እነገዱ አንዳርጋቸው አሜሪካ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል – Video

በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው ልዑካን ቡድን በዋሽንግተን ዲሲ ሲገባ በኢትዮጵያዊያን ዘነድ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። በአሜሪካ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና ትዉልደ ኢትይጵያዊያን ጋር ለመነጋገር ወደ አሜሪካ የመጣው የልኡካን ቡድን ከሁለት ወራት በፊት ከነ ዶ/ር አብይ ጋር ሊመጣ ታስቢ የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ የብአዴን ከፍተኛ አመራርና በለውጡ ሂደም ትክቅ ሚና ሲጫወቱ ፣  የድብቅ ጀግና ተብለው ይጠሩ የነበሩ አቶ ተስፋዬ ከዚህ አለም በመለየታቸው መክንያት ሳይመጡ ቀርተዋል።

አቶ ገዱ ስለጉዞው ዓላማ ሲናገሩ “የጉዞው ዓላማ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአማራ ልማት ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል ነው፡፡ ለውጡን ተከትሎ በክልሉ መንግስት አቋም ላይ በመወያየት በቀጣይ ስራዎች ላይ አብሮ ለመስራት ያለውን መልካም አጋጣሚ ማሳወቅም ሌላው ዓላማ ነው፡፡” ሲሉ ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው ጉዳይ የበለጠ እንዲሳተፉ ፍላጎት እንዳላቸው ገልሰዋል።

“ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ያላቸውን አንድነት በማጠናከር ታላቅነትን በጋራ የማስቀጠል ስራም ከውይይቱ ዓላማዎች መካከል ነው” ያሉት አቶ ገዱ ይዘውት የመጡት ልዑክ በሰሜን አሜሪካ በሚኖረው ቆይታ በተለያዩ ግዛቶች ኢትዮጵያውያን ጋር ምክክር ጀምረዋል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.