በብርቱካን መመረጥ ቅር የሚላቸው በግርግር ስልጣን መያዝ የሚሹ የድንገቴ ፖለቲከኞች ብቻ ናቸው (ስዩም ተሾመ)

እንሆ… #ፍትህ እና #ምርጫ በሃቀኛ ሰዎች እጅ ላይ ወደቀ፡፡ #ቃለ_መህላ የምትፈፅመዋ ሴት የፍትህን ትርጉም፣ የምርጫን ፋይዳ ከማንም በላይ ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ እውነት ለመናገር ወ/ሪት #ብርቱካን_ሚደክሳን ስለ ፍትህ ምንነት ለማስረዳት የሞራል ብቃት ያለው፣ ስለ ህዝብ ድምፅ መከበር ከእሷ ፊት ቆሞ የሚደሰኩር ደፋር ያለ አይመስለኝም፡፡ የህወሓት ፋሽስታዊ ስርዓት ለሁለት ተከፍሎ እርስ በራሱ ሊባላ አንዱ ሌላውን ሲያድን ህግ ይከበር ያለች፣ ዳኛ ሆና ስትሾም ለራሷና ለህዝብ የገባችውን ቃል ጠብቃ የጨቋኞችን ግብዝነት እና ጉልበት በህግ የዳኘች ፅኑና ታማኝ ሰው ነች፡፡ “ቃል የእምነት ዕዳ ነው!” ብላ ራሷን ለአውሬዎች አሳልፋ የሰጠች፣ ቃሏን ከማጠፍ ይልቅ መታሰር የመረጠች፣ በዚህም በቃላት የማይገለፅ መከራና ፍዳ የተቀበለች የፅናት እና ሀቀኝነት #ተምሳሌት ነች፡፡ ስለዚህ በብርቱካን መሾም ቅር የሚሰኝ ካለ #የግብሩ_ይዉጣ ምርጫ ማካሄድ የሚሻ፣ በሰሞነኛ ግርግርና ሆይ-ሆይታ የስልጣን ኮርቻ ላይ መፈናጠጥ የሚያልም፤ በነፃ ውይይት እና የሃሳብ የበላይነት ላይ የተመሠረተ ነፃና ገለልተኛ ምርጫ ከተካሄደ ማንም እንደማይመርጠው የሚያውቅ የድንገቴ ፖለቲከኛ ነው፡፡

 

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.