እንቦጭን ማጨድ የሚያስችሉ 2 ማሽኖች ተገዙ 

ዓለም አቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማህበር በ10 ሚሊዮን ብር ወጪ 2 የእንቦጭ ማጨጃ ማሽኖች ከነሙሉ መለዋወጫቸው ግዥ መፈፀሙን አስታወቀ፡፡

H-9 905 የተባሉ ከፍተኛ የአረም ማጨጃ ማሽኖች እያንዳንዳቸው 75 የፈረስ ጉልበት ያላቸው ሲሆን 359 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም 10 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎባቸዋል፡፡

ማሽኖቹ በአንዴ 26 ነጭብ 2 ሜትሪክ ኪዩብ አረም ማጨድ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ለማሽኖቹ ግዥ የሚሆነው ገንዘብ በአሜሪካ እና በእንግሊዝ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደተሰበሰበ ማህበሩ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

EBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.