18ኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተካሄደ

18ኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተካሄደ 1አዲስ አበባ፣ህዳር 9፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መነሻና መድረሻውን 6 ኪሎ ያደረገው 18 ኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

‘‘የነገ መሪ ሴቶችን አሁን እናብቃ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ ዓመታዊ የጎዳና ላይ ሩጫም በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሳትፈዋል።

በዘንድሮው የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ በወንዶች ምድብ የመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግጉ አትሌት ሃጎስ ገብረሕይወት አሸናፊ ሆኗል።

ቦንሳ ዲዳና ጥላሁን አየን ደግሞ በቅደም ተከተል  2ኛ እና 3ኛ  በመሆን ውድድሩን  አጠናቀዋል።

በሴቶች ምድብ ደግሞ አትሌት ፎቴን ተስፋዬ 1ኛ በመውጣት ውድድሩን ያሸነፈች ሲሆን፥  ፀሃይ ገመቹ 2ኛ እና ፀጋ ገብረስላሴ 3ኛ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቅ ችለዋል ።

በአፍሪካ ትልቁ የሆነው  ይህ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በኢትዮጵያ  ከተጀመረ በ1993 ጀምሮ እስካሁን ለ18 ጊዜ ተካሂዷል።

የዘንድሮው  ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ጋር በመገጣጠሙ ምክንያት ከዚህ በፊት  መነሻና መድረሻ የነበረውን ቦታ ከመስቀል አደባባይ  ወደ ስድስት ኪሎ መቀየሩ ይታወቃል።

ሰለሆነም ሩጫው መነሻ ቦታውን ታሪካዊው የ6 ኪ.ሎ አደባባይ በማድረግ  በሚኒሊክ ሆስፒታል፤ ቀበና፤ እንግሊዝ ኤምባሲ፤ ሾላ ገበያ፤ አድዋ ድልድይ፤ በአዋሬ ገበያ አድርጎ በፓርላማ ወደ አራት ኪሎ ተመልሶ ማጠናቀቂያውን ስድስት ኪሎ አድርጓል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.