በሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) እና በአብይ አህመድ የሚመራው ኦዴፓ (የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ) መዋሃዳቸው እየተነገረ ነው

ከግንቦት 7 ጋር ግንባር ፈጥሮ የነበረው የሌንጮ ባቲው ODFም በቅርብ እንደሚዋሃድ ይገመታል።
ኦዴፓ ሁለት ጊዜ አሸንፏል።

የሆነው ሁኖ የአማራ ህዝብ ተስፋ ነው የምንለው አብን ዙሪያ መለሱን ይመለከት ዘንድ ምኞቴ ነው።ይህ ነገር ተተንትኖ ቢሰራበት መልካም ነው።

አዴፓ በአማራ ስም የተቋቋሙ ፓርቲዎች ጋር ተወያይቶ መቀራረብ ሲገባው እነ ግንቦት 7ን እና ሰማያዊውን ስፖንሰር አድርጎ መጓዙ የውድቀቱ መጀመሪያ ነው ማለታችን ይታወሳል።በዚህም ህዝቡ ለአሰላለፍ ግራ ተጋብቶ ሰንብቷል።አሁንም አጭሩ እና ዘላቂው መንገድ ብሄርተኝነቱ ላይ ብቻ መሰረትንም መገንባት ነው።መደራደሪያው ብሄርተኝነት እንጅ ሀገር መሆን የለባትም።ሀገር መደራደሪያ የምትሆነው ከ80 ብሄር ብሄረሰብ ጋር ስብሰባ ስትቀመጥ ነው።

ኦሮሞ ፖለቲካ ጠርዙን ይዞ በፅኑ መሰረት ላይ ሲጓዝ አዴፓ ግንቦት 7 ለሚባል ምናባዊ ድርጅት ቀይ ምንጣፍ እያነጠፈ ብሄርተኝኑቱ ላይ ውሃ ለመቸለስ ላይ ታች ብሎ ነበር።

ዳሩ ግን አዴፓ ራሱንም ሳይጠቅም ግንቦት 7ንም ሳይጠቅም ተንሳፎ ቀረ።ከዚያም ወደ ጓዳው ዙሮ አጀንዳ ፈጥሮ ሲቧቀስ ሰነበተ (ንዝንዙ ሊቀጥልም ይችላል)።

Ayalew Menber

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.