ህግና ስርአት መከበር አለበት! (ነዓምን ዘለቀ ፣ የአግ7 ከፍተኛ አመራር)

የፌደራል መንግስት እና የክልል አስተዳደሮች ስረአተ አልበኞችን ብቻ ሳይሆን በታችኛው እርከን ላይ የሚገኙ የአስተዳደርና የደንነት ባለስልጣናትን ተጠያቂ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ የመኖር፣ የመንቀስቀስ፣ የመናገር፣ የመደራጀት፣ የማደረጀት፣ የመስብሰብ ፓለቲካዊና የሲቪል መብቶች ሙሉ በሙሉ መከበር አለበት። በዚህ ላይ ድርድር መኖር የለበትም፡ ዜጎች በማናቸውም ቦታ ለሚያደርጉት ስላማዊ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ሙሉ ደህነትና ዋስትና መንግስት መስጠት ሃላፊነት አለበት። የመንደር አምባገነነኖችን ማስታመምና ማስተናገድ ለወደፊቱ ጠንቅ ነው።

በእነ ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው ለውጥ አራማጅ መንግስት ባለፉት ስድስት ወራት አየወሰደ በሚገኘው ልዩ ልዩ እርምጃዎች የተገኙና በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚታዩ ተጨባጭ ለውጦች በእጅጉ የሚደነቁና የሚበረታታ ሂደት ቢሆንም፡ ሰረአት አልበኝነት አሁንም እንደነገሰ ነው፣ በስረአተ አልበኞች ብቻ ሳይሆን በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት የዞን፡ የከተማ፡ የወረዳ የአስተዳድርና የደህንነት አካላት ከስረአት አልበኞች ጋር በመተባብር ዜጎች ላይ ድብደባ መፈጸም፣ መዘርፍ፣ ወይንም ወከባ፣ ድብደባና ዝርፊያ ሲፈጸም እርምጃ አለመውሰድ ብቻ ሳይሆን ተባባሪ የመሆንም ሁኔታዎች በልዩ ልዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መከሰታቸው ቀጥለዋል።

ሰሞኑን በጅማና በአሰላ አካባቢዎች የአስተዳደርና የደህንነት አባላት እውቅና አልፎም ትብብር ጭምር በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ የተደረጉት ህገ ወጥ ድርጊቶች የመብት ረገጣ፣ ወከባ፣ ዝርፊያና ድብደባዎች የዚህ የስረአተ አልበኝነትና የክልልና የፌደራል መንግስትና አስተዳድሮች የዜጎችን ደህነት ለመጠበቅ፣ መብቶቻቸውን ለማስከበር አቅም በእጅጉ ማነስ የሚያሳዩ መገለጫዎች ናቸው።

የዜጎችን ደህንነትና መብት የሚረግጡና የሚያስረግጡ የታችኛው የመንግስት እርከን ባለስልጣኖች ተጠያቂ ማድረግ የክልልና የፌደራል መንግስት ሃላፊነት በመሆኑ አነዚህን ድርጊቶች በፈጸሙና ባስፈጸሙት የመንግስት ባለስልጣኖችና ተመራጮች ለህገ-ወጥ ተግባሮቻቸው ተጠያቂ ማድረግ፣ ብሎም ህጋዊ እርምጃ መውሰድ፣ ወደ ህግ ፊት ማቅረብ ካልተቻለ አሁንም እንደቀድሞው ዜጎች የሚደርስባቸው የመብት ገፈፋና ረገጣ ይቀጥላል ማለት ነው።

የፌደራል መንግስታና የሚመለከታቸው የክልል አስተዳደሮች ይህን የሀገሪቱን ሰላምና መረጋጋት፡ የዜጎች ደህነትና መብቶች መጠበቅ እንደ ወሳኝና ቅድሚያ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ አድርገው በመውሰድ እግር በእግር እርምጃ ካልወሰዱ ተመሳሳይ ድርጊቶች እየቀጠሉ ይሄዳሉ፡ እነዚህን ህግና ስርአትን የማሰጠበቅ እርምጃዎች መውሰድ ካለተቻለ ህዝብ ለውጡን እንዳያጣጥም፡ ብሎም ሰላም ፣ መረጋጋት እንዳይሰፍን አልፎም የለውጡን ሂደት ወደ ወደ ሰከነ፡ የተረጋጋና፣ ሰላማዊ ሀገራዊ ከባቢ ለማሸጋገር አዳጋች አየሆነ ይመጣል።

4 COMMENTS

 1. የዐቢይ አስተዳደሩ ፍርሃት ይሁን ወይም ቸልተኝነት ዝምተኛነቱ የሚያሳዝን ነው፡፡ እስከመቼ አስተዳደሩ በነጃዋር አይነት ቅዥታም ጅሌ ተፈርቶ ህገወጥነት እንዲሚቀጥል አይገባኝም፡፡ መንግሥት መኖሩን ያስጠረጥራል፡፡ ህገወጥነት አልባሌነት ነገሮች ተላምደው ወደ ደንብነት ተቀይሮ ይህብረተስብ ቀውስ እንዳንገባ ያሳስባል፡፡የመንደር አዛዡ መብዛትና አንዱ በአንዱ ማመክኛኘቱ ሃላፊነት የሚወስድ ሳይኖር እንዴት ህብረተሰቡ አገር በአገርነቱ እንዲሚያዛልቀን አይገባኝም፡፡የአቢይ አስተዳደር አንድ መላ በፓሊሲም ሆነ በህግ እርምጃ ካልወሰደ ይወል ይደር እንጂ በሃላፊነት ያስጠይቀዋል፡፡

 2. Kuni
  ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ናት ይባላል:: የሚችለውን ገድሎና አውድሞ የህግ የበላይነት በአጭር ጊዜ መተግበር ዐቢይ አሕመድ ( ኮሎኔል) ያጣው አይመስለኝም:: ዐቢይ ግግንድልዩ መሪ ነው:: እጅግ ትልቅ የትእግስት ፀጋ አለው:: ጊዜውን ጠብቆ ሁሉንም ይፈፅማል:: ብዙ የጠበቅሁት ጃዋርም ሲንቀዠቀዥ አሁን እርቃኑን እየቀረ ነው:: ማን ጠበቀ ዐቢይ ይህ ሁሉ ጄኔራል በ8 ወራት አስሮ ለፍርድ ያቀርባል ብሎ? የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ደጀን ከጀርባው ስላለ ማንም ግለሰብ ከፍርድ አያመልጥም::

 3. @Tessema
  ጥሩ መመኘት ጥሩ ነው:: ሆኖም ሚሊየን ቢያስር የህዝብ ደህነትና ሰላም ከሌለ ዋጋ የለውም::::
  የወያኔን ማንቁርት እያነቀ ፍርድ ማቅረቡ ያስደስታል::: ኢትዮጵያ ብትኖር አስቸኳይነቱ ይገባሃል::ወንድሜ ቁጭ ብሎ ቅልበሳ የሚይነፈንፈው ብዙ ነው
  ከምንም በላይ ግን ስላምና ደህ ን ነት በአስቸኳይ!!

 4. ህውሀት ትግራይ ላይ የፈጠረው የዘረኝነት በሽታ በቀላሉ ለመደርመስ ያስቸግራል:: እዚያ የመሸጉት ገዳይና አስገዳዮች ለፍርድ ሲቀርቡ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱት ግጭቶች በሙሉ ያከትማሉ:: የዐቢይ መንግስት ለህዝብ ደህንነት የገንዘብ ኖቶችን ቢቀይር የህውሀትን የዝርፊያና ግድያ ድርጅት እርቃን ያስቀራል:: ይህ እንደ አማራጭ ቢተገበር ያለምንም ግጭት እንዚህን ዘራፊዎች መዘረር ይቻላል:: እኔ ድሮ ኤርትራውያን ህውሀትን አምርረው ሲጠሉ አይገባኝም ነበር:: እባቦች ናቸው ሲሉኝ መልሼ በመከራከሬ ዛሬ ይቆጨኛል:: ከኢትዮጵያ ምድር መፈጠራቸው ይገርመኛል:: ዐቢይ ትእግስት ያስፈልገዋል ጦርነት መጀመር ቀላል ይመስላል ሆኖም ሁሉንም አውዳሚ ነው::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.