አክራሪ ብሄረተኛነትና የሚፈጥረው ከማንኛውም ነገር በላይ ለራስ ነገድ ጭፍን ታማኝነትን የማሳየት ዝንባሌ (በዶክተር አሰፋ ነጋሽ)

በዶክተር አሰፋ ነጋሽ —› የኢሜይል አድራሻ –› Debesso@gmail.com Amsterdam (the Netherlands) – ሀምሌ 7 ቀን 2010 ዓ. ም.

ክፍል ሁለት —-› ከክፍል አንድ የቀጠለ

ብሄረተኛነትና የሚፈጥረው የራስ ነገድ አምልኮ፤ በሁሉም ነገር የእኔ ነገድ ብቻ ይቅደም!!!!! ብሄረተኛነት ከማንም በላይ የራስን ነገድ ተወላጅ ማስቀደምን፤ የራስን ነገድ ከሌላው ሁሉ አብልጦ መውደድን፤ ለራስ ነገድ ማድላትን፤ የራስን ነገድ ማፍቀርን፤ በራስ ነገድ ማንነት ካለ ልክ መኩራራትንና ከራስ ነገድ ውጭ ያሉ ነገዶችን ማንነት ማናናቅን፤ መጥላትን ያስተምራል። በብሄረተኛነት መንፈስ የሚነዱ ሰዎች ከምንም ነገር በላይ ታማኝነታቸውን የሚያሳዩት ለዚያ የእኔ ነገድ ለሚሉት ወገን ነው እንጂ ለእውነት ወይም ለፍትህ ጉዳዮች አይደለም። ብሄረተኛነት ለራሱ ነገድ ጥቅም ታማኝና ሙት መሆንን ተከታዮቹ ለሆኑ የአንድ ነገድ ተወላጆች ያስተምራል። አንድ በብሄረተኛነት ስሜት የተለከፈ ወገን በማናቸውም ጉዳዮች ወገናዊነቱን የሚያሳየው ለዚያ የእኔ ነገድ ለሚለው ህዝብ ነው። አክራሪ ብሄረተኛነት የአንድ ነገድ ተወላጆች የሆኑ ሰዎች ከእነሱ ነገድ ውጭ ባሉ የሌሎች ነገዶች ተወላጆች ላይ የሚያደርሱትን በደል እንደ በደል እንዳያዩ ያደርጋቸዋል። አክራሪ ብሄረተኛነት ፍርደ-ገምድልነትን፤ ከራስ ነገድ ውጭ ላለ ሰው አለመራራትን፤ ከራስ ነገድ ውጭ ያለን ሰው እንደ ሰው ፍጡር አለማየትን ያስተምራል። አክራሪ ብሄረተኛነት የግለሰቦችን ማንነትና ህልውና በሚሸረሽር፤ የግለሰቦችን ህሊና በሚፍቅና በሚያጠፋ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ ስለሆነ አብዛኞቹ በዚህ የአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት ህሊናቸው የታወረ የአንድ ነገድ ተወላጆች የአንድ ዓይነት የአክራሪ ብሄረተኛ የፓለቲካ አስተሳሰብና እምነት ተሸካሚዎች ይሆናሉ። በዚህም ምክንያት በርካታ የአንድ ነገድ ተወላጆች የሆኑ የአንድ አክራሪ ብሄረተኛ ድርጅት ተከታዮች እንደ አንድ ሰው ማሰብ፤ እንደ አንድ ሰው ባንድ ዓላማ ስር መሰለፍ ይጀምራሉ።

በዛሬዋ ኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ የሆነው የወያኔ መንግስት ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ ታሪክ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት በደል በህዝብ ላይ የፈጸመ ቢሆንም አብዛኛዎቹ የዚህ መንግስት ደጋፊዎች የሆኑት የአንድ ነገድ ተወላጆች የዚህን መንግስት አጥፊነት፤ ሀገር አፍራሽነት፤ በሃይማኖትና በነገድ ከፋፋይነት፤ ዘራፊነት፤ ደም-አፍሳሽነት፤ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለባዕዳን አሳልፎ ሰጪነት፤ ጠብ-አጫሪነት፤ ተንኳሽነት ወዘተ ተረድተውና አይተው ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሆነው በተቃውሞ አልቆሙም። እንዲያውም ባብዛኛው የአንድ ነገድ ተወላጆች የሆኑት የዚህ መንግስት ደጋፊዎች ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በተጻራሪነት በመቆም ከማንም በላይ የባለመብትነት ስሜት (strong sense of entitlement) ሲሰማቸው አይተናል፤ ታዝበናል። የወያኔ ትግሬዎች በስፋት ተሰራጭተውና ህይወታቸውን መስርተው በሚኖሩባት ኢትዮጵያ ውስጥ በውዴታም ይሁን የወያኔ መንግስት በሚያደርስባቸው ተፅዕኖ ምክንያት የዚህ መንግስት ዓይንና ጆሮ በመሆን ከስርዓቱ ጋር እጅና ጓንት ሆነው ቆይተዋል። የወያኔ ትግሬዎች የሚለው አገላለጽ የወያኔ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች የሆኑትን እንጂ ሁሉንም የትግራይ ተወላጆች የሚመለከት አይደለም። ይህ ሁኔታ ወያኔ ትግሬዎችን ገና ከጠዋቱ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በጥርጣሬ ዓይን እንዲተያዩ አድርጓቸዋል። ዛሬ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት ስሜት የተለከፉ በርካታ የወያኔ ትግሬዎች፤ ከፓትርያርክ እሰክ ተራ ምዕመናን፤

ከፕሮፌሰር እስክ መሃይሙ፤ ከሃብታሙ እስከ ድሃው፤ ከሼኩ እስከ ተራው ሙስሊም ወዘተ ድረስ የሚገኙበት ሁኔታ ይህ ነው። አብዛኞቹ የወያኔ ትግሬዎች ከወያኔ ስርዓት ጀርባ በመቆም ለስርዓቱ ያላቸውን ድጋፍ በጭፍነነት ሲገልጹ የምናያቸው በዚህ ምክንያት ነው። ሌላው ቀርቶ ይህችን ዓለም ንቀው ዋልድባን የሚያኽል እጅግ ታላቅ የሆነና የተከበረ የመናኞች ገዳም ውስጥ የገቡ አንዳንድ የትግራይ መነኮሳት ጭምር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው የወያኔ መንግስት የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ ይዞታ የሆነውን ሰፊ መሬት ወደ ትግራይ ክልል ከልሎ ይህንን የገዳሙን መሬት ለሸንኮራ አገዳ ማብቀያ (አዲስ ለተቋቋመው የስኳር ፋብሪካ) የሰጠበትን ህገ-ወጥ ድርጊት በአደባባይ ሲደግፉ ታይተዋል። አክራሪ ብሄረተኝነት እንኳን የምድርን ደስታ የሚመኘውን የዚህ ዓለም ሰው ቀርቶ ይህቺን ዓለም እንኳን ንቆና እንደ ሞተ ሰው ተቆጥሮ በቁሙ ፍታት ተደርጎለት፤ ተዝካር ወጥቶለት ዋልድባ ገዳም የገባውን የትግራይ መነኩሴ ጭምር ህሊና-ቢስና ይሉኝታ-ቢስ አድርጓል።
አክራሪ ብሄረተኛነት ምንድነው? ተከታዩቹ የሆኑ የአንድ ነገድ ተወላጆችንስ እንዴት ይቀይራቸዋል? አክራሪ ብሄረተኛነት የአንድ ነገድ ተወላጆች እንደ መንጋ (human crowd) መሪያቸውን በጭፍን እንዲከተሉ የሚያደርግ ጽንፈኛ የፓለቲካ እንቅስቃሴ (extremist political movement) ውስጥ
ይከታል። የአንድ የአክራሪ ብሄረተኛ ድርጅት ወይም የፓለቲካ እንቅስቃሴ ተከታይ የሆነ ሰው የኔ ነገድ ወይም የኔ ህዝብ ለሚለው ህዝብ ከልክ ያለፈ ፍቅር ያሳያል። በዚያው ልክ ከእሱ ነገድ ውጭ ላሉት፤ አብረውት ለሚኖሩት የሌሎች ነገዶች ተወላጆች ከፍተኛ ጥላቻንና ንቀትን ያዳብራል፤ ያሳያልም። የአንድ አክራሪ ብሄረተኛና ጽንፈኛ መንግስት ወይም ድርጅት ደጋፊ የሆነ ሰው የእሱ ነገድ ተወላጆች በማናቸውም የሰውነት/የሰብዓዊነት መለኪያዎችና መመዘኛዎች ከሌሎች ነገዶች ተወላጆች ሁሉ የበላይ እንደሆኑ በእርግጠኛነትና በሙሉ ልብ ያምናል። የአንድ አክራሪ ብሄረተኛ እንቅስቃሴ ድርጅት ወይም መንግስት ተከታዮች የሆኑ የአንድ ነገድ ተወላጆች ሌሎችን ከእነሱ ነገዶች ውጭ የሆኑ ሌሎች ነገዶችን እጅግ አድርገው የሚንቁና የሚጠሉ ይሆናሉ። ይሄ ስለ አክራሪ ብሄረተኞች ባህርያት የምገልጸው ጉዳይ ዛሬ በተቃዋሚነት የተሰለፉ በአንድ ነገድ ማንነት ላይ የሚያጠነጥን አክራሪ ብሄረተኛነትን የሚያራምዱ ድርጅቶችንና ደጋፊዎቻቸውንም ይጨምራል። አንድ አክራሪ ብሄረተኛ ማናቸውንም የእሱ ነገድ ተወላጅ የሆነ ሰው በሌሎች ነገዶች ተወላጆች ላይ የሚፈጸመውን የክፋት ድርጊት፤ ድርጊቱ ምንም ያህል አስከፊም ቢሆን እንኳን ቢሆን በአዎንታዊነት ያየዋል። በተቃራኒው አንዳንድ አክራሪ ብሄረተኛ የሆነ የአንድ ነገድ ተወላጆች ከእሱ ነገድ ውጭ ያሉ በጠላትነት የሚታዩ የሌሎች ነገዶችን ተወላጆች ድርጊቶች በጎነት እንኳን ቢኖራቸው በአሉታዊ መነጽር ያዩዋቸዋል። በአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት የተለከፉ የአንድ ነገድ ተወላጆች እነሱ እንደ ደመኛ ጠላት አድርገው የሚያዩዋቸውን የሌሎች ነገዶች ተወላጆች ሲጎዱ አንዳችም ዓይነት የጸጸት ስሜት አይሰማቸውም። በአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት የተለከፉ የአንድ ነገድ ተወላጆች በሌሎች ነገዶች ላይ የክፋት ድርጊቶችን ሲፈጽሙባቸው እነሱ በሌሎች ነገዶች ተወላጆች ላይ በሚፈጽሟቸው የክፋት ሥራዎች ምክንያት ምንም ዓይነት የእፍረት፡ የሀዘኔታም ሆነ የጸጸት ስሜት አይሰማቸውም። አብዛኛዎቹ የአንድ የአክራሪ ብሄረተኛ መንግስት ወይም ቡድን ተከታዮች እነሱ የእኛ መንግስት ነው የሚሉት ኃይል በሌሎች ከእነሱ ነገድ ውጭ ባሉ የሌሎች ነገዶች ተወላጆች ላይ የሚፈጽመውን ማናቸውም ዓይነት የእብሪት ድርጊት፤ የጅምላ ጭፍጨፋ፤ የዘር ማጽዳት (ethnic cleansing)፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበረሰባዊ፤ ፓለቲካዊና ባህላዊ መድሎዎችን የሚያስፋፉ ፓሊሲዎችን ሁሉ ካለ አንዳች የይሉኝታና የፍትሃዊነት ስሜት ይደግፋሉ። ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የአንድን አናሳ ነገድ ጥቅም በበላይነት የሚያስጠብቁ የአፓርታይድ ፓሊሲዎችን ነድፎ ተፈጻሚ አድርጓል። እነዚህ ፓሊሲዎች ደግሞ ብዙሃኑ የኢትይጵያ ህዝብ የሲዖል ህይወት እንዲመራ አድርገዋል። ይሁን እንጂ በእነዚህ ረጅም ዓመታት አንድም ጊዜ ቢሆን አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጆች በዚህ የአፓርታይድ ሥርዓት ላይ ተቃውሞ አላሰሙም። እንዲያውም በእነዚህ ዓመታት ሁሉ አብዛኞቹ ትግሬዎች (በዝምታቸውም ይሁን ምንም

ባለማድረጋቸው – through silence or inaction) ከዚህ ዘረኛ መንግስት ጀርባ በደጋፊነት ቆመዋል። በዚህ ጽሁፍ ዘረኛ ብዬ ስል በነገድ ተወላጅነት ስሜት ለራስ ነገድ ማድላትን የሚያመለክት ነው እንጂ በትግሬዎችና በሌላው ኢትዮጵያዊ መካከል ቀለምን ወይንም ሥነ-ህያዊ (biological difference) የሆነ የተፈጥሮ ልዩነት አለ ማለቴ እንዳልሆነ ግልጽ ይሁን። እዚህ ላይ አንባቢ እንዴት አብዛኛዎቹ የአንድ አክራሪ ብሄረተኛ መንግስት ወይም ቡድን ተከታዮች የሆኑ ያንድ ነገድ ተወላጆች የሌሎችን ከእነሱ ውጭ ያሉ ነገዶችን ተወላጆች ህልውና ለማጥፋት ቡድናቸው ወይም መንግስታቸው የሚያደርገውን ጥረት ሙሉ በሙሉ ይደግፋሉ ብሎ በመገረም ሊጠይቅ ይችላል? ለዚህ ምላሽ ይሆን ዘንድ የአክራሪ ብሄረተኛነት በአንድ ነገድ ተወላጆች ላይ የሚፈጥረውን ስነ ልቦናዊ ተጽዕኖናና የሚያስከትለውን የስነ ምግባር ለውጥ በክፍል ሶስት ሥር በማቀርበው ተከታታይ ጽሁፌ ይዤ እቀርባለሁኝ።
እስቲ ወያኔ ስልጣን እንደያዘ ከሻቢያና ከሱዳን መንግስት ጋር ተባብሮ በወልቃይት ወረዳውስጥ በሚገኙት የካብትያና የዳንሻ ከተሞች ላይ የፈጸመውን ወታደራዊ ወረራ የጎንደር ልማት ድርጅት በሰኔ ወር 1984 ዓ.ም. በእንግሊዘኛ ቋንቋ ጽፎ አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ለመሳሰሉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ካቀረበው የአቤቱታ መግለጫ ጥቂት ክፍል ከዚህ ቀጥሎ አብረን እናንብብ። “ወያኔና ሻቢያ ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ በእነዚህ ለም ወረዳዎች ላይ የሱዳንን አየር ኃይል ጭምር ያሳተፈ የተባበረ ወታደራዊ ዘመቻ በማድረግ በወልቃይት የሚገኙትን የካትቢያንና የዳንሻን ከተሞች በአውሮፕላን ደበደቡ። ይህ ያስከተለው የንብረት ጥፋት እጅግ ከፍተኛ ነበር። ምንም የማያውቁ ህጻናት፣ ሴቶችና አረጋውያን እጅ እንዳመጣ ተገድለዋል። ከዚህ መዓት ተርፈው ወደ ኋላ ለማፈግፈግ የሞከሩት ተከበው በአሰቃቂ ዓይነት ሁኔታ ተረሸኑ። በክፍለ ሀገሩ ዋና ከተማ በጎንደር የሚኖሩ የሟቾች ዘመዶች እየታደኑ ወደ ወልቃይት እንዲመጡ ከተደረገ በኋላ በአደባባይ ተረሸኑ። በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ሽማግሌዎችና ታዋቂና ሀገር-አውል ሰዎች በአደባባይ ተረሸኑ1” ከእንግሊዘኛው ወደ አማርኛ ተርጓሚው (አሰፋ ነጋሽ)። የወያኔ ትግሬዎች በዚህ ዓይነት ነው ካለፉት 38 ዓመታት ጀምሮ የጎንደር ታሪካዊ ይዞታዎች የሆኑትን ወልቃይትና ጸገዴን በኃይል ወረው ከሰባት መቶ ሺህ በላይ የሚቆጠሩ የታጠቁ የትግራይ ተወላጆችን በእነዚህ ቦታዎች ላይ ያሰፈሩት። ይህንን ያደረጉት ነባሩን ህዝብ በመግደል፤ በማፈናቀል፤ በማሰደድና የእነዚህን አካባቢዎች የህዝብ አሰፋፈር ስብጥር ሥር-ነቀል በሆነ መንገድ በመቀየር (During the last 38 years, the TPLF has radically changed the demographic profile of the Welakit and Tsegede region it annexed to Tigrai) ነው። እስቲ ከላይ በጠቀስኩት መንገድ ወያኔ ትግሬዎች በፋሽስታዊ እብሪት ተነሳስተው ስለወሰዱት የወልቃይትና ጸገዴ መሬት አብርሃ ደስታ የተባለው አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛ የጻፈውን ከዚህ ቀጥለን እናንብብ። አብርሃ ደስታ ይህንን ከላይ የጠቀስኩትን በወያኔ፤ በሻቢያና በሱዳን መንግስት ትብብር የተፈጸመ ጥቃት የረሳ ይመስላል። አብርሃ ደስት ላለፉት ሰላሳ ስምንት ዓመታት ባላሰለሰ መንገድ በወልቃይትና ጸገዴ አማሮች ላይ በህወሃት እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጽዳት ዘመቻ (38 years of incessant ethnic cleansing campaign directed against Amaras of Welkait and Tsegede) ረስቶ ነው ዛሬ የወልቃይትና የጸገዴ ህዝብ ታሪካዊ ይዞታው የነበረው መሬቱ እንዲመለስለት በህጋዊ መንገድ የሚያቀርበውን ጥያቄ ካለ አንዳች እፍረትና ይሉኝታ፤ እንዲያውም እብሪት በተጠናወተው ቋንቋ “የግዛት ማስፋፋት ጥያቄ እንደማያዛልቅ ነገርኳቸው” የሚለን። አብርሃ ደስታ ወልቃይትን በተመለከተ ያቀረበውን አዲሱን ወያኔዊ ትርክቱን ከዚህ በታች አቅርቤዋለሁኝ። “ከአማራ ብሄርተኞች ጋር ያልተግባባሁበት ነጥብ የወልቃይት ጉዳይ ነው። ከእስር ልፈታ አከባቢ “የወልቃይት ጥያቄ” መነሳቱን ነገሩኝ። የግዛት መስፋፋት ጥያቄ እንደማያዛልቅ ነገርኳቸው። አልተግባባንም። ወልቃይትን የጦር ሜዳ ከማድረግ የዘለለ ነገር እንደማይኖረው ነግሬያቸው ተለያየን። የሀገር አንድነት ይቀድማል ከሚል እሳቤ እና ይታረማሉ ከሚል ተስፋ በትዕግስት ለማለፍ ሞከርኩኝ።

1 – Appeal Letter written to Amnesty International by the Gondar Development & Cooperation Organization (GDCO), on the 15th of June 1992.

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አሕመድ ከባህርዳር ሰዎች ጋር ሲነጋገር የተነሱ ጥያቄዎች ስሰማ ተገረምኩኝ። አሁን ደግሞ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጎንደር ሂዶ “ወልቃይት እንደ ካሽሚር” በሚል ርእስ የአማራ አክቲቪስቶች ትግል የነፃነት ሳይሆን የግዛት ማስፋፋት እንደሆነ በግልፅ ቋንቋ አስረድቷል። ዓላማቸው ወልቃይትን የጦር አውድማ በማድረግ ትግራይን ማዳከም ነው። እኔም እላለሁ፤ ወልቃይትን የጦር ሜዳ ማድረግ ይቻል ይሆናል፤ ወልቃይት መውሰድ ግን ከቶ አይቻልም። የየትኛውንም ህዝብ የነፃነት ጥያቄ እደግፋለሁ፤ የግዛት ማስፋፋት ጥያቄ ግን አናስተናግድም። (ትግራዋይ ሕበር ተወደብ!)2። “ትግራዋይ ሕበር ተወደብ” የሚለው የትግርኛ ሀረግ ወደ አማርኛ ሲተረጎም – “ትግራዋይ ንቃ፤ ተደራጅ፤ ታጠቅ” የሚል መልዕክት አለው። ለትርጉሙ ሁሌም ተባባሪዬ የሆነውና በአሜሪካን ሀገር የሚኖረውን ወዳጄን አቶ ጌታቸው ረዳን (የአክሱም ተወላጅ) አመሰግናለሁኝ። የትግራይ ፋሽስቶች ከሃያ ሰባት ዓመት በፊት ሥልጣን ላይ በወጡበት ጊዜ እንዳደረጉት ሁሉ ዛሬም ከሱዳን የጦር ሰራዊት ጋር በማበር ቋራና መተማን በመሳሰሉት ከሱዳን ጋር ድንበረተኛ የሆኑ አካባቢዎች ላይ የሚኖረውን ድሃ የአማራ ገበሬ በከባድ መሳሪያ እየገደሉና እያፈናቀሉ ነው ያሉት።
ከላይ የወልቃይትንና የጸገዴን ህዝብ መከራ ጠቅሼ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ውስጥ የቡድን መብትን የሚያስቀድም፤ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሰብዓዊ መብት የሚጻረር፤ በአክራሪ ብሄረተኛነት ፍልስፍና የተቃኘ የፓለቲካ ሥርዓት ከትግራይ በታች ባሉት የኢትዮጵያ ክፍሎች የብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ህይወት ቀጥፏል። በተጨማሪም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን አፈናቅሏል፤ ቤተሰባቸውንም በትኖ ለጎዳና ተዳዳሪነት፤ ለልመና፤ ለስደትና ውርደት ዳርጓል። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ከስምንት ሚሊዮን በላይ እናትና አባት የሌላቸው ልጆች አሉ። የነገድ ፌዴራሊዝም የፈጠራቸው ግጭቶች፤ የህዝብ መፈናቀል፤ የቤተሰብ መበተን ወዘተ በተወሰነ ደረጃ ለዚህ አባት እናት ለሌላቸው ልጆች ችግር መፈጠር የራሱን አስተዋጽዖ አድርጓል። እስቲ የወያኔን በነገድ ማንነት ላይ የተመሰረተ የፌዴራሊዝም ሥርዓት ውጤቶች ለማሳየት የሚረዱንንና የጥፋቱን ደረጃ የሚያሳዩ ምሳሌዎችን ከዚህ በታች ላቅርብ። የወያኔ መንግስት በፓርላማ ላይ ወጥቶ የ2,400,000 (ሁለት ነጥብ አራት ሚሊዮን) ቁጥር ያለው የአማራ ህዝብ መጥፋቱን (ይህ ቁጥር እስከ አምስት ሚሊዮን ይደርሳል የሚሉ ወገኖች አሉ) አምኗል። ማንነትን መሰረት ባደረገ የነገድ ፌዴራሊዝም ምክንያት አሁን በቅርቡ እንኳን ከቀድሞው የሀረርጌ ክፍለ ሀገር ከክልሌ ለቀህ ውጣ በሚል ምክንያት ከ800,000 በላይ ቁጥር ያላቸው ኦሮሞዎችና ከ200,000 በላይ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሶማሌዎች ተፈናቅለዋል። ከቀደሞው የሲዳሞ ክፍለ ሀገር ከ740,0003 በላይ ቁጥር ያላቸው ጊዴኦዎች እና ከ1780004 በላይ ቁጥር ያላቸው የጉጂ ኦሮሞዎች ተፈናቅለዋል። ከመፈናቀል ባለፈ ደግሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሞተዋል። ከቀድሞው የባሌ ክፍለ ሀገር ከ30,000 በላይ ቁጥር ያላቸው ሲዳማዎች የአክራሪ ብሄረተኛነት ፓለቲካ ውጤት በሆነው የነገድ ማንነትን መሰረት ያደረገ ውዝግብ እናንተ ወደ ክልላችሁ ሂዱ ተብለው ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ተባረዋል። ከጉራ ፈርዳ በትግሬው መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ፤ በሲዳማው ሽፈራው ሽጉጤ አስፈጻሚነት በአንድ ጊዜ ብቻ ከ78,000 በላይ ቁጥር ያላቸው አማሮች5 ተፈናቅለዋል። ከአመያ (ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ውስጥ የሚገኝ ሥፍራ) በወያኔ ትዕዛዝ ሰጪነት፤ በኦህዴድ ካድሬዎች አስፈጻሚነት ከ5000 በላይ ቁጥር ያላቸው አማሮች ቤትና ንብረታቸው ተቃጥሎ ተባረዋል። በ1992 ዓ. ም. ከአስራ ሁለት ሺህ በላይ

2 – አብርሃ ደስታ የተባለው የትግራይ ብሄረተኛና የአረና ትግራይ የፓለቲካ ፓርቲ መሪ በፌስ ቡክ ገጹ በ13th of May 2018 እንደ አውሮፓ አቆጣጠር at 12:19pm ከለቀቀው ጽሁፍ የተወሰደ።
3 – ይህ አሃዝ አቶ ደመቀ መኮንንና አቶ ለማ መገርሳ በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል የተፈናቀሉትን የጉጂ ኦሮሞዎችና የጊዴኦ ተወላጆች የሆኑ የኢትዮጵያ ዜጎች ለመጎብኘት በሄዱበት ወቅት የኢትዯጵያ ቴሌቪዥን አጠናቅሮ በሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ. ም. ካስተላለፈው ዜና የተገኘ መረጃ ነው።
4 – ዝኒ ከማሁ
5 – Assefa Negash, Why Have the Amaras Once Again Become Victims of Ethnic Cleansing by the TPLF? 18th of April 2012

ቁጥር ያላቸው አማሮች በወያኔ ትዕዛዝ ሰጪነት፤ በኦህዴድ ካድሬዎች አስፈጻሚነት ከምስራቅ ወለጋ(ጊዳ ኪራሙ አካባቢ) ቤትና ንብረታቸው ተቃጥሎ፤ የሚጸልዩባቸው ቤተክርስቲያናት በእሳት እንዲጋዩ ተደርጎ፤ በቤት ያለ ንብረታቸው እንዲዘረፍ፤ በማሳ ላይ ያለ ሰብላቸው እንዲቃጠል6 ተደርጎ ከተፈናቀሉ በኋላ፤ የአማራ ክልል ተብሎ በሚጠራውና በአዊ ዞን ውስጥ ጃዊ የተባለ በረሃማ ሥፍራ ላይ ተጥለው ለወባና ሌሎች በሽታዎች እንዲጋለጡ ከተደረገ በኋላ ብዙዎቹ ለሞት በቅተዋል። ከሞት የተረፉትም ቤተሰባቸው ተበትኖ ጎዳና ተዳዳሪዎች ሆነዋል። ቤኒሻንጉል ተብሎ በሚጠራው ክልል ውስጥ ኬላዎች ተቋቁመው በዚያ ኬላ የሚያልፉ የአማራ ሴቶች መታወቂያ አሳዩ እየተባሉ እንዲቆሙ ከተደረገ በኋላ እየተያዙ ይደፈሩ ነበር7። ወያኔ ሥልጣን ላይ እንደወጣ መተከል ይባል በነበረው አውራጃ ዲባ ጤናና ማንዱራ ጉንጉዋ በተባሉ ወረዳዎች ውስጥ የቤኒሻንጉል ነጻ አውጭ ድርጅት በሚባል ኃይል ፈጻሚነት ከስድሳ ሺህ በላይ ቁጥር ያላቸው አማሮች ሲፈናቀሉ፤ ከሁለት መቶ ሰባ በላይ የሆኑት ደግሞ ተገድለዋል። ከዚህ በተረፈም በርካታ ወንዶች ተኮላሽተዋል፤ 6833 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ በእርሻና በጎተራ ያለ እህል እንደዚሁም የቤት እንስሳት (ከብቶች፤ በጎች ወዘተ) ተዘርፈዋል8። ይህን ድርጊት ከኋላ ሆኖ የሚመራው የህወሃት መንግስት ነበር።
እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው አሃዛዊ መረጃዎች በጥቂቱም ቢሆን የወያኔ ትግሬዎች መንግስትበዘረጋው ጥላቻና ልዩነት-ፈጣሪ የሆነ የነገድ ማንነትን መሰረት ያደረገ የፌዴራሊዝም ሥርዓት ምክንያት ከትግራይ በታች ባሉት የኢትዮጵያ ክፍሎች የፈጸመውን መጠነ-ሰፊ የሆነ ህዝብን የማፈናቀል፤ ቤተሰብና ትውልድን የመበተን ድርጊት የሚያሳዩ ናቸው። በነገድ ማንነት ላይ የተመሰረተ፤ ጥላቻ- ወለድ የሆነ ፌዴራሊዝም የወያኔን መንግስት የአፓርታይድ ሥርዓት ህልውና ለማረጋገጥ የተዘረጋ እንጂ ዲሞክራሲን፤ እኩልነትንና የህግ ሥርዓትን በኢትዮጵያ ለማንገስ የሚረዳ እንዳልሆነ ከላይ የጠቀስኳችው መረጃዎች ይመሰክራሉ። እነዚህ ከላይ የዘረዘርኳቸው የጥፋት ድርጊቶች ሁሉ የተፈጸሙት የአንድን ትግሬ የሚባልን አናሳ ነገድ ተወላጆች የጥቅም የበላይነት ለማረጋገጥ ነው። እነዚህ ሁሉ ጥፋቶች አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት የፈጠራቸው የወያኔ ፋሽስታዊ መንግስት ፓሊሲ ውጤቶች ናቸው። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስትነት ደረጃ ራሱን የተከለው ፋሽስቱ የወያኔ ትግሬዎች መንግስት የአንድን አናሳ ነገድ ጥቅም የበላይነት ለማረጋገጥ ሲል የፈጠረው የአፓርታይድ ሥርዓት የሚመራበት ፍልስፍና በይዘቱም ሆነ በተፈጥሮው ታሪክ ከመዘገባቸው የፋሽስት/ናዚ ሥርዓቶች ጋር አንድ አይነት ነው ብዬ እሞግታለሁ። ይህንን ስለ ፋሽዝም/ናዚ ሥርዓት ምንነትና ዛሬ በሥልጣን ላይ ካለው የወያኔ መንግስት ጋር ስላለው ዝምድና በቅርቡ በማቀርባቸው ተከታታይ ጽሁፎች አሳያለሁኝ። ————————የክፍል ሁለት መጨረሻ————————-

——–› ክፍል ሶስት ይቀጥላል!!!!

6 – Tesfaye Tafesse, The Predicaments of Amara Migrant-settlers in East Wellega Zone, Ethiopia – Proceedings of the 16th International Conference of Ethiopia, 2009 pp. 860
7 – ሙሉቀን ተስፋው – የጥፋት ዘመን፤ ከ1983 -2007 ዓ. ም. በአማራ ህዝብ ላይ የተፈጸመ የዘር ማጽዳት – ሃምሌ 2008 ዓ. ም. የታተመ መጽሃፍ
8 – የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ (ኢሰመጉ) ሶስተኛ ሪፓርት፤ ሃምሌ 9 ቀን 1984 ዓ. ም.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.