ከአማራ ተማሪዎች ማህበር በዩኒቨርሲቲዎች ስላለው ችግር

Amhara Students Association/የአማራ ተማሪዎች ማህበር

– ከወደ አምቦ በደረሰን መረጃ መሠረት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሞና በአማራ ተማሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት ሁለት የአማራ ተማሪዎች ከፎቅ ላይ ተወርውረው በህክምና ላይ ናቸው ።ሌሎች ቁጥራቸውን በውል ያላወቅናቸው የአማራ ተማሪዎች ቀላል የማይባል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

– በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የአማራ ተማሪዎች ዶርማቸውን ለቀው በሜዳ ላይ ናቸው።

– በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የአማራና የኦሮሞ ተማሪዎች የሚኖሩት በፖሊስ እየተጠበቁ ለየብቻ ነው። ሲወጡ ሲገቡ ፖሊስ በመሀል ሆኖ ነው።እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር። በግጭቱ ምክንያት በቤታቸው ያሉ ተማሪዎችን ቀን ቆርጦ እስከ ሰኞ 01/03/2011 ዓ.ም ካልመጣችሁ እያለ እያስጨነቃቸው ነው።

– ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ካምፓስ በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ተማሪዎች እስካሁን አልተጠሩም። ተማሪዎቹ ባለፉት ዓመታት የሆኑትን እያሰቡ፣ ብንጠራም አስተማማኝ ዋስትና ስለሌለን የሚመለከተው አካል አንድ ይበለን እያሉ ይገኛሉ።በዩኒቨርሲቲዎች እየተነሳ ያለው ግጭት በሌሎች አካባቢዎችም ሊቀጥል እንደሚችል አንዳንድ ፍንጮች እየታዩ ነው።


ስለዚህ:-
1)ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት:-
የአማራ ተማሪዎች ያለ ጠባቂና ያለ ተቆርቋሪ በየቦታው እየተገደሉ ነው:የአካል ጉዳት እየደረሰባቸው ነው:ከዚህ ያመለጡት ደግሞ በፍርሃት ትምርታቸውን መከታተል አልቻሉም ።ከሁኔታዎች መረዳት የቻልነው ችግሩ ከዚህም እንደሚከፋ ነው።ነገን ማሰብ የምንችለው መጀመሪያ ህልውናችንን ማረጋገጥ ስንችል ነው።ስለዚህ የአማራ ክልል መንግስት የአማራ ተማሪዎችን በአማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀብሎ እንዲያስተምር ስንል እንጠይቃለን


2)ለትምህርት ሚኒስቴር:-
እኛን የሚያሳስበን የተማሪዎቻችን ደህንነት ነው:ከምንም ነገር በፊት ቅድሚያ ለህይወታቸው ዋስትና እንዲሰጣቸው እንፈልጋለን:ይህንና መሰል ጉዳዮች ከዚህ በፊት ተገናኝተን የተወያየን ቢሆንም ቅሉ ነገሮች እየተባባሱ መምጣታቸውንና እናንተም የጠየቅናቸውን ጥያቄዎች መመለስ አለመቻላችሁን ተገንዝባችኋል ብለን እናምናለን።ስለዚህ ጥያቄያችን የህልውና ጥያቄ መሆኑን ተረድታችሁ የአማራ ተማሪዎችን ከተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ በሰላም እንድትለቁልንና በክልላቸው ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲማሩ አስፈላጊውን ሀሉ እንድታደርጉላቸው አስከዚያው ድረስ ግን ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ስንል እንጠይቃለን


3)ለሌሎች ብሔር ተማሪዎች:-
ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሆይ በአማራ ተማሪዎች ላይ እያደረጋችሁት ያለው ነገር ቢያመንም ቅሉ ነገን በማሰብና ዘላቂ መፍትሔን በመሻት ልዩነቶቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ እንነጋገር ስንል ጥሪ እናቀርባለን።አለበለዚያ ግን “የጉርሻ ወንፈል ወጥ ይጨርሳል”እንዲሉ መጨረሻ የሌለው ነገር ውስጥ ከመግባታችን በፊት ቆም ብላችሁ እንድታስቡ እናሳስባችኋለን።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.