ዮናስ ጋሻዉ በወያኔ የደረሰበት የፍትህ ሰቆቃ

አባቱ በደርግ ጊዜ የፍኖተ ሰላም ከንቲባ ነበሩ። ወያኔ ከገባ በኋላ አባቱን ሲያሳድድ እናቱን ደግሞ ፈረስ ቤት ያለፈቃዷ ተቀይራ እንድትሰራ አድርገዋታል። በኋላም ባለቤቷ የደርግ አባል ነዉ በሚል ለአምታት ካሰቃዩአት፡ መስሪያ ቤት ዉስጥ በሷ ስም የተመዘገበ ንብረት እና ገንዘብ ከዘረፏት በኋላ በ 94 አ.ም መኪና አጋጭተዉ ገድለዋታል። ወንድሙም በአደባባይ ባሕር ዳር ከተማ በመከላከያ ከተገደለ በኋላ በኦራል መኪና በአስከሬኑ በመመላለስ አጥንቱን አድቅቀውታል፡፡ በዚህ ያልረካው ወያኔ ዮናስን በማሰር እንዲህ አካሉን አጉድሎ ለቆታል፡፡ ከኮተቤ ጫካ ጀምሮ እስከ ቅሊንጦ በቃላት የማይገለጽ ሰቆቃ ተፈጥሞበታል ዮናስ ጋሻዉ። ዮናስ የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አልነበረም፡፡ ብቸኛው ጥፋቱ አማራ ሁኖ መወለዱ ብቻ ነው፡፡
ኮተቤ ወስደዉ ሁለት እጁን ዛፍ ላይ አስረዉ በማንጠልጠል ደብድበዉታል በማእከላዊ
*ሁለቱን የዘር ፍሬዉን አፍሠዉታል
-*ከፊት ጥርሱ የታችኛዉን በ ጉጠት ጎትተዉታል
*ጥፍሮቹን ነቅለዋል
*ብልቱን በጉጠት ጎትተዉታል።
*ብልትህም ቆ*ጥህም አይሰራም ከንግዲህ አትወልድ በለዉ የጣት ቀለበቱን፡ ያንገት ሃብሉን ወስደዋል
* አንዲት ሴት እናትህን፣ አባትህን ድራሻቸዉን አጥፍተናል አንተ ደግሞ ልትታገል እያለች ከታሰረበት የጨለማ ክፍል ብዙ አሰቃይተዋለች።

ዮናስ ዛሬ ባሕር ዳር መግባቱ ተሰምቷል፡፡ በተቀናጀ መንገድ ሁሉንም ከእስር የተለቀቁ ወገኖች መርዳት እስኪጀመር እለት ምግብና ሕክምና የሚውል ድጋፍ ልናደርግ ይገባል፡፡ ዮናስ ከእግር ሕመሙ ባለፈ አዕምሮው በመጎዳቱ ተፈጥሯዊ እንቅልፍ አይወስደውም፡፡ የሚተኛው የእንቅልፍ መድኃኒት በመዋጥ ነው፡፡

ዮናስ መርዳት ለምትፈልጉ

Yonas Gashaw Demeke, ዓባይ ባንክ አ.ማ, የቁጠባ ቁጥር 115 101 2403200 010

share በማድረግ ለሌሎች እናጋራ

ስለዮናስ ሰኔ ላይ የፃፍሁት ነዉ። የዮናስን ስልክ የምታዉቁ ሀሳብ መስጫዉ ዉስጥ አስቀምጡልኝ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.