የትግራይ ሕዝብ በከፈለው መስዋተነት የኦሮሞ ህዝብ ተጠቃሚ ነው -ጃዋር መሐመድ

ጆዋር መሐመድ ለትግራይ ቲቪ ዛሬ ከሰጠው ኢንተርቪው የተቀነጨበ  ታማሪ ሰይፈስላሴ ገብረመስቀል ጓንጉል እንደሚከተውን አቅርቢታል። ጃዋር መሐመድ
—-

*በአሁኑ ሰዓት የሕወሐት ባለስልጣናትን ብቻ ሳይሆን መላው የትግራይ ህዝብንም ለማጥቃት የተዘጋጁ ቡድኖች እና ግለሰቦች አሉ። የትግራይ ህዝብ እነዚህ ለመመከት ከማንም ጊዜ በላይ በተጠንቀቅ ሊቆም ይገባል።

*የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያ አንድነት ያካሄደው ትግል እና የከፈለው መስዋእትነት ማንም ሊዘነጋው አይገባም። የትግራይ ሕዝብ የደርግን ሰርዓት ለመጣልና የፌዴራል ሥርዓቱ እንዲመሠረት ከፍተኛውን መስዋዕት ከፍሏል፡፡ በዚህም የኦሮሞ ሕዝብ ተጠቃሚ ሆኗል፡፡

*አሁንም ይህ የፌዴራል ሥርዓት እንዲቀጥል ከትግራይ ሕዝብ ጎን ልንሰለፍ ይገባል፡፡

*የትግራይ ህዝብ ያሳየው ሰላማዊ ሰልፍም የህዝብ ድምፅ ሰለሆነ መከበር ያለበትና እኔም የምደግፈው ነው።

*ወደ ትግራይ ክልል በአማራ ክልል አድርገው የሚሄዱ መንገዶች መዘጋት ትልቅ ሰህተት ነው ወዲያው የፌደራል መከላከያ ሃይል መጥቶ ሰርዓት ልያስይዝና ማስከፈት ይገባል።

*የኦሮሞና የትግራይ ህዝብ ግንኙነት የቆየ እንደሆና አሁንም የበለጠ መልካም እንዲሆን መሰራት ይገባናል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.