ሰባት የፖለቲካ ድርጅቶች ዉህደት ሊፈጥሩ ነው

በዉጭ አገር ይንቀሳቀሱ የነበሩ አምስት፣ በአገር ቤት የሚንቀሳቀሱ ሁለት ድርጅቶ ተዋህደው አገር አግቀፍ ድርጅት ለመመስረት ተሰማምተዋል።  ድርጅቶቹ አገር ውስጥ የሚገኙት  የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት (ኦሞ ህዝቦች) እና የኢትዮጵያ ራእይ ፓርቲ (ራእይ) እንዲሁም በዉጭ ያሉ የኢትዮጵያ መድህን ሞክራሲያዊ ፓርቲ (መድህን)፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክርቤት (ሽግግር)፣ ብሩኅ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብሩኅ)፣ ቱሳ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ቱሳ) እና ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ (ኢትዮጵያችን) ናቸው።

የድርጅቶቹ የመግባቢያ ሰነድ ከዚህ በታች ስፍሯል።

7 ፖለቲካ ድርጅቶች የጋራ ግንዛቤ፣ የመግባቢያና የውሣኔ ሰነድ

፩ኛ. መግቢያ፡-

የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣኑ ባለቤት ለመሆን ሳይመርጣቸው በላዩ ላይ ከተቀመጡ መንግሥታት ጋር ያልተቋረጠ ትግል እንዳደረገና አሁንም እየታገለ መሆኑ ይታወቃል። የሥልጣኑ ባለቤት ያልሆነ ሕዝብ ሉዓላዊነቱን ማስከበር አይችልም። ሕዝብ የሉዓላዊነቱ ባለቤት ባልሆነበት አገር ደግሞ መብቶቹ የሚከበሩበትና በሚመርጠው መንግሥት ለመተዳደር የሚያስችለውን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ማግኘት ይቸገራል።

የህወሓት-መሩ የኢሕአዴግ መንግሥት ባለፉት ሃያ-ሰባት ዓመታት፣ በተለይም ድኅረ-ምርጫ-ዘጠና-ሰባት በተከተላቸው ደፍጣጭ ፖሊሲዎች ለመብቶቹ መከበር ጥያቄ ባቀረበው ሕዝብ ላይ በወሰዳቸው አረመኔአዊ የጉልበት እርምጃዎች ምክንያት ሁኔታዎች እየተባባሱ የአገር አንድነትንና ሰላምን የሚያናጋ ከፍተኛ ሥጋት ማስከተሉ ይታወቃል።

በተለያዩ የአደረጃጀት ዘይቤዎች የተቋቋሙ የፖለቲካ ድርጅቶች ለዜጎች እኩልነት፣ ለፍትኃዊ ሥርዓትና ለአገራዊ አንድነት ሲታገሉ መቆየታቸውና አሁንም በመታገል ላይ መሆናቸው ግልጥ ነው። በተለይም ጎጠኛና ሕዝብ-ከፋፋይ የፖለቲካ ፍልስፍናን የአገዛዙ መርሆ ያደረገው ሕወሓት/ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ የታገሉና በመታገል ላይ ያሉ ድርጅቶች ቁጥራቸው የበዛውን ያህል ዓላማና ግባቸውም እንዲሁ የተለያዩ መስመሮችን የያዙ በመሆናቸው በአገራችን የፖለቲካ መድረክ በአጠቃላይና በተለይም አገዛዙን በሚቃወመው ጎራ በኩል ያለው የኃይል አሠላለፍ በብዥታ የተናጠና ስብጥርጥሩ የወጣ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

ለለውጥ የቆመው ኃይል በሚከተለው ውጥንቅጡ የወጣ የኃይል አሠላለፍ አገዛዙን አስገድዶ ወደ ድርድር ለማምጣትም ሆነ የሚከተለውን አፍራሽ ፖሊሲ እንዲቀይር በቂ ጫና ለማድረግና አልፎም በመታገል ላይ ላለው ሕዝብ ሁነኛ አማራጭ መሆን እንዳይችል አድርጎታል። ያም በመሆኑ የአገራችንን ችግሮች ከመባባስ ለማስቆምም ሆነ ሕዝብ የሚከፍለውን ክቡር መስዋዕት የሚመጥን ውጤት ማስገኘት አልተቻለም።

ሕዝብ ላለፉት አያሌ ዓመታት ባደረገው መራር ትግል በተለመደው የእብሪት መንገድ መቀጠል ያልቻለው የኢሕአዴግ አገዛዝ ከወራት በፊት በውስጡ የአመራር ሽግሽግ ማድረግ ተገድዷል። በዚኽ ሂደት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ተክተው ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን በተረከቡበት ጊዜ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ካደረጉት ንግግር ጀምሮ የወሰዷቸው አዎንታዊ እርምጃዎች በአገራችን ላይ አንዣብቦ የነበረውን ከፍተኛ አደጋ ማርገብ አስችሏል።

ይህ የለውጥ ጅማሮ መልክ ይዞ እንዲቀጥል፤ የሕዝብን ጥያቄዎች በየደረጃቸው መመለስ እንዲቻልና እንዳይቀለበስ ጠንካራ ተፎካካሪ ኃይል ያስፈልጋል።

ከትግል ተምክሯችንና ሕዝባችን ከፖለቲካ ድርጅቶች ከሚጠብቀው አደረጃጀት የወደፊት ጉዞአችን ከሚጠይቀን አካሄድ አንፃር ተመሳሳይነትና ተቀራራቢ የፖለቲካ ዓላማ፣ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ኘሮግራምና የትግል ስልት ያላቸው ድርጅቶች በተናጠል ሳይሆን በጋራ፣ በአንድነት ተደራጅተው ቢታገሉ ከሕዝቡ ጋር በመሆን ወደ አለሙት ግብ ለመድረስ የተሻለ አማራጭ ነው ብለን አምነናል።

፪. የጋራ ግንዛቤ፣

 1. በአሁኑ ጊዜ የተጀመረው የለውጥ አቅጣጫ በአገራችን አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋትን በማስገኘቱ በሕዝብ ዘንድ አዲስ ተስፋን ማሳደሩ፣ የፖለቲካ እስረኞች ጨምሮ ከመፈታታቸው እስከ እንቅስቃሴአቸውን በአብዛኛው በውጭ አገር አድርገው የቆዩ ድርጅቶች በአገራቸው ላይ በይፋ ለመታገል ጥሪ መደረጉ፣ ወዘተ. የሁኔታዎች መሻሻል መታየት መጀመሩ ለበለጠ ለውጥ ሊበረታታ እንደሚገባ፣
 2. የለውጡ ጅማሮ ግን ጠንካራ መሠረት ላይ እንዲቆም መርህን የተከተለና አገርና ሕዝብን ባስቀደመ መንፈስ አስፈላጊው ርብርብ ካልተደረገበት የመቀልበስ አደጋ ሊያጋጥመው እንደሚችል፤ በተለይም ጠንካራና ከማንም የፖለቲካ ወይንም ከብሄር ቁጥጥር ነጻ በሆኑ ብሄራዊ ተቋማት ማለትም የምርጫ ቦርድ፤ ፍርድ ቤት ወዘተ… የተደገፈ ሕዝብን የፖለቲካ ስልጣኑ ባለቤት ለማድርግ ቅድመ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት እንዲቻል፤
 3. በአገራችን ላይ የሥርዓት ለውጥ እንዲኖር እስካሁን ሲታገሉ በቆዩት ድርጅቶች በኩል እያንዳንዳቸው በተናጠል፣ አልፎ-አልፎና በተወሰነ ደረጃም ውሱን በሆነ መልኩ በጋራ፣ የሚቻላቸውን ያህል ጥረት ማድረጋቸው ባይዘነጋም፣ አሁንም በመለወጥ ላይ ላለው ሁኔታ መጣኝና ለሕዝብ አሳማኝነት ያለው አማራጭ ማቅረብ የሚችል፣ ቢያንስ ለሂደቱ አጎልባች አስተዋጽዖ ማድረግ የሚችልበት የኃይል አሠላለፍ ያልያዘ እንደሆነ፣
 4. የዚህ ለውጥ መካከለኛ ግቡ በአገራዊ የሰላምና እርቅ ሂደት ብሔራዊ መግባባት እውን እንዲሆንና ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ለማድረግ አስፈላጊ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደሆነ፣
 5. ይህ እውን የሚሆነውና ተፈጻሚነት የሚኖረው ግን በኢሕአደግ በጎ-ፈቃድ ብቻ ሣይሆን ለሥርዓት ለውጥ ሲታገል የቆየውና የሚታገለው ኃይል ተሰባስቦ እርባና ያለውና ጫና-አሣዳሪ ሚና ሊጫወት እንደሚገባው፣
 6. ለዚህም ተመሳሳይ ዓላማና ግብ ያላቸው ወደ አንድነት መጥተው አስተሳሰባቸውን አንጥረውና አቅማቸውን አጎልብተው ጠንካራ ተፎካካሪ ኃይል መሆን የሚያስችላቸው አደረጃጀት በመያዝ ሁነኛ አማራጭ ሊሆኑ እንደሚያስፈልግ፣
 7. ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጎቿ አገር በመሆኗ በኢትዮጵያ እኩልነትን የሚያረጋግጥና ፍትህን የሚያሰፍን ሕዝባዊ ሥርዓት እውን እንዲሆን አግላይና በታኝ ከሆነ የፖለቲካ ቅኝትና ያንንም መሠረት ያደረገ የፖለቲካ አደረጃጀት ልንቀበለው እንደማይገባ፣
 8. የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ጥያቄ ውስጥ የማይገባና ለድርድር የማይቀርብ መሆኑ፣
 9. አሁን ባለው ሁኔታ ኢሕአዴግ እንደ ድርጅቶች ስብስብ/ግንባር አገራችንን ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመውሰድ አደረጃጀቱና የፖለቲካ ፍልሥፍናው እንደማያስችለው፣
 10. ኢትዮጵያችን ሕዝቧ ሲታገልለትና መስዋዕት ለሆነበት ሕገ-መንግሥታዊ ዴሞክራያዊ-ሥርዓት እውን መሆን የሰከነ የሽግግር ሂደት እንደሚያስፈልግ ተገንዝበናል።

፫. የጋራ መግባቢያና ውሣኔ፤

ዝርዝር ዓላማና ግባችን ወደፊት ይፋ በሚሆነው የፖለቲካ መርሃ-ግብራችን (ፕሮግራማችን) የሚብራራ ቢሆንም፤ የሚከተሉት መሠረታዊ የፖለቲካ መርሆዎቻችን ናቸው።

 1. ሕዝብ የሥልጣን ምንጭና ባለቤትነት፣ የግለሰብ ሁለንተናዊ መብቶች፤ የሕግ የበላይነት፤ የንብረት ባለቤት የመሆን፤ ዜጎች በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ያለ ምንም ገደብና እንቅፋት የመዘዋወር፣ የመኖርና ንብረት የማፍራት እንዲሁም በማኅበራዊ ኑሮና በፖለቲካ ተሣታፊ የመሆን፣ የቋንቋ፣ የባህል፣ የእምነትና የፆታ እኩልነት ወዘተ… መብቶች እንዲከበሩ  የምንታገልላቸው ዓላማዎች ናቸው።
 2. የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣኑ ባለቤት እንዲሆን የምናደርገው ትግል ሠላማዊ እንደሚሆንና የምርጫ ፖለቲካን የምንታገልበት መንገድ መሆኑን አምነንበታል።
 3. በአገር-ውስጥም ሆነ ከአገር-ውጭ ያለው የድርጅቶች ቁጥር ብዛት የሕዝባችንን ትግል ካጓተቱት ምክንያቶች አንዱ መሆኑን ተረድተናል። የድርጅቶች ቅጥ-ያጣ የቁጥር መንዛዛት በተለይም አሁን ላለው አዎንታዊ የለውጥ ጅማሮ ደንቃራ እንደሚሆንም ተገንዝበናል።
 4. በመሆኑም የሕዝባችንን ብሶት በማዳመጥ በአገራችን የተጀመረው ለውጥ ለአስተማማኝ ውጤት እንዲበቃ ለአንድነት፣ ለፍትህና ለእኩልነት የቆምን፣ በፖለቲካ እምነታችንና በአደረጃጀታችን ተመሳሳይነት ያለን፣ ዴሞክራሲያዊና አገር ወዳድ የፖለቲካ ድርጅቶች እስካሁን በተናጠል ስንታገልልት የቆየነውን አገራዊና ሕዝባዊ ዓላማ በተሻለ ለመግፋትና ለውጤት ለማብቃት በማሰብ ባደረግናቸው ውይይቶች ኃይላችንን ማሰባሰቡ አስፈላጊ መሆኑን አምነንበታል።
 5. ለዚህም ድርጅቶቻችንን በአንድ መዋቅር ሥር ለማጠቃለልና፤ በመዋሃድ አንድ ድርጅት መሆን አስፈላጊ መሆኑን ተስማምተናል።
 6. ድርጅቶቻችንን በአንድ መዋቅር ሥር ለማድረግ የውህደት አመቻች ኮሚቴ እንዲሰየም ወስነናል።
 7. የውህደት አመቻች ኮሚቴው ሥራውን እንዳጠናቀቀ ውህደቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን ተስማምተናል።
 8. የሚዋሃዱት ድርጅቶች አጠቃላይ ድርጅታዊ አወቃቀርና የኃላፊነት ምደባዎች፣ የአዲሱ ድርጅት ስያሜና አርማ፣ መተዳደሪያ ደንብና የፖለቲካ ፕሮግራም፣ ወዘተ…  ከጉባኤው በፊት በውህደት አመቻች-ኮሚቴው ለስብስቡ ድርጅቶች ቀርቦና ተወያይተውበት በሙሉ ስምምነት ማጽደቅ ይኖርባቸዋል። በነዚህ በቀረቡ መሰረታዊ ጉዳዮች ያልተስማማ ማንኛውም ድርጅት ይህ የተፈረመ ሠነድ መያዣ አይደለምና እራሱን ከውህደቱ የማግለል ሙሉ መብት አለው።
 9. በውህደቱ መካተት የሚፈልጉ የፖለቲካ ድርጅቶች ሲያመለክቱ በአመቻች ኮሚቴው በሚቀርበውና ስምምነት በሚደረግበት ለአባልነት የሚያበቃ መመዘኛ መሠረት አሟልተው የሚገኙ፣ ይኸን የመግባቢያ ሰነድና ቀደም ሲል የተደረጉ ስምምነቶችን የሚቀበሉ የውህደቱ አካል ሊሆኑ፣ ወይም ውህዱን ፓርቲ ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ ተስማምተናል።
 10. ውህደቱ እውን እስከሚሆን ድረስ ሁላችንም የለውጡ ሂደት እንዳይደናቀፍና መሥመሩን እንዳይስት ድርጅታዊ ኃላፊነታችንን መወጣት የሚያስችሉና ከመግለጫዎች ጀምሮ ባሉና በዝርዝር በሚቀመጡ የሕዝቡን ትግል ለማጠናከር የሚረዱ ተግባራትን በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል።
 11. ውህደቱ እውን እስከሚሆንና አዲሱ ድርጅት (ፓርቲ) እንቅስቃሴውን በመሥራች ጉባዔው በሚፀድቁት ድርጅታዊ ሰነዶች (የፖለቲካ ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ወዘተ…) መሠረት እስከሚጀምር ድረስ፣ በውህደቱ ሂደት የሚሣተፉ ድርጅቶች ህልውናቸው ተጠብቆና በዚህ የጋራ ግንዛቤ ሰነድ ላይ ስምምነት የተደረገባቸውን መርሆኣዊ አቋሞች ባልተፃረረ ሁኔታ እንቅስቃሴዎቻቸውን የመቀጠል መብታቸው የሚከበር መሆኑ ግንዛቤ ተወስዶበታል።
 12. በውህደት የምንመሠርተው ድርጅት የሚያካሂደው ትግል ሕዝብን ማዕከል አድርጎ መቀጠል ስለሚኖርበት፣ እንቅስቃሴው በይፋ በአገር ውስጥ እንዲሆን ወስነናል።
 13. በውህደቱ ሂደት ተሣታፊ የሆኑ ድርጅቶች ውህደቱን ተግባራዊ ለማድረግ በሚድርጉ የጋራ ጥረቶችም ሆነ በውህደት የሚመሠረተው ድርጅት የፖለቲካ ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ወዘተ… የመሣሰሉ ድርጅታዊ ሰነዶችን በማዘጋጅቱ ተግባር ላይ በሚቋቋሙ የተግባር ኮሚቴዎች ውስጥ በወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍና ሥራ ላይ ከመዋላቸው በፊት በሚደረጉ ውሳኔዎች ላይ እኩል ተሣታፊ የመሆን መብታቸው እንደሚከበር፣ የተሰጣቸውን ኃላፊነትም በብቃት የመወጣት ግዴታ እንዳለባቸው ተስማምተናል።
 14. የውህደቱ ተሣታፊ ድርጅቶች በውህደቱ ሂደት በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ የሚያዙ ቃለ-ጉባዔዎች፣ የኢሜይልና የደብዳቤ ልውውጦች፣ በስልክ የሚደረጉ የሃሳብ ልውውጦች፣ ወዘተ… የስብስቡ ምስጢር ስለሆኑ እያንዳንዱ ድርጅት በኃላፊነት መንፈስ ተገቢውን ጥንቃቄ በመስጠት ሊይዝና ሊጠብቅ እንደሚገባ ተስማምተናል።
 15. በውህደቱ ሂደት ማንኛውም በስብስቡ ስም ሆነ ስለስብስቡ በጽሑፍም ይሁን በቃል ለመገናኛ ብዙኃን የሚሰጡና ለሕዝብ ይፋ የሚደረጉ ጋዜጣዊ መግለጫዎች፣ የሂደቱ አባል ድርጅቶችን የጋራ ይሁንታ ያገኙ ሊሆን እንደሚገባ ተስማምተናል።
 16. የውህደቱ ምሥረታ በአገር ውስጥ እንዲሆን ተስማምተናል።

የትብብር ጥሪ፤

ሀ.    በአገራችን የሥርዓት ለውጥ እንዲኖር እስካሁን ስትታገሉ ለቆያችሁና ከላይ በተዘረዘሩት መሠረታዊ መርሆዎችና ግንዛቤዎች ላይ ተመሳሳይ አቋም ያላችሁ ኢትዮጵያዊ የአንድነትና የዴሞክራሲ ኃይሎች የጀመርነው የውህደት ሂደት አካል እንድትሆኑና የሕዝባችን ትግል ለአስተማማኝ ውጤት እንዲበቃ የሚደረገውን ጥረት እንድናጠናክር ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን።

ለ.   በሁኔታዎች አስገዳጅነት በማንንነት ጥያቄ ዙሪያ ለተደራጃችሁና ዓላማና ግባችሁን ለአገራዊ አንድነትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በማድረግ ለምትንቀሳቀሱ ድርጅቶች የትብብር ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን።

እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተመለከተው የድርጅቶች ተወካዮች በድርጅቶቻችን ስምና በተሰጠን ሙሉ ውክልና ይህንን ሰነድ መቀበላችንን በፊርማችን እናረጋግጣለን።

 1. ወ/ሮ ፅጌረዳ ሙሉጌታ፤ የኢትዮጵያ መድህን ሞክራሲያዊ ፓርቲ (መድህን)
 2. አቶ ተሻለ ሰብሮ፤ የኢትዮጵያ ራእይ ፓርቲ (ራእይ)
 3.  አቶ ስለሺ ጥላሁን፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክርቤት (ሽግግር)
 4. ዶ/ር አክሎግ ቢራራ፤ ብሩኅ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብሩኅ
 5. አቶ በርገና ባሳ፤ ቱሳ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ቱሳ)
 6. አቶ ነሲቡ ስብሀት፤ ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ (ኢትዮጵያችን)
 7. አቶ ግርማ በቀለ፤ የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት (ኦሞ ህዝቦች)

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ሀገራችን ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት ታቅፍና ተከብራ በነፃነት ለዘለዓለም ትኑር!!

ህዳር ፲፭  ቀን፤ ፪ ሽህ ፲፩ ዓ/ም   (November 25, 2018)

7 ፖለቲካ ድርጅቶች የጋራ ግንዛቤ፣ የመግባቢያና የውሣኔ ሰነድ

፩ኛ. መግቢያ፡-

የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣኑ ባለቤት ለመሆን ሳይመርጣቸው በላዩ ላይ ከተቀመጡ መንግሥታት ጋር ያልተቋረጠ ትግል እንዳደረገና አሁንም እየታገለ መሆኑ ይታወቃል። የሥልጣኑ ባለቤት ያልሆነ ሕዝብ ሉዓላዊነቱን ማስከበር አይችልም። ሕዝብ የሉዓላዊነቱ ባለቤት ባልሆነበት አገር ደግሞ መብቶቹ የሚከበሩበትና በሚመርጠው መንግሥት ለመተዳደር የሚያስችለውን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ማግኘት ይቸገራል።

የህወሓት-መሩ የኢሕአዴግ መንግሥት ባለፉት ሃያ-ሰባት ዓመታት፣ በተለይም ድኅረ-ምርጫ-ዘጠና-ሰባት በተከተላቸው ደፍጣጭ ፖሊሲዎች ለመብቶቹ መከበር ጥያቄ ባቀረበው ሕዝብ ላይ በወሰዳቸው አረመኔአዊ የጉልበት እርምጃዎች ምክንያት ሁኔታዎች እየተባባሱ የአገር አንድነትንና ሰላምን የሚያናጋ ከፍተኛ ሥጋት ማስከተሉ ይታወቃል።

በተለያዩ የአደረጃጀት ዘይቤዎች የተቋቋሙ የፖለቲካ ድርጅቶች ለዜጎች እኩልነት፣ ለፍትኃዊ ሥርዓትና ለአገራዊ አንድነት ሲታገሉ መቆየታቸውና አሁንም በመታገል ላይ መሆናቸው ግልጥ ነው። በተለይም ጎጠኛና ሕዝብ-ከፋፋይ የፖለቲካ ፍልስፍናን የአገዛዙ መርሆ ያደረገው ሕወሓት/ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ የታገሉና በመታገል ላይ ያሉ ድርጅቶች ቁጥራቸው የበዛውን ያህል ዓላማና ግባቸውም እንዲሁ የተለያዩ መስመሮችን የያዙ በመሆናቸው በአገራችን የፖለቲካ መድረክ በአጠቃላይና በተለይም አገዛዙን በሚቃወመው ጎራ በኩል ያለው የኃይል አሠላለፍ በብዥታ የተናጠና ስብጥርጥሩ የወጣ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

ለለውጥ የቆመው ኃይል በሚከተለው ውጥንቅጡ የወጣ የኃይል አሠላለፍ አገዛዙን አስገድዶ ወደ ድርድር ለማምጣትም ሆነ የሚከተለውን አፍራሽ ፖሊሲ እንዲቀይር በቂ ጫና ለማድረግና አልፎም በመታገል ላይ ላለው ሕዝብ ሁነኛ አማራጭ መሆን እንዳይችል አድርጎታል። ያም በመሆኑ የአገራችንን ችግሮች ከመባባስ ለማስቆምም ሆነ ሕዝብ የሚከፍለውን ክቡር መስዋዕት የሚመጥን ውጤት ማስገኘት አልተቻለም።

ሕዝብ ላለፉት አያሌ ዓመታት ባደረገው መራር ትግል በተለመደው የእብሪት መንገድ መቀጠል ያልቻለው የኢሕአዴግ አገዛዝ ከወራት በፊት በውስጡ የአመራር ሽግሽግ ማድረግ ተገድዷል። በዚኽ ሂደት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ተክተው ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን በተረከቡበት ጊዜ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ካደረጉት ንግግር ጀምሮ የወሰዷቸው አዎንታዊ እርምጃዎች በአገራችን ላይ አንዣብቦ የነበረውን ከፍተኛ አደጋ ማርገብ አስችሏል።

ይህ የለውጥ ጅማሮ መልክ ይዞ እንዲቀጥል፤ የሕዝብን ጥያቄዎች በየደረጃቸው መመለስ እንዲቻልና እንዳይቀለበስ ጠንካራ ተፎካካሪ ኃይል ያስፈልጋል።

ከትግል ተምክሯችንና ሕዝባችን ከፖለቲካ ድርጅቶች ከሚጠብቀው አደረጃጀት የወደፊት ጉዞአችን ከሚጠይቀን አካሄድ አንፃር ተመሳሳይነትና ተቀራራቢ የፖለቲካ ዓላማ፣ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ኘሮግራምና የትግል ስልት ያላቸው ድርጅቶች በተናጠል ሳይሆን በጋራ፣ በአንድነት ተደራጅተው ቢታገሉ ከሕዝቡ ጋር በመሆን ወደ አለሙት ግብ ለመድረስ የተሻለ አማራጭ ነው ብለን አምነናል።

፪. የጋራ ግንዛቤ፣

 1. በአሁኑ ጊዜ የተጀመረው የለውጥ አቅጣጫ በአገራችን አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋትን በማስገኘቱ በሕዝብ ዘንድ አዲስ ተስፋን ማሳደሩ፣ የፖለቲካ እስረኞች ጨምሮ ከመፈታታቸው እስከ እንቅስቃሴአቸውን በአብዛኛው በውጭ አገር አድርገው የቆዩ ድርጅቶች በአገራቸው ላይ በይፋ ለመታገል ጥሪ መደረጉ፣ ወዘተ. የሁኔታዎች መሻሻል መታየት መጀመሩ ለበለጠ ለውጥ ሊበረታታ እንደሚገባ፣
 2. የለውጡ ጅማሮ ግን ጠንካራ መሠረት ላይ እንዲቆም መርህን የተከተለና አገርና ሕዝብን ባስቀደመ መንፈስ አስፈላጊው ርብርብ ካልተደረገበት የመቀልበስ አደጋ ሊያጋጥመው እንደሚችል፤ በተለይም ጠንካራና ከማንም የፖለቲካ ወይንም ከብሄር ቁጥጥር ነጻ በሆኑ ብሄራዊ ተቋማት ማለትም የምርጫ ቦርድ፤ ፍርድ ቤት ወዘተ… የተደገፈ ሕዝብን የፖለቲካ ስልጣኑ ባለቤት ለማድርግ ቅድመ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት እንዲቻል፤
 3. በአገራችን ላይ የሥርዓት ለውጥ እንዲኖር እስካሁን ሲታገሉ በቆዩት ድርጅቶች በኩል እያንዳንዳቸው በተናጠል፣ አልፎ-አልፎና በተወሰነ ደረጃም ውሱን በሆነ መልኩ በጋራ፣ የሚቻላቸውን ያህል ጥረት ማድረጋቸው ባይዘነጋም፣ አሁንም በመለወጥ ላይ ላለው ሁኔታ መጣኝና ለሕዝብ አሳማኝነት ያለው አማራጭ ማቅረብ የሚችል፣ ቢያንስ ለሂደቱ አጎልባች አስተዋጽዖ ማድረግ የሚችልበት የኃይል አሠላለፍ ያልያዘ እንደሆነ፣
 4. የዚህ ለውጥ መካከለኛ ግቡ በአገራዊ የሰላምና እርቅ ሂደት ብሔራዊ መግባባት እውን እንዲሆንና ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ለማድረግ አስፈላጊ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደሆነ፣
 5. ይህ እውን የሚሆነውና ተፈጻሚነት የሚኖረው ግን በኢሕአደግ በጎ-ፈቃድ ብቻ ሣይሆን ለሥርዓት ለውጥ ሲታገል የቆየውና የሚታገለው ኃይል ተሰባስቦ እርባና ያለውና ጫና-አሣዳሪ ሚና ሊጫወት እንደሚገባው፣
 6. ለዚህም ተመሳሳይ ዓላማና ግብ ያላቸው ወደ አንድነት መጥተው አስተሳሰባቸውን አንጥረውና አቅማቸውን አጎልብተው ጠንካራ ተፎካካሪ ኃይል መሆን የሚያስችላቸው አደረጃጀት በመያዝ ሁነኛ አማራጭ ሊሆኑ እንደሚያስፈልግ፣
 7. ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጎቿ አገር በመሆኗ በኢትዮጵያ እኩልነትን የሚያረጋግጥና ፍትህን የሚያሰፍን ሕዝባዊ ሥርዓት እውን እንዲሆን አግላይና በታኝ ከሆነ የፖለቲካ ቅኝትና ያንንም መሠረት ያደረገ የፖለቲካ አደረጃጀት ልንቀበለው እንደማይገባ፣
 8. የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ጥያቄ ውስጥ የማይገባና ለድርድር የማይቀርብ መሆኑ፣
 9. አሁን ባለው ሁኔታ ኢሕአዴግ እንደ ድርጅቶች ስብስብ/ግንባር አገራችንን ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመውሰድ አደረጃጀቱና የፖለቲካ ፍልሥፍናው እንደማያስችለው፣
 10. ኢትዮጵያችን ሕዝቧ ሲታገልለትና መስዋዕት ለሆነበት ሕገ-መንግሥታዊ ዴሞክራያዊ-ሥርዓት እውን መሆን የሰከነ የሽግግር ሂደት እንደሚያስፈልግ ተገንዝበናል።

፫. የጋራ መግባቢያና ውሣኔ፤

ዝርዝር ዓላማና ግባችን ወደፊት ይፋ በሚሆነው የፖለቲካ መርሃ-ግብራችን (ፕሮግራማችን) የሚብራራ ቢሆንም፤ የሚከተሉት መሠረታዊ የፖለቲካ መርሆዎቻችን ናቸው።

 1. ሕዝብ የሥልጣን ምንጭና ባለቤትነት፣ የግለሰብ ሁለንተናዊ መብቶች፤ የሕግ የበላይነት፤ የንብረት ባለቤት የመሆን፤ ዜጎች በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ያለ ምንም ገደብና እንቅፋት የመዘዋወር፣ የመኖርና ንብረት የማፍራት እንዲሁም በማኅበራዊ ኑሮና በፖለቲካ ተሣታፊ የመሆን፣ የቋንቋ፣ የባህል፣ የእምነትና የፆታ እኩልነት ወዘተ… መብቶች እንዲከበሩ  የምንታገልላቸው ዓላማዎች ናቸው።
 2. የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣኑ ባለቤት እንዲሆን የምናደርገው ትግል ሠላማዊ እንደሚሆንና የምርጫ ፖለቲካን የምንታገልበት መንገድ መሆኑን አምነንበታል።
 3. በአገር-ውስጥም ሆነ ከአገር-ውጭ ያለው የድርጅቶች ቁጥር ብዛት የሕዝባችንን ትግል ካጓተቱት ምክንያቶች አንዱ መሆኑን ተረድተናል። የድርጅቶች ቅጥ-ያጣ የቁጥር መንዛዛት በተለይም አሁን ላለው አዎንታዊ የለውጥ ጅማሮ ደንቃራ እንደሚሆንም ተገንዝበናል።
 4. በመሆኑም የሕዝባችንን ብሶት በማዳመጥ በአገራችን የተጀመረው ለውጥ ለአስተማማኝ ውጤት እንዲበቃ ለአንድነት፣ ለፍትህና ለእኩልነት የቆምን፣ በፖለቲካ እምነታችንና በአደረጃጀታችን ተመሳሳይነት ያለን፣ ዴሞክራሲያዊና አገር ወዳድ የፖለቲካ ድርጅቶች እስካሁን በተናጠል ስንታገልልት የቆየነውን አገራዊና ሕዝባዊ ዓላማ በተሻለ ለመግፋትና ለውጤት ለማብቃት በማሰብ ባደረግናቸው ውይይቶች ኃይላችንን ማሰባሰቡ አስፈላጊ መሆኑን አምነንበታል።
 5. ለዚህም ድርጅቶቻችንን በአንድ መዋቅር ሥር ለማጠቃለልና፤ በመዋሃድ አንድ ድርጅት መሆን አስፈላጊ መሆኑን ተስማምተናል።
 6. ድርጅቶቻችንን በአንድ መዋቅር ሥር ለማድረግ የውህደት አመቻች ኮሚቴ እንዲሰየም ወስነናል።
 7. የውህደት አመቻች ኮሚቴው ሥራውን እንዳጠናቀቀ ውህደቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን ተስማምተናል።
 8. የሚዋሃዱት ድርጅቶች አጠቃላይ ድርጅታዊ አወቃቀርና የኃላፊነት ምደባዎች፣ የአዲሱ ድርጅት ስያሜና አርማ፣ መተዳደሪያ ደንብና የፖለቲካ ፕሮግራም፣ ወዘተ…  ከጉባኤው በፊት በውህደት አመቻች-ኮሚቴው ለስብስቡ ድርጅቶች ቀርቦና ተወያይተውበት በሙሉ ስምምነት ማጽደቅ ይኖርባቸዋል። በነዚህ በቀረቡ መሰረታዊ ጉዳዮች ያልተስማማ ማንኛውም ድርጅት ይህ የተፈረመ ሠነድ መያዣ አይደለምና እራሱን ከውህደቱ የማግለል ሙሉ መብት አለው።

 1. በውህደቱ መካተት የሚፈልጉ የፖለቲካ ድርጅቶች ሲያመለክቱ በአመቻች ኮሚቴው በሚቀርበውና ስምምነት በሚደረግበት ለአባልነት የሚያበቃ መመዘኛ መሠረት አሟልተው የሚገኙ፣ ይኸን የመግባቢያ ሰነድና ቀደም ሲል የተደረጉ ስምምነቶችን የሚቀበሉ የውህደቱ አካል ሊሆኑ፣ ወይም ውህዱን ፓርቲ ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ ተስማምተናል።
 2. ውህደቱ እውን እስከሚሆን ድረስ ሁላችንም የለውጡ ሂደት እንዳይደናቀፍና መሥመሩን እንዳይስት ድርጅታዊ ኃላፊነታችንን መወጣት የሚያስችሉና ከመግለጫዎች ጀምሮ ባሉና በዝርዝር በሚቀመጡ የሕዝቡን ትግል ለማጠናከር የሚረዱ ተግባራትን በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል።
 3. ውህደቱ እውን እስከሚሆንና አዲሱ ድርጅት (ፓርቲ) እንቅስቃሴውን በመሥራች ጉባዔው በሚፀድቁት ድርጅታዊ ሰነዶች (የፖለቲካ ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ወዘተ…) መሠረት እስከሚጀምር ድረስ፣ በውህደቱ ሂደት የሚሣተፉ ድርጅቶች ህልውናቸው ተጠብቆና በዚህ የጋራ ግንዛቤ ሰነድ ላይ ስምምነት የተደረገባቸውን መርሆኣዊ አቋሞች ባልተፃረረ ሁኔታ እንቅስቃሴዎቻቸውን የመቀጠል መብታቸው የሚከበር መሆኑ ግንዛቤ ተወስዶበታል።
 4. በውህደት የምንመሠርተው ድርጅት የሚያካሂደው ትግል ሕዝብን ማዕከል አድርጎ መቀጠል ስለሚኖርበት፣ እንቅስቃሴው በይፋ በአገር ውስጥ እንዲሆን ወስነናል።
 5. በውህደቱ ሂደት ተሣታፊ የሆኑ ድርጅቶች ውህደቱን ተግባራዊ ለማድረግ በሚድርጉ የጋራ ጥረቶችም ሆነ በውህደት የሚመሠረተው ድርጅት የፖለቲካ ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ወዘተ… የመሣሰሉ ድርጅታዊ ሰነዶችን በማዘጋጅቱ ተግባር ላይ በሚቋቋሙ የተግባር ኮሚቴዎች ውስጥ በወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍና ሥራ ላይ ከመዋላቸው በፊት በሚደረጉ ውሳኔዎች ላይ እኩል ተሣታፊ የመሆን መብታቸው እንደሚከበር፣ የተሰጣቸውን ኃላፊነትም በብቃት የመወጣት ግዴታ እንዳለባቸው ተስማምተናል።
 6. የውህደቱ ተሣታፊ ድርጅቶች በውህደቱ ሂደት በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ የሚያዙ ቃለ-ጉባዔዎች፣ የኢሜይልና የደብዳቤ ልውውጦች፣ በስልክ የሚደረጉ የሃሳብ ልውውጦች፣ ወዘተ… የስብስቡ ምስጢር ስለሆኑ እያንዳንዱ ድርጅት በኃላፊነት መንፈስ ተገቢውን ጥንቃቄ በመስጠት ሊይዝና ሊጠብቅ እንደሚገባ ተስማምተናል።

 1. በውህደቱ ሂደት ማንኛውም በስብስቡ ስም ሆነ ስለስብስቡ በጽሑፍም ይሁን በቃል ለመገናኛ ብዙኃን የሚሰጡና ለሕዝብ ይፋ የሚደረጉ ጋዜጣዊ መግለጫዎች፣ የሂደቱ አባል ድርጅቶችን የጋራ ይሁንታ ያገኙ ሊሆን እንደሚገባ ተስማምተናል።

 1. የውህደቱ ምሥረታ በአገር ውስጥ እንዲሆን ተስማምተናል።

የትብብር ጥሪ፤

ሀ.    በአገራችን የሥርዓት ለውጥ እንዲኖር እስካሁን ስትታገሉ ለቆያችሁና ከላይ በተዘረዘሩት መሠረታዊ መርሆዎችና ግንዛቤዎች ላይ ተመሳሳይ አቋም ያላችሁ ኢትዮጵያዊ የአንድነትና የዴሞክራሲ ኃይሎች የጀመርነው የውህደት ሂደት አካል እንድትሆኑና የሕዝባችን ትግል ለአስተማማኝ ውጤት እንዲበቃ የሚደረገውን ጥረት እንድናጠናክር ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን።

ለ.   በሁኔታዎች አስገዳጅነት በማንንነት ጥያቄ ዙሪያ ለተደራጃችሁና ዓላማና ግባችሁን ለአገራዊ አንድነትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በማድረግ ለምትንቀሳቀሱ ድርጅቶች የትብብር ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን።

እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተመለከተው የድርጅቶች ተወካዮች በድርጅቶቻችን ስምና በተሰጠን ሙሉ ውክልና ይህንን ሰነድ መቀበላችንን በፊርማችን እናረጋግጣለን።

የተወካይ ስም፣     የወከለው ድርጅት፣       የተወካይ ፊርማ

 1. ወ/ሮ ፅጌረዳ ሙሉጌታ፤ የኢትዮጵያ መድህን ሞክራሲያዊ ፓርቲ (መድህን)

 1. 2. አቶ ተሻለ ሰብሮ፤ የኢትዮጵያ ራእይ ፓርቲ (ራእይ)

 1. 3. አቶ ስለሺ ጥላሁን፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክርቤት (ሽግግር)

 1. 4. ዶ/ር አክሎግ ቢራራ፤ ብሩኅ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብሩኅ)

 1. 5. አቶ በርገና ባሳ፤ ቱሳ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ቱሳ)

 1. አቶ ነሲቡ ስብሀት፤ ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ (ኢትዮጵያችን)

 1. 7. አቶ ግርማ በቀለ፤ የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት (ኦሞ ህዝቦች)

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ሀገራችን ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት ታቅፍና ተከብራ በነፃነት ለዘለዓለም ትኑር!!

ህዳር ፲፭  ቀን፤ ፪ ሽህ ፲፩ ዓ/ም   (November 25, 2018)

1 thought on “ሰባት የፖለቲካ ድርጅቶች ዉህደት ሊፈጥሩ ነው

 1. Except from the 7th in the list, aren’t all representative of the Amharic speaker?
  Are they forming unity with their self? Or do they think of their Menelik’s era deception? Myo mia!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.