ያልተዘገበና የተረሳ የቲፒ  ጉዳይ  -ግሬስ አባተ

ስለ ቴፒ ጉዳይ ለመፃፍ ስነሳ ሀምሌ 2007 ዓ.ም በዚሁ ዞን፤ ከዞን ከተማነት ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ የፃፍኩትን ፅሁፍ ተመልሼ አየሁት፤ ከዞን ከተማነት በተጨማሪ በወቅቱ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረው ነገር የሸካዎች ያልተገደበ ጠቅላይነት አንዱ ነው፤ ይህም ጠቅላይነት ሌሎችን የበይ ተመልካች አድርጓል፡፡ በዚህ ላይ አንዳችም ነገር ባለመሰራቱ ይመስላል በየኪ ወረዳ የሚኖሩ ህዝቦች በዚህ ዞን አንቀጥልም በሚል ጥያቄያቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

እዚህ ላይ በጣም አስገራሚ የሆነው ነገር ከዛሬ 3 አመት በፊት ከተማው የጦርነት ቀጠና በሆነበት ሁኔታም የሚዲያ ሽፋን እምብዛም አላገኘም፤ አሁንም ያለው ነገር ተመሳሳይ ነው፡፡ እርግጥ ነው ከሁለት ቀናት በፊት ኢቴቪ በከፊልም ቢሆን በከተማው ያለውን ሁኔታ ዘግቧል። ይሁን እንጂ በዚሁ ከተማ በዚህ አመት ትምህርት እየተሰጠ አይደለም፣ የሚዛን- ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አካል የሆነው የቴፒ ካምፓስም እስካሁን ተማሪዎችን መቀበል አልጀመረም፣ ሆስፒታልን ጨምሮ በርካታ የአገልግሎት ተቋማት አገልግሎት የማይሰጡበት ሁኔታ ሲፈጠር ቆይቷል። ይህ ሁሉ በሆነበት ሚድያዎች ዝምታን መምረጣቸው አሳፋሪ ነው፡፡

ጉዳዩን ከዚህ ተሻግረን እንድንመለከት የሚያደርገን ከላይ የጠቀስኳቸው ሁኔታዎች ባሉበት የደቡብ ክልል ምክር ቤት ባለፉት ሁለት እና ሶስት ሳምንታት ያደረገውን ስብሰባ ተከትሎ በተለይም በክልሉ ያሉ ጥያቄዎችን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ በዚህ ከተማ ያለውን ጥያቄ አንድም ቦታ አለመጥቀሱ ጉዳዩ ሲስተማቲካሊ ቸል እንደተባለ ያሳያል፡፡ ነገር ግን የመብት ጥያቄው በሰላማዊ መንገድ ቢፈታ ለዞኑም ሆነ ለአከባቢው መልካም ቢሆንም ከራሳቸው ተሻግረው ማሰብ የማይችሉ የዞኑ አመራሮች ጠቅላይነታቸውን ላለማጣት እና የዘረጉት የጎጥ መዋቅር እንዳይፈርስ ዛሬም እየተፍጨረጨሩ ነው፡፡

በመጨረሻም ለዚህ የመብት ጠያቂዎች የምለው ነገር ጥያቄያቸው ተገቢና የሚደገፍ ቢሆንም በከተማው እየሆነ ያለውን ነገር የተቃውሞ መገለጫ አድርገው መመልከታቸው ትክክል አይደልም፡፡ የአገልግሎት ተቋማት አገልግሎት ባለመስጠታቸው የመጀመሪያው ተጎጂ የከተማው ህዝብ ነው፤የመማር ማስተማር ሂደቱ በመቋረጡ በርካቶች ቤት እንዲቀመጡ ሆኗል፣ሌሎችም ከከተማው በመውጣት በችግር ለመማር ተገደዋል፣ሆስፒታሎች አገልግሎታቸው ሲቋረጥ ተስተውሏል፣መንገዶች ተዘግተዋል፤የዚህ መብት ጠያቂዎች ይህንን እንዲቀጥል መፍቀድ የለባቸውም፡፡ ከዚህም ተሻግረው ጥያቄያቸውን በተደራጀና ስልጡን በሆነ መንገድ መቀጠል አለባቸው፡፡

1 COMMENT

  1. ወቅቱ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረው ነገር የሸካዎች ያልተገደበ ጠቅላይነት አንዱ ነው፤ ይህም ጠቅላይነት ሌሎችን የበይ ተመልካች አድርጓል፡፡ That might partially be the case if you don’t consider the human rights violations perpetrated against the SHEKACHO people by the ruling party. As has happened in the rest of the country, if one is a member of the ruling party or has a connection all doors are open.
    The recent wave of violence including killings and evictions directed at the SHEKACHO children, women and men who, just as anyone else minding their own miserable lives was perpetrated by individuals and their descendants who settled in the area because they were victims of drought and those who came to work as daily laborers in the plantations. I agree to the fact that they outnumber the indigenous population,which necessitates some sort of recognition and representation But when they start burning houses and evicting the indigenous SHEKACHO without any cause, they lose let alone legal, any moral ground it is because of their fundamental rights. It is rather a complete racism- hegemony other people.
    As to the media blocked, it has been the voices of the SHEKACHO people that is being silenced. There is ESAT that is providing propaganda coverage that re-victimizes the SHEKACHO people as a group of violent individuals going after other people in the area

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.