ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የመጀመሪያቸው በሆነው 11ኛው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

• አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተወዳዳሪ ሆና ለመገኘት አንድ ድምፅ ልታሰማ ይገባል።
• ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ ለበርካታ ችግሮች ምላሽ የሚሆኑ የማሻሻያ እርምጃዎችን ወስዳለች
• በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን ፈታለች፣ የመገናኛ ብዙሃንን ነፃነት ማረጋገጥና የተዘጉ ድረ ገፆችን መክፈት ለአብነት ተጠቅሰዋል።
• ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅትም በሙስና ላይ ሰፊ እርምጃ እየወሰደች እና የፍትህ ስርዓቷን እያሻሻለች ትገኛለች።
• ከኤርትራ ጋር የነበረንን ግጭት መፍትሄ በመስጠት ችግሩን በመቋጨታችን በአፍሪካ ቀንድ አንፃራዊ ሰላም እና መረጋጋት መጥቷል።
• በአከባቢው ሰላም፣ ብልፅግና እና ተስፋ እየመጣ ነው በመሆኑ የመንግስታቱ ድርጅትም ኤርትራ ላይ ጥሎት የነበረው ማአቀብ አንስተዋል።
• ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በካቢኔዋ የሴቶች እኩልነትን ማሳካት ችላለች።
• የሀገሪቱን እና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶችን ሴት ማድረጓን አንስተዋል
• ኢትዮጵያ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር የበኩሏን ድርሻ ለመወጣት ቪዛን በአውሮፕላን ማረፊያ መዳረሻ የመስጠት አገልግሎትን ለሁሉም የህብረቱ አባል ሀገራት ዜጎች ጀምራለች።
• ጠ/ሚንስትሩ የአፍሪካ ህብረትን የማሻሻል ከመነሻው የተሳካ እንዲሆን አስተዋፅኦ ላደረጉት ለሩዋንዳው ፕሬዚዳንት እና ለወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ፖል ካጋሜ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
• ህብረቱ በፋይናንስ እራሱን መቻሉን ማረጋገጥ ይገባናል ።
Ethiopian Broadcasting Corporation

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.