የወያኔ ሹሞችና የጦር ጀነራሎች ጉቦ ተቀብለው፣ህፃናቶችን በጉዲፈቻነት ውጭ አገር ሸጡ!የደም ገንዘብ! ‹‹የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር››

(ክፍል አንድ)    ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም

ኢት-ኢኮኖሚ     ET-ECONOMY

‹‹የሚበላው የሌለው ህዝብ፣ መሪዎቹን ይበላል!!!›› ትንቢተ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና

‹‹ይሄ የኔ ሰው ነው፤አትንካው!!!” የሚባልበት የአይነኬዎች ስርአት ነው፡፡›› ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

የዓለም ዓቀፍ አዶብሽን ጋይድ ኢንክ ሠራተኛ የሆነው ጀምስ ሃርድሊንግ ከኢትዮጵያን በጉዲፈቻ ህፃናትን ለመውስድ ለሃገሪቱ ባለሥልጣኖችና ሹማምንት ጉቦ እንደሰጡ ለአሜሪካ ፌዴራል ፍርድ ቤት ገልፀዋል፡፡ ከ2008 እስከ 2009 እኤአ ጀምስ ሃርዲንግና የወንጀል ግብረአበሩ ለአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ኦፍ ጀስቲስ በተናዘዙት መሠረት ከኢትዮጵያ ህፃናትን በማደጎ ወደ አሜሪካ አሳዳጊ ወላጆች ለማስገባት የውሸት መረጃዎችን በማዘጋጀትና የሃሰት ዶሴዎች በመስጠት ወንጀል መሥራታቸውን አምነዋል፡፡

Adoption Agency Director Admits bribing Ethiopian Officials (January 9, 2015 by Alexis Stevens)

“An Atlanta man who previously ran an adoption agency pleaded guilty Thusday in federal court to his role in a scheme involving children from Ethiopia, the U.S. Department of Justice said. James Harding, 55, admitted that between 2008 and 2009, he and his co-conspirators submitted fraudulent documents to the State Devpartment to facilitate adoptions of Ethiopian children by U.S. parents, according to Assistant Attorney General Leslie R. Caldwell and U.S. Attorney Bill Nettles of the District of South Carolina.  Harding was employed as the international Adoption Guides Inc. at the time of the crimes. Harding admitted that he and his conspirators submitted false documentation, including contracts for adoptions signed by orphanafes that could not properly allow the children to be adopted, according to officials. Harding and others paid bribes to Ethiopian officials, including cash and all-expenses-paid travel to a government leader who approved the adoptions, despite not maintaining a proper licensed orphanage.”

የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖችና ሹማምንት ጉቦ እየተቀበሉ ህፃናቶችን በጉዲፈቻነት ይሸጡ ነበር፡፡

Adoption Agency Director Admits bribing Ethiopian Officials “We pay bribes to Ethiopian officials to approve the adoptions.” former adoption agency director by Alexis Stevens, an Atlanta…

Adopted Ethiopian children being given away on facebook (March 24, 2015)

“Ethiopia allocates an annual healthbudget of $ 140 million. However, it conveniently go out of its way nd make adoption easier and accessible as caring for its 5 million orphans costs $ 115 million a month. They even named the program as “Alternative Child Care” By Channel 4 News

“Hundreds of parents travel from the United States to Ethiopia every year to adopt kids, with 250,000 kids adopted to the US from overseas since 2000.”

‹‹ጥርስ  ያለው የጉዲፈጫ መርማሪ ኮሚሲዮን ይቆቆም!!!› በጉዲፈቻ ስም ለተሸጡ ህፃናት፣ እናቶች ዘብ እንቁም!!!›› ‹‹ ዶክተር አቢይ አህመድ፣  ጥርስ  ያለው ፀረ ሙስና መርማሪ ኮሚሲዮን አቆቁም!!!›› በጉዲፈቻ ለተሸጡ  ህፃናቶች እናቶችን እንታደጋቸው!!! በጉዲፈቻ ለተሸጡ ህፃናት እናቶች ጩህት ይሰማ!!!

ኢትዮጵያዊያን ጉዲፈቻ ህፃናት የሸጡ ለፍርድ ይቅረቡ፣ እንደ አዲስ ዘመን መረጃ መሠረት ‹‹ በአፍሪካ ወደ 35 ሽህ ልጆች በጉዲፈቻ መሰጠታቸውንና ከእነዚህም መካከል 25 ሺዎቹ ከኢትዮጵያ መሆናቸው በህዝብ ተወካች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቆሚ ኮሚቴ የቤተሰብ ህግ  እንደገና ለማሻሻል በወጣው ረቂቅ አዋጅ ውይይት ላይ ተገልፆል፡፡›› ከነዚህም ውስጥ የሰባት ሽህ ህፃናት እናቶች የልጆቻቸውን አድራሻ ለመጠየቅ ነጋ ጠባ በሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት እንባቸውን እያፈሰሱ ይገኛሉ፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይህን ጉዳይ ከምንጩ ከልጆቹ እናቶች በማዳመጥ ህፃናቶቹ በህይወት ይኑሩ ይሙቱ ቁርጣቸውን እንዲያውቁ የመጀመሪያዎ ሥራዎ ቢያደርጉት የእናትዎን ውለታ ለሌሎች ደሃና አስታዋሽ ያጡ  ኢትጵያዊ እናቶች ባለውለታ ይሆናሉ፣ በምትወዶቸው ልጆችዎ ስም አደራ እንላለን፡፡ ይሄን መረጃ ለዶክተር አብይ አህመድ እንዲደርሳቸው በማድረግ ልጃቸው፣ ጎደኞቻቸው፣ የባህር ማዶ ቴሌቨዝንና ሬዲዩ ዝግጅት ክፍሎች፣ የሳሻል ሚዲና ድረ-ገፆች እንዲተባበሩ በእናቶቹ ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ የህፃናቶች በጉዲፈቻነት በመላክ ለተሰማሩ ኤጀንሲዎች፣በኢትዮጵያ የተቆቆሙ የሃገር ውስጥና የባህርማዶ የጉዲፈቻ/ማደጎ ህፃናት ኤጀንሲ ተመዘገበው ህጻናት ወደውጪ የላኩ ኤጀንሲዎች 7000 ህፃናት ያሉበት ደብዛቸው የጠፉ ልጆችን የላኩ ድርጅቶች ተጣርተው ለፍርድ ቀርበው እንዲጠየቁና ወንጀለኛ ሆነው ከተገኙ ያላቸው ንብረት ተሸጦ ለወላጆቻቸው ካሣ እንዲከፈል፡፡ ‹የጉዲፈቻ አጣሪ ኮሚሲዮን እንዲቆቆም› ከሃገር ውስጥና በባህር ማዶ  ህጋዊ በሆነ መንገድ ህፃናት በጉዲፈቻ የላኩትን ኤጀንሲዎች ምርመራ እንዲደረግባቸው መንግሥት መመሪያ እንዲሰጥ ያስፈልጋል፡፡ ያለ ፕሬስ ነፃነት የጉዲፈቻ ህፃናትና የሙስና ወንጀሎች መፍትሄ አያገኝም፡፡

የጉዲፈቻ/ማደጎ ህፃናት ሽያጪ፤ የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግሥት ከማደጎ ህፃናት ሽያጪ የሚያግበሰብሱት የነፍስ ሽያጪ በተመለከተ በብዙ ጥናቶች  በመረጃዎች ተደግፎ ተገልጾል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ 70 የውጪ ሃገር የጉዲፈቻ ኤጀንሲዎች በሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር Ministry of Women’s Affairs ፍቃድ ሰጪነት ተመዝግበው በመስራት ላይ ናቸው፡፡ ኅዳር 1/2010ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ መሠረት 25,000 ህጻናት ልጆች  በአማካኝ ከአንድ ሕፃን 20 ሽህ ዶላር ሽያጭ ቢሆን 500,000,000 ዶላር በ20 ብር ምንዛሪ ተመን በ10,000,000,000 ቢሊዮን ብር ህፃናት ተሸጠዋል፡፡ 25,000 ህጻናት ልጆች  በአማካኝ ከአንድ ሕፃን 30 ሽህ ዶላር ሽያጭ ቢሆን 750,000,000 ዶላር በ25 ብር ምንዛሪ ተመን በ18,750,000,000 ቢሊዮን ብር ህፃናት ተሸጠዋል፡፡ በሃገራቶች መኃል የሚከናወነውን የጉዲፈቻ ሥነ-ስርዓት ከሚያቀላጥፉ ድርጅቶች/ ተቆማት መሃክል የጉዲፈቻ ኤጀንሲዎች፣ የግልና የመንግሥት ህፃናት ማሳደጊያ ድርጅቶች፣ ፍርድ ቤት፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የሚመለከታቸው ኢንባሲዎች፣ ማዘጋጃ ቤት፣ ኢሚግሬሽን አውቶሪቲ፣ የፍትህ ሚኒስትር፣ የፖሊስ ኮሚሽን፣ እና የሃገር ውስጥ የመንግስት ባለስልጣናት በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ የጉዲፈቻ ሥነ-ስርዓት ያመቻቹ በዚህ የሙስና የተሠማሩ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የጉዲፈቻ ህፃናት የተሸጡ ሰባት ሽህ ህፃናቶች የት እንዳሉ አድራሻቸው እንደማይታወቅ ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ጉዳዮ መቅረቡ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ የእነዚህ የደሃ ልጆች ህይወት ለመታደግ ዘብ የቆመላቸው ማንም ኢትዮጵያዊ አልተገኘ፡፡ የባህር ማዶና የሃገር ውስጥ ጋዜጠኞቻችን በናይጀሪያ ቦካሃራም ያገታቸውን 300 ሴት ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ዜና ሲናኝ የኛዎቹ ማፈሪያ 7000 ህፃናቶች ሽያጭና አድራሻቸው መጥፋት ቁብም አልሰጣቸው!!! የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግስት፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የሚመለከታቸው ኢንባሲዎች፣ ኢሚግሬሽን አውቶሪቲ፣ የፍትህ ሚኒስትር፣ የፖሊስ ኮሚሽን፣ እና የሃገር ውስጥ የመንግስት ባለስልጣናት በህይወት ይኑሩ ይሙቱ ለእናቶቻቸው የማወቅ መብታቸው ተጥሶል፡፡ የእናቶቻቸው እንባ መሬት ያንቀጠቅጣል፣ መቅስፍት ያመጣል፣ መንግሥትና ህብረተሰቡ እጅ በኃጢዓትና ወንጀል የተበከለ ሆኖል፡፡ የእናቶቻቸው እንባ ከሩቅ ይጣራል! የሰው ያለህ! የፍትህ ያለህ! የልጅ ያለህ! እያለ ይጮሃል፡፡

በኤርትራ እናቶች በደርግ ዘመን የታሰሩ ልጆቻቸው ፍለጋ፣  በህይወት ይኑሩ አይኑሩ ሳያውቁ፣ የት እንዳሉ ሳይገለፅላቸው ከአገር ሃገርና ከእስር ቤት እስር ቤት ለአመታት ሲንከራተቱ ቆይተው፣ ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዩርጊስ ለእናቶቹ መልስ በመስጠት የሞተውን በማርዳት፣ የታሰረውን ቦታውን በመጠቆም የእናቶችን እንባ በማበሳቸው በኤርትራ እናቶች ዘንድ በበጎ ተግባራቸው ሲታወሱ ይኖራሉ፡፡  ዶክተር አብይ አህመድ ለእነዚህ ሰባት ሽህ የተሸጡ ህፃናቶች እናቶች መልስ ይሰጡአቸው ዘንድ እናቶቹ በእናትዎ  ስም ቃል እንዲገቡላቸው ይለምናሉ፡፡ ህፃናቶቹ የት እንዳሉ፣ መኖርና አለመኖር ለእናቶቻቸው መልስ ያልሰጠ ትውልድ  በልጆቹ ነግ በኔ ብሎ ንስሃ መግባት ይጠበቅበታል፡፡  ጆን ዶን ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት ‹‹ ማንም በራሱ ደሴት ሊሆን አይችልም፡፡›› ሁላችንም የአኅጉሩ ቁራጭ- የዋናው ክፋይ ነን፡፡ የማንም መወገድ፣ የማንም መገለል -የማንም ሞት ይጎዳኛል (diminishes me) ምክንያቱም የሰው ልጆች ጉዳይ ሁሉ ያገባኛልና›› ብሎ ጮኃል፡፡ የኢትዮጵያዊያን ሕልም  ለማወቅም ሆነ ለመቅረፅ ከፈለግን ትክክለኛው ግንዛቤና አቅጣጫ ይህ መሆን ያለበት ይመስለኛል፡፡››አቶ ሙሉጌታ ሉሌ ከ22 አመታት በፊት ከፃፍት የተቀነጨበ፡፡

 

የህፃናት ጦር ሰራዊት (ማንጁስ) (child soldiers) የጦር አበጋዞቹ የማንነት ጥያቄን በመገንባት ረገድና አዲስ የማንነት መታወቂያ የህፃናት ጦር ሰራዊት በመመሥረት አሊያም ጎልማሳ የጦር ሠራዊት በመገንባት ጥንታዊውን የቤተሰብ ምስረታና የቤተሰብ ፍቅር በማጥፋት ለጦር አበጋዞቹ ብቻ ታማኝ፣ታዛዥና ውጤታማ ሠራዊት  ለመገንባት አስችሎቸዋል፡፡ ጥንታዊው የህብረተሰብ ግንኙነቶችና  የቤተሰብ ፍቅር ማጣትና መቆረጥ ውጤት ነው፡፡(ማኪንሌይ፣2007፣ገፅ 58) Warlords can also use identity construction in order to create new identities with warrior names for child soldiers or adult soldiers who are recruited to their networks as if to throw off the ties of family tradition. This reconstruction of identities is thought to make them less responsible for terrible conducts and more effective fighters, as their traditional social context is cut off (MacKinlay, 2007, p.58). The media has produced several stories about these young soldiers with new warrior names who often dress up in attires like wigs and gowns to further distance themselves from their former social identity and context: የጦር አበጋዞቹ ሕፃናቱንና ጎልማሶቹን ዋርዲያና ዘበኛ በማድረግ ወርቃማ ዘመናቸውን፣ የትምህርት ቤት ግዜቸውን እንዲያጠፉና በጦርነት ሜዳ ውሎ ባዩት የስነልቦና ጠባሳና ለአካለ ጎዶሎነት ይዳረጋሉ፡፡ የጦር አበጋዞቹ ሕፃናቱንና ጎልማሶቹን ቀይ እንባባ፣ቀይ እንቡጦች፣ ብረቱ ወጣት (The iron youth)፣ ማንጁስ በሚል ስም ለአቅመ አዳምና ሄዋን ያልደረሱ ህፃናትን ለወታደርነት ይመለምላሉ፡፡ የጦር አበጋዞቹ የማንነት ጥያቄን በማደል በኢትዩጵያውያን ዜጎች የመታወቂያ ወረቀት ላይ clan identification የዘር ሃረግ (አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግራይ፣ ወዘተ) በማለት ዘውጌ ብሄርተኛነትን በመፈብረክና ኢትዩጵያዊ ብሄርተኛነትን በማዳከም ታሪክ የማይረሳው በደል ፈፅሞል፡፡ የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግሥት በ27 ኣመታት የግፍ አገዛዝ ዘመኑ 25 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ህፃናቶች በባህር ማዶ አገራቶች ውስጥ ተሸጠዋል፡፡ ይሄን ግፍ የፈፀሙ ባለሥልጣኖችና ሹሞች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው እንላለን፡፡

የአሜሪካ ዓለም ዓቀፍ ስታፍ ቦኒ ዊስት ፎል እና አምበር ሊዊስ በአመት 600 ህፃናቶችን አሜሪካ ካለው የኢትዮጵያ ኢንባሲ ሠራተኞች በጉዲፈቻ የመጡ ህጻናትን በመረከብ ለወላጆቻቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡ እባካችሁ በፀሎታችሁ አስታውሶቸው….

600 +Ethiopia Self-reports delivered! By America World (October12,2018)

“America World staff, Bonnie westfall & Ammber Lewis, delivered over 600 Ethiopia Annual self-report to the Ethiopian Embassy staff was grateful to receive the Ethiopian adoption reports and impressed with how many there were. A big thank you to all the families who submitted them! Please continue to pray with..”

 

የኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ጉዲፈቻ አገደች!!! ዘጋች!!! የኢትዮጵያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ወደ ባህር ማዶ አገራት በማደጎነት የሚሰጡ ህፃናት አገደች፡፡ በኢትዮጵያ 4.3 ሚሊዮን ህፃናቶች እናትና አባታቸውን በሞት እንዳጡ ዘግበዋል፡፡ ህጻናቶች በድህነት የተነሳ በመንግሥትና በግል የህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ እንደሚኖሩ ተገልፆል፡፡

Ethiopia adoption closed to international adoption (January 9, 2018) 

“On January 9, 2018 the Ethiopia government made the decision to ban international adoption from Ethiopia. Unfortuately, this country that is about twice the size of Texas has an estimated 4.3 million orphans. The children are primarily orphaned due to poverty, and live in both government-run and privately established orphanages. The need is great in Ethiopia. There are many children in …”

 

የህግ የበላይነት ይከበር!!!

ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው!!!

‹‹ ሙሰኛ ሲሰባ፣ ብር ይልሣል!!! ››

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.