የቀድሞ የስራ ባልደረባውን ፊቱን የፈላ ውሃ ውስጥ የነከረው የስራ ሃላፊ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመስሪያ ቤቱ ፓርቲ ፕሮግራም ላይ እንደ ቀልድ በቀድሞ አለቃው ፊቱን የፈላ ውሃ ውስጥ የተነከረው የ23 ዓመት ወጣት ለማገገም አንድ ወር ያህል ፈጅቶበታል።

የቀድሞ የስራ ባልደረባውን ፊቱን የፈላ ውሃ ውስጥ የነከረው የስራ ሃላፊ 1የወንጀል ድርጊቱ ፈፃሚ እንደ መዝናኛ ቀለል አድርጎ በ23 ዓመቱ ወጣት ላይ የፈጸመው ጥቃት ፊቱ ላይ ከባድ ጠባሳ ማሳረፉም ተገልጿል።

በወጣቱ ላይ ይህ አሰቃቂ ድርጊት የተፈጸመው በፈረንጆቹ ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ሲሆን፥ መረጃው ለህዝብ ይፋ የሆነው እና የወንጀል ድርጊቱ የተጋለጠው በእጅ ስልክ የተቀረጹ 2 የምስልና ድምጽ መረጃዎች በሳለፍነው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወሩ ከቆዩ በኋላ መሆኑ ተነገሯል።

ወጣቱ በጃፓን አንድ የመዝናኛ ኤጄንሲ ተጠቃሪ የነበረ ሲሆን፥ የደርጊቱ ፈጻሚ ደግሞ የኤጀንሲው ፕሬዚዳንት ነው ተብሏል።

ሰሞኑን በማህበራዊ ምዲያዎች ከተዘዋወሩ የድምጽ እና ምስል መረጃዎች በአንደኛው ጉዳቱ በወጣቱ ላይ ያደረሰውን ጠባሳ የሚያሳይ ሲሆን፥ ሁለተኛው ደግሞ ፊቱ የማይታይ ሰው ለሴኮንዶች ያህል ለስጋ ማብሰያ የፈላ ውሃ ውስጥ ወጣቱን ፊቱን ነክሮ ሲያወጣው የሚሳዩ ናቸው ነው የተባለው።

በአካባቢው የነበሩ ሰዎችም ድርጊቱን በመቃዎም ፋንታ ሲሳሳቁ እና ቁጭ ብለው ሲያዩ የነበረ ሲሆን፥ ወጣቱ እየተነከረበት ከነበረው የፈላ ውሃ ጎን ሌላ የተጣደ ነገር ሲያበስል የነበረ ሰው መታየቱም ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ከምን ጉዳይ ጋር በተያያዘ በወጣቱ ላይ ጉዳቱ ስለመፈጸሙ መረጃዎች ያለመገኘታቸው ነው የተገለጸው።

እነዚህን መረጃዎች የጉዳቱ ሰለባ እና ጠበቃው ወደ ፍርድ ቤት መውሰዳቸውም ታውቋል።

የጉዳቱን ሰለባ ጠቅሰው የመገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ወጣቱ የተጣደ ውሃ ባየ ቁጥር የስቃይ ስሜቱ እንደሚያስታውስ ተገልጿል።

ድርጊት ፈፃሚው ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ይህን ኣይነት ጭካኔ የተሞላበት ተግባር ከፈጸመ ቢሮ በርካታ ድርጊቶችን በሰራተኞች ላይ ሊፈጽም አንደሚችል አስተያየት ስጭጪወች ተናግረዋል።

ከጃፓን ብቻ ሳይሆን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የወንጀል ድርጊት ፈፀሚው ለፈረድ እንዲቀርብ ግፊት እየተደረገ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ምንጭ፦ odditycentral.com

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.