ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ለአፍሪካ የአመራር መጽሔት የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ሽልማት እጩ ሆነው ተመረጡ

 

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለአፍሪካ የአመራር መጽሔት የየዓመቱ (2018) ምርጥ አፍሪካዊ ሽልማት እጩ ሆነው ተመረጡ፡፡ ሽልማቱ በተለያዩ ዘርፎች የላቀ አስተዋፅዖ ላበረከቱ የአፍሪካ የቢዝነስ፣ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ መሪዎች እውቅና የሚሰጥ ነው፡፡

በየዓመቱ በሚካሄደው በዚህ የሽልማት ዘርፍ የነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ናይጄሪያዊው መሐመድ ሳኑሲ ባርኪንዶ እና የቀድሞው የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ሴሬትሳ ካማ ኢያን ካማ የዶ/ር ዐቢይ ተፎካካሪዎች ናቸው፡፡

የሽልማቱ አሸናፊ የሚለየው በመጽሔቱ ድረ-ገፅ ላይ በኢንተርኔት በሚሰጥ ድምፅ ሲሆን እስካሁን ዶ/ር ዐቢይ 87 በመቶ የሚጠጋውን ድምጽ በማግኘት ተፎካካሪዎቻቸውን እየመሩ ይገኛሉ፡፡ ድምጽ የሚሰጥበት ጊዜም እስከ ታህሳስ 1/2011 ድረስ መሆኑ ተገልጿል፡፡

https://www.satenaw.com/ethiopias-pm-tinubu-others-nominated-african-leadership-magazine-persons-year-2018/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.