በጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ የተፈጠረው ግጭት ከክልሉ ውጭ ያሉ ሃይሎች እጅ አለበት ተባለ

ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ የተፈጠረው ግጭት ከክልሉ ውጭ ያሉ ሃይሎች እጅ አለበት ተባለ። ይሄንን በተመለከተ አብመዽ የኽልሉን የጸትታ ሃላፊ ጀነራል አሳምነው ጽጌን አነጋገሮ የሚከተለውም ዘገባ አስፍሯል።

‹‹በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት የክልሉ መንግስት እየሰራ ነው፡፡›› የአማራ ክልል የሰላም ደህንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ

ባሕር ዳር፡ሕዳር 25/2011 ዓ.ም(አብመድ) ትናንት በተፈጠረው ግጭት በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡34 ቤቶች ወድመዋል፤6 የእህል ወፍጮዎች ተቃጥለዋል ነው ያሉት ብርጋዴር ጄነራል አሰማነው ጽጌ፤ ጭልጋ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት የክልሉ መንግስት እየሰራ ነውም ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል የሰላም ደህንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ ለአማራ ቴሌቪዥን በስልክ እንደገለጹት ለግጭቱ ምክንያቶች የሆኑት በአካባቢው የሌሎች እጅ እንዳለበትና የቅማንት አስተዳደር ራሱን ለማስተዳደር በህገመንግስቱ የተሰጠውን መብት ላለመጠቅም መፈለጉ ናቸው፡፡

በዚህም የመንገድ መዘጋት እና የሰው መታገት እያጋጠመ ነው፡፡ይህንን ችግር ለመቅረፍ ደግሞ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ስለሆነም የተዘጉ መንገዶችን መክፈት እና የማህበረሰቡን ሰላም መመለስ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎች ዘላቂ የሰላም መፍትሄ እንዲያገኙ የክልሉ መንግስት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ኃላፊው እንደገለጹት ከዚህ በፊትም በአካባቢው ተደጋጋሚ ግጭቶች በማጋጠሙ፣ተሸከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲደረግ መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡

ዛሬ ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ባገኘነው መረጃ መሰረት ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 153 ሰዎች በተጠርጣሪነት ተለይተዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.