ሰበር ዜና.. ዳኛ ብርቱዋ ብርቱካን ሚዴቅሳ እና የሰብአዊ መብት ተከራካሪ አቶ ዳንኤል በቀለ ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዛሬ ከሕወሓት አገዛዝ ነፃ ወጥቷል

የቀድሞው የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አማካሪ፣ የሂውማን ራይስት ዋች የአፍሪካ ዳይሬክተርና ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ የህሊና እስረኛ የነበረው አቶ ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹሟል።

በዚህ ጉዳይ ዶ/ር አብይ መመስገን አለባቸው፨ በመጀመሪያ “Inhuman” የሆነውን የሰብዐዊ መብት ኮሚሽነር ከማይገባው ቦታ በማንሳታቸው ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ በቦታው ላይ በጣም ተገቢውን ሰው መሾማቸው በጣም አስደሳች ነው፨

ዛሬ ሃገሬ በጣም ቀንቷታል! የሰብዐዊ መብት የመብቶች ሁሉ ቁንጮ የሚመስለኝ እኔ ይህን ዜና ስሰማ በጣም ነው ደስስስ ያለኝ በእውነት ! ደህና ቀን የመምጣት ፣ጎህ የመቅደድ ምልክቶች እያየን ነው፨ የሰው ልጅ ክቡርነትን ማወቅ የእድገት መጀመሪያ ፣የሰውነት ዋና መለኪያ ነው፨ መጨረሻችንን ያሳምርልን

መስከረም አበራ

2 COMMENTS

  1. Great news ! Nobody with his her right mind questions both the capability and personal character of Birtukan !
    But slow down and follow things carefully whether the system of EPRDF let her exercise her would be position and responsibility in the real sense of independence or otherwise. Not to be actively or critically watchful whether the appointments of some public figures such as Birtukan is just painting EPRDF’s reform (not fundamental change of its very system ) with attractive flavor in order to deceivingly make the people happy and supportive of its victory in the upcoming election . This is not conspiracy theory or any kind of pessimism . It is to argue that in a political situation that is characterized by almost the total silence and dullness with regard to creating a national platform of dialogue and meaningful conversation at which all stake holders should take active and decisive participation, appointing individuals here and there will never make the process move towards the realization of a fundamentally qualitative democratic society as it should be. SO, I do think we should not be victims of political excitement or amusement any time and any where we see or hear certain events (steps) being taken by EORDF . I know these days we wittingly or unwittingly seem to believe in a very distorted narration of “it is not EPRDF but it is Dr Abyi and his close associates ” . I hate to say but I have to say that this kind illusion and delusion will be one of the self-defeating factors . So, calm down , think big , think and talk about issues of critical importance .
    I strongly believe that it is the way it should be!

  2. በእኔ እምነት የኢትዮጵያውያን መከራ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያበቃ ዘንድና ኢትዮጵያን በቃሉ መሠረት ከእንግዲህ እስከ ወዲያኛው ሊባርካት ሲል ፈጣር/ ሀያሉ አምላክ በጠ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ ፣ በዶ/ር ለማ መገርሳ ፣ በም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን እና በዶ/ር ገዱ አንዳርጋቸው ተመስሎ መጥቷል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.