investors complain of the lack of level playing field; there are indications that SOEs receive preference in government tenders (ICS 2017). While many tenders are publicly advertised, there are major instances of contracts being awarded without a tender (GI 2017). Metal & Engineering Corp, the biggest employer in the country, has frequently received contracts without a bidding process (GI 2017). Documents relating to procurement processes are difficult to obtain due to a burdensome bureaucracy and a lack of transparency (GI 2017). The FDRE Public Procurement & Property Administration Agency publishes a list of companies barred from future bidding due to past violations on its website (GI 2017).

የተፈጥሮ ኃብቶች Natural Resources፣  የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ያለዓለም አቀፍ ጫረታ ሳይወጣ ለጣሊያኑ ሳሊኒ የተሰጠ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡There is a high risk of corruption in Ethiopia’s natural resources sector. Financial records relating to natural resource exploitation are not publicly available (GI 2017). There have been concerns that the Grand Ethiopian Renaissance Dam was developed without competitive bidding and the quality of the environmental assessment was lacking (TI 2015). Ethiopia’s extractive industries, especially the mining sector, are a hotbed for corruption ; state-owned drilling companies benefit from political favoritism, whereas private companies face high market-entry barriers (World Bank, 2012). Following its application in 2014, Ethiopia is currently working towards implementing the EITI standard to improve accountability and transparency in the mining sector (EITI 2017). Ethiopia’s compliance with the standard will be measured starting in 2018 (EITI 2017).

በኢትዮጵያ የሪል ስቴት የቤቶች ልማት ልማት ፖሊሲ ሳይወጣ፣ የሪል ስቴት አልሚዎች እውቀትና ክህሎት ሳይጠና፣ የቤቶቹ ገንቢዎች ገንዘብ በዝግ አካውንት ባንክ ውስጥ ሳይቀመጥ በቀጥታ በሪል ስቴት ዲቨሎፐርስ አካውንት ውስጥ የቤት ፈላጊዎች ገንዘብ በመቀመጡ ብዙ ዜጎች ለዘረፋ ተዳርገዋል፡፡ በዚህም የህወሓት/ኢህአዴግ ሙስኛና ሌባ መንግሥት የዜጎቹን የወደፊት እድልና ተስፋ ቀጭቶል፡፡ የዜጎቹን ገንዘብ ቆጥቦ ቤት የመገንባት የወደፊት ተስፋ አጨልሞል፡፡ የቤቶችና የገንዘብ ቁጠባ ባንክን (ሞርጌጅ ባንክን) አፍርሰዋል፡፡ በሪል ስቴት የቤቶች ልማት ስም የብዙ ዜጎች መሬት ተነጥቆል፣ ተዘርፎል፣ ከፍተኛ የመሬት ቅርምት ተደርጎል፡፡ ዛሬ በከተማችን የምናያቸው ቢሊየነሮችና ሚሊየነሮች የሃብታቸው ምንች ከመሬት ቅርምት የተገኘ ለመሆኑ ጠንቆይ መቀለብ፣ ኮኮብ ቆጣሪ ማጠየቅ፣ መፀሃፍ ገላጪ ማስነበብ አይጠይቅም፡፡  በ2002ዓ/ም ድረስ የሪል እስቴት አልሚዎች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የወሰዱት ቦታን በማየት የተፈጸመውን ወንጀል፣ መሬቱን የተዘረፈውን ዜጋ በማስረጃ ለማየት ይጠቅማል እንላለን፡፡ ወያኔ ግብረ አበሮቻቸው በተመቻቸላቸው የዘረፋ ሥርዓት የህዝብ ንብረትና ሃብት በጉልበት ነጥቀው ዜጎችን አደህይተዋል፣ ዛሬ አንድ ሜትር ካሬ መሬት እስከ 350 ሽህ ብር በጨረታ ይቸበቸባል፣ ዛሬ አንድ ቪላ ቤት ከ5 እስከ 10 ሚሊየን ብር ይሸጣል፡፡ የከተማው ነዋሪ በመሬቱ ላይ እንዳይኖር አራትና አምስት ፎቅ ካልሰራህ ልቀቅ እየተባለ ከመሬቱ ተገፋ፣ ተነጠቀ፣ ተዘረፈ፡፡ የእነዚህ ሪል ስቴት አልሚዎች የደም ገንዘብ ከዜጎች ላይ የተመዘበረ በመሆኑ በህግ ሊጠየቁ ይገባል እንላለን፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት በሪል ስቴት ልማት ስም የተላለፈላቸው የ160 ግለሰቦችና ድርጅቶች ስም ዝርዝር (2002 የተደረገ ጥናት)

{1} የመሬት ቅርምት እስከ 57,679  ሽህ ካሬ ሜትር እስከ 1,336,296 ሚሊዩን የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣የዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት በሪል ስቴት ልማት ስም የተዘረፈውን ዜጋ ይታደጋል፡፡

 • አያት ኃ/የተ/የግ/ማ የቦታው ስፋት 1,336,296 ካ.ሜ ልዩ ልዩ ክፍለ ከተማዎች
 • ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ የቦታው ስፋት 262,868 ካ.ሜ ልዩ ልዩ ክፍለ ከተማዎች
 • ካራ ቆሬ ኃ/የተ/የግ/ማ ድምር የቦታው ስፋት 255,046 ካ.ሜ ልዩ ልዩ ክፍለ ከተማዎች
 • ጊፍት ትሬዲንግ ሪ/ኃ/የተ/የግ/ማ የቦታው ስፋት 162,997 ካ.ሜ የካ 20/21 ክፍለ ከተማ
 • ሳትኮን ኮንስትራክሽን የቦታው ስፋት 104,100 ካ.ሜ የካ 20/21 ክፍለ ከተማ
 • ተ/ብርሃን አምባዬ ሪል እስቴት የቦታው ስፋት 100,000 ካ.ሜ የካ 20/21 ክፍለ ከተማ
 • ዮሴፍ ተገኝ ድምር የቦታው ስፋት 71,996 ካ.ሜ የካ 20/21 የካ 20/21 ክፍለ ከተማ
 • Getty / ኖርዝ ጌት /LTD/ የቦታው ስፋት 68,700 ካ.ሜ ቦሌ 16 ክፍለ ከተማ
 • ቫርኔሮ የቦታው ስፋት 67,500 በካ.ሜ ን/ስ/ላ 1 ክፍለ ከተማ
 • ሙሉነሽ ፍጥረት የቦታው ስፋት 66,763 ካ.ሜ ን/ስ/ላ 1ክፍለ ከተማ
 • ጌታቸው ወልዴ ሪል እስቴት የቦታው ስፋት 57,679 ካ.ሜ በን/ስ/ላ 1 ክፍለ ከተማ
{2} የመሬት ቅርምት ከ40,000  ሽህ እስከ 50,000 ሽህ ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ የመሬት ቅርምት 50,000 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ሴንቸሪ 21 ኮንስትራክሽን፣ ኤስ ኤን ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ጋድ ኮንስትራክሽን፣ ጂ.ኤች ሲሚክስ፣ ከአጆ ኢንተርናሽናል፣ ኖብል ሪል እስቴት፣ አደይ አበባ ሪል እስቴት፣ ገ/ሚካኤል ማርቆስ፣ ፔትራም ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ዮቴክ ኮንስትራክሽን፣ ቢኒያም ጥላሁን /ማርብስ/፣ ካንትሪ ክለብ ደቤሎኘመንት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ያንኮማንድ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ፈሪስት ሪል እስቴት፣ እንይ ጀነራል ቢዝነስ፣ አክስስ ሪል እስቴት፣ አድሮም ጀኔራል ትሬዲንግ፣ ሉና /የተ/የግ/ማ፣ ማጅኮን ጠ//ተቋራጭ፣ ደግነት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ፖስራክሲንክ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/የመሬት ቅርምት 49,610 ሽህ እስከ 40,000 ሽህ ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ ጋራድ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ በርታ ኮንስትራክሽን፣ ጌት አስ ኢንተርናሽናል፣ኃይሌና አለም ሪል እስቴት፣አምባሳደር ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ዶ/ ቻርልስ ሪል እስቴት ናቸው፡፡      

{3} የመሬት ቅርምት 30,000 ሽህ እስከ 39,216 ሽህ ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አሚዎች፣ብርሃን ጐህ//የተ/የግ/ማ፣ ኤን ኤም ቢ፣ አምድይሁን ጠቅላላ ንግድ፣ ጋን ችንግ ሪል እስቴት፣ አሴ ትሬዲንግ፣ ስርደንጂ ሃውሲንግፓን አፍሪካ ሪል እስቴት፣አሴ ትሬዲንግ፣ አሴር ሪል እስቴትተፈሪ ይርጋ፣ ሮማናት ሪል እስቴት፣ ብስራት ፀጋ ሪል እስቴት፣ መሐመድ ሰብደንኢኬር ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ደ.ኤምሴ፣ ኮሜቶ ትሬዲንግ፣ይርጋ ሀይሌና ቤተሰብ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ካስትል ሪል እስቴትካንጋሮ ኘላስት ሪል እስቴት ናቸው፡፡

{4} የመሬት ቅርምት 20,000 ሽህ እስከ 25,000 ሽህ ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ኒው ሆኘ ሪል እስቴት፣ ሰሙ ተክሌ፣ ሆም ስዊት ሆም፣ ሾላ አክስዮን ማህበር፣ ናሰው ሪል እስቴት፣ ፊባ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ሆስኢ ትሬዲንግ፣ ሚካኤል ቤቶች አካባቢ ካስማ ኢንጂነሪግ፣ ማረፊያ ሪል እስቴት፣ ክንድያ ሀጐስ ሪል አስቴት፣ ዜደ.ኤምሮማናት ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማ ሪል እስቴት ናቸው፡፡

{5} የመሬት ቅርምት 19,800 ሽህ እስከ 10,000 ሽህ ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ ሁሴን ሲራጅ ሪለ እስቴት፣ቶኘ ላንድ ሪል እስቴት፣ ሲሳይ ደስታ፣ አል አድ አሳ ሪል አስቴትሀውስ ዊዝደም ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ አቤንኮ ሪል እስቴትማይተባይ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ዮሐንስ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ፊሊክስ ኃ/የተ/የግ/ጉላጉል ትሬዲንግ ኃ/የት/የግ/ማ፣ ላዋራ ንግድና ኢንዱስትሪ፣ ወ/ ይርጋለም አሰፋው፣ ስብሃቱና ልጆቹ፣ አዜብ ሃይሉ፣ ፍቃዱና ጓደኞቹ ሪለ እስቴት /የተ/የግ/ራጉኤል የቤቶች ግንባታ /ማ፣ ሰንሴት ሆምስ ሪል እስቴት፣ ቶፊቅ ሻሽአበው ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ዋይድ ኢንጂነሪንግ፣ ፍሬው ብርሃኔ ሪል እስቴት፣ መሠረት በትዛዙ ሪል እስቴት፣ መሃመድ አሊ ሪል ስቴትሉሲ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ወ/ሮ አልጋነሽ ሃይሉ ሪል እስቴት ናቸው፡፡

{6} የመሬት ቅርምት 1,072 ሽህ እስከ 6,940  ሽህ ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ ኤልያስ አባሚልኪኤልያስ መሃመድና ኢብራሂም መሃመድ፣ እስክንድር ካሳ፣ አምሳለ ጌታቸው ፣ጀኖሪል አስቴት፣ ማይክሮ /ሥራ ተቋራጭ፣ ማደክ ካርጌት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ሜይ ሪል እስቴት፣ አዱኛ እጅጉ፣ ሳሙኤል አለማየሁ፣ አቶ ሰለሞን ወርቁ፣ ማቲያስ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ማቲያስ ኃ/የተ/የግ/ማ፣አንቶኒዩ ካርናቪያክኢምፓየር ሪል እስቴት፣ ፋሪይም ኃየተ/የግ/ማ፣ አቶ አስራት መኮንን አለምረዘነ ተፈራመልካም ራዕይ ሪል እስቴት፣ አበራ ቶላ፣ መክሊት ሪል እስቴት ናቸው፡፡ በወያኔ አገዛዝ ባለፈው 27 አመታት ውስጥ በህዝቡ ውስጥ የተፈጠረ የኃብት ክፍፍል መረን ያጣው ዜጎች በቤቶች ልማት ስም የተነጠቁት አንጡራ የመሬት ኃብት የተነሳ ነው፣መሬታቸውን የተነጠቁ ከግማሽ ሚሊን የሚበልጡ ሰዎች ቱጃሮች ሊካሱ ይገባል፣ተመጣጣኝ ቤት ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡

የህዝብ መሬት የተቀራመቱት ሌቦችም ለፍርድ ይቅረቡ!!!

ምንጭ {1} Last updated: August 2017 GAN Integrity

{2} https://www.business-anti-corruption.com/country-profiles/ethiopia/.

{3} https://tradingeconomics.com/ethiopia/corruption-rank.

 

 

‹‹ ከአገር በቀል ወደ አገር ነቀል የሪል ስቴት ዲቭሎፕርነት!!! የመሬት ቅርምት ሚሊየነሮች!!!››

‹‹የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር›› ሚሊዮን ዘአማኑኤል

ኢት-ኢኮኖሚ      /ET- ECONOMY

በወፍጮ ላይ መጁ

‹‹ስሚኝ እማምዬ፣ለምን ታለቅሻለሽ

በወፍጮ ላይ መጁ፣ሲጨፍር እያየሽ!!!››

ማምዬ ስሚኝ፣ለምን ታነቢያለሽ

በመሬት ቅርምት፣አገር ተሸጠልሽ

መብራት ወሃ የለ፣በደሳሳው ጎጆሽ፣

በመሬት ቀማኛ፣ ቀላድ መተሩብሸ

አጃና ባቄላ፣ አንቺ ነሽ የከካሽ

አሻሮና ብቅል፣ በተራ የፈጨሽ

ዓለም ተሸዓተ፣ ወያኔ እያለሽ

የትም፣ የትም ፍጪው

ዱቄት፣ ድቄቱን አምጭው

ሰው ስው ባልሸተተ ልማት

ልጆችሽ አለቁ፣ በርሃብና ስደት

ከጥንት ከጠዋቱ፣ በተካንሽው ዘዴ

ከወፍጮ ስር እህል፣ ከመጁ ስር ስንዴ

አልመሽ አድቅቀሽ፣ከሆነብሽ ሁዳዴ

ሰጪው ዱቄትሽን፣ ለንፋስ ዘመዴ፣

እንኮን የመሶቡን የጄን ተውኩላችሁ

እነ ዘር ቆጣሪ፣ እነ አጥር አጣሪ

ቀረ ዓለም ከእንግዴ፣ ከሰው ከፈጣሪ!!!

‹‹ስሚኝ እማምዬ፣ለምን ታለቅሻለሽ

በወፍጮ ላይ መጁ፣ሲጨፍር እያየሺ!!!

ጦቢያ ወፍጮ ሆና፣ መጁ ወየነልሽ

አንዱ ጡት ሲጠባ፣አንዱ ተጠማልሽ

የእንጀራ እናት ጡጦ፣ አጉርሽው እባክሽ!!!

ዱቄትሽ ተነጥቀው፣ ተራቡ ልጆችሽ

መሬት ላራሹ! ይሉ እንዳልነበር

አራሹም መሬቱም የተመነጠር!!!

የደም ግብር ለአግአዚ ጦር

እስከ መቼ እንገብር!!

ተሰደድ ከቀያቸው

ተነቀሉ ከቤታቸው

የተከሉ ከወንዛቸው

ኮበለሉ ድንበር ዘለው

የዓባይ ልጅ ውሃ ጠማው

ከውቅያኖስ ጠጡ ሰምጠው

አፈር ገፍተን፣ድቄት ፈጭተን

ታሰርን ሞተን፣የተገፋን

አብረን ተርበን የተጠማን

ዛሬም ነገም እየገበርን

ያልሰማህ ስማ ለአዋጁ አዋጅ

‹የማን ቤት ፈርሶ፣ የማ ሊበጅ

የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ!!!››

የአበው ቃል ስማ፣ እንደ እሣት የሚፋጅ

ሃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው

ወፍጮ ላይ ታዝሎ፣ አይጨፍርም መጅ!!!››

የእናት ጡት ነካሽ፣ ያዘው እጅ በእጅ

የአበው ቃል ስማ፣ ለሃገር የሚበጅ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.