እነ ዶ/ር መራራ ማሳመን ሲያቅጣችው ማስፈራራቱን እንደ ስትራቲጂ እየተጠቀሙበት ነው #ግርማ_ካሳ

ዶ/ር መራራ ጉዲና አሁን ያለውን የጎሳ ፌዴራል አወቃቀር መቀጠል አለበት እያሉ ነው። ችግሩ ያለው ፌዴራሊዝሙ ላይ ሳይሆን አተገባበሩ ላይ ነው ያሉት ዶ/ር መራር ፣ ወደ ቀድሞ አስተዳደር መመለስ ዋጋ እንደሚያስከፍል ይናገራሉ። አሁን ያለው አወቃቀር ዋጋ እንዳላስከፈለ።

‹‹የትግራይ፣ የኦሮሞ፣ የሶማሌ፣ የጋምቤላ …ነፃ አውጭ ድርጅቶች ባሉበት፤ የአማራ ነፃ አውጭ የሚመስሉ ድርጅቶች እየተፈጠሩ ባሉበት ሁኔታ ወደቀድሞው አስተዳደር ሥርዓት (ጠቅላይ ግዛት) ለመመለስ መሞከር ዋጋ ያስከፍለናል” ያሉት ዶ/ር መራራ፣ መፍትሔው አሁን ያለውን የፌዴራላዊ ሥርዓት በሕዝቦች ፈቃድ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ማድረግ ነው ይላሉ።

ዶ/ር መራራ አሁን ያለው የፌዴራል አወቃቀር የሚቃወሙ ወገኖች ለምን እንደሚቃወሙ ጠንቅቀው ያውቃሉ ብዬ አስባለሁ። ቅንጅት፣ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ ኢዴፓ፣ መኢአድ ..በአገር ውስጥ ሲንቀስቀሱ የነበሩና የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄረተኛ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያንና አክቲቪስቶች፣ አሁን ያለውን የጎሳ አወቃቀር ሲቃወሙ ፣ ወደ ድሮ አሃዳዊ፣ ፌዴራል ያልሆነ ስራዓት እንመለስ በማለት አይደለም። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ፌዴራሊዝምን አይቃወምም። ፌዴራሊዝም ላይ ምንም ችግር የለም። ማንም የድሮውን አሃዳዊ ስርዓት ይምጣ አለለም።

ይሄን እውነታ ዶ/ር መራራ ጠንቅቀው እያወቁ፣ የድሮውን ፣ አሃዳዊ የሆነውን አስተዳደር ስለመመለስ ለምን እንደሚያወሩ ግልጽ ሊሆንልኝ አልቻለም።

አሁን ያለውን የጎሳ አወቃቀር ይቀየር በሚባልበት ጊዜ የጎሳ አወቃቀሩን የሚደገፉ ወገኖች፣ አሁን ያለውን የጎሳ አወቃቀር ለምን የተሻለ እንደሆነ አሳማኝ መከራከሪያ ከማቅረብ ይልቅ ፣ በሐሳብ ማሸነፍ ሲያቅታቸው፣ “ወደ ድሮው ስርዓት ሊመለሱን፣ ነው፣ አሃዳዊ ስርዓት ሊያመጡበን ነው፣ ደም መፋሰስ ነው የሚሆነው… .ወዘተረፈ” እያሉ ደጋፊዎቻቸውን በዉሸት በማታለልና ሌላውን በማስፈራራት የጎሳ አወቃቀሩ እንዳይቀየር የማድረግ ታክቲክና ስትራቴጂ ያላቸው ነው የሚመስለው። ዶር መራራ ይሄንኑ ታክቲክ ነው ሞደሬት በሆኑ መልኩ ለመጠቀም የሞከሩት።

ዶ/ር መራራ አሁን ያለው ፌዴራል አወቃቀር መቀጠል አለበት ሲሉ፣ አንድ አብረው የተናገሩት አባባል አለ። “የፌዴራል ሥራ’ዓቱ በሕዝቦች ፈቃድ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ማድረግ” ይላሉ። ይሄ የሚደገፍ አባባል ነው። ግን ይሄን አባባል አስበዉት የተናገሩት አይመስለኝም። ለምን እርሳቸው እንዳሉት የሕዥብ ፍላጎት ከተጠየቀ የጎሳ አወቃቀሩ ስለሚቀየር። ይኸው እኮ እያየን ነው የደቢብ ክልልን ነዋሪዎች አንቀበልም እያሉ ነው ፣ በይፋ።

አሁን ያለው ፌዴራሊዝም በሕዝብ ስምምነት የተደረገ ፌዴራሊዝም አይደለም። በሕወሃትና ኦነግ ፖለቲከኞችና ባላስልጣናት የኦነግንና የሕወሃት ፍላጎት ያንጸባረቀ ፌዴራል አወቃቀር ነው። በተለይም የአማራውና አማርኛ ተናጋሪዉን፣ እንዲሁም ሕብረብሄራዊ የሆነውን የኢትዮጵያ ብሄረተኛው ጥቅምና ፍላጎት ያካተተ አይደለም። እንደውም እነዚህን ማህበረሰባት የጎዳ ነው። በመሆኑም አማራው፣ የብዙ ብሄረሰቦች ድብልቅ የሆነው የኢትዮጵያ ብሄረተኛው ፍቃድና ፍላጎት ከተጠየቀ አሁን ያለው የጎሳ አወቃቀር መቀየሩ የማይቀር ነው።

ዶ/ር መራራ “የአማራ ነጻ አውጭ” ስላሉት አባላል ትንሽ ልበል። በኢትዮጵያ ውስጥ በጉልህ ሁኔታ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የአማራ ድርጅቶች አብንና አዴፓ ናቸው። እስከሚገባኝ ድረስ እነዚህ ድርጅቶች የአማራ ነጻ አውጭ ድርጅቶች አይደሉም። እንደ ኦነግና ሕወሃት ኦሮሚያንና ትግራይ ነጻ እናወጣ ብለው የተደራጁ አይደለም።

ዶ/ር መራራ ምን አልባት መረጃው ከሌላቸው እነዚህ ድርጅቶች አሁን ያለው የጎሳ አወቃቀር ፈርሶ፣ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት የሚያስተዳደር ፍትሃዊ ፣ ዘመናዊ፣ ከዘር ጋር ያልተገናኘ ፌዴራል አወቃቀር ከመጣ፣ በአማራ ስም ተደራጅተው መቀጠል የማይፈለጉ ናቸው። የነዚህ የአማራ ድርጅቶች ጥያቄ “አማራው ለብቻ የራሱ ክልል ይኑረው፣ አማራው ብቻ ይጠቀም” የሚል ሳይሆን “አማራው ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት በተለይም በትግራይና በኦሮሞ ብሄርተኞችን በደል ስለደረሰበት፣ ስለተፈናቀለ፣ አሁንም እየተፈናቀለ ስላለ፣ በኦሮሞ ክልል ፈንታሌ ወረዳ ሰሞኑን እንደሆነው፣ አማራው መበደል የለበትም፣ ከሌላው እኩል መሆን አለበት” ብለው የእክልነትና የሕልዉና ጥያቄ አንስተው የተነሱ ናችው።

ከዚህ በፊትም በኦፌኮ የዶ/ር መራራ ጉዲና ምክትል አቶ በቀለ ገርባ ተመሳሳይ ንግግር ተናግረው ነበር። በአገራችን ለተከሰቱ የጎሳ ግጭቶች ምክንያቱ የጎሳ ፌዴራል አወቃቀሩ ሳይሆን የዲሞክራሲ እጦት ነው ብለው። ይመስለኛል ዶ/ር መራራ የፌዴራሊዝም አተገባበሩ ላይ ችግር ያሉትን ዲሞክራሲያዊ አልነበረም ከሚል ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ ኖሮ አያውቅም። ምን አልባት አሁን በቅርብ እናይ ይሆናል። ከኢሕአዴግ በፊት የነበረው ወታደራዊ ደርግ ነበር። ከደርግ በፊት ደግሞ ንጉሳዊ አገዛዝ ነበር(absolute monarchy) ። በአጤ ሚኒሊክ ጊዜ ደግሞ በተወሰነ መልኩ ፌዴራል አስተዳደርም ነበር ማለት ይችላል። በወላይታ ንጉስ ጦና፣ በወለጋ ደጃዝማች ሞረዳ፣ በጂማ፣ ጂማ አባ ጂፋር፣ በጎጃም ንጉስ ተክለሃይማኖት …ያስተዳድሩ ነበር።

ሆኖም ግን በኢሕአዴግ ዘመን እንዳየነው ፣ የጎሳ ግጭቶችን፣ ከሚናገሩት ቋንቋ፣ ከዘራቸው፣ ከጎሳቸው የተነሳ ዜጎች ሲፈናቀሉ ያየንበት ሁኔታ አልነበረም። የዲሞክራሲ እጦት ቢኖር ኖሮ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እንደሚሉን በደርግም ነገስታቱ ዘመንም መፈናቅሎች በብዛት ይኖሩ ነበር።

አሁን ባለንበት ጊዜ በትግሬና በአማራ፣ በጉሙዝን በኦሮሞ፣ በሲዳማና ወልያታ፣ በኦሮሞና በጌዴዎ፣ በሃረሪና በኦሮሞ ..መካከል ግጭቶችን አይተናል። በአማራና በኦሮሞ መካከል ደግሞ አሁን ያለው የጎሳ አወቃቀር ከቀጠለ፣ በሸዋ ጉዳይ ደም መፋሰስ መኖሩ የማይቀር ነው። አማርኛ ተናጋሪዎች በብዛት የሚኖሩባቸው አካባቢዎች በተለይም ሸዋ በኦሮሞ ክልል በጭራሽ መቀጠል አይቻልም። ወይም ኦሮሞው ከሌላው እክሉ ሆኖ ተከባብሮ ሕብረ ብሄራዊ በሆነ ክልል መኖር ከፈለገ አማራውም ይስማማል። አለበለዚያ ግን አማራው አይቀበልም። ጉራጌዎች ወሊሶ የኛ ነው ይላሉ። ሲዳማዎች ሻሸመኔ የኛ ነው ይላሉ። ብዙ ብዙ የተወሳሰቡ አስችጋሪ ጥያቄዎች አሉ። ይህ የጎሳ አወቃቀርን መቀጠል ትርፉ ደም መፋሰስ ብቻ ነው።

ለጊዜው ሌላውን ሁሉ ትተን የጎሳ አወቃቀሩን አስከፊነት ለማየት በሶማሌዎችና በኦሮሞዎች መካከል ያለውን ግጭት ብቻ ለማየት እንሞክራለን።

ከዚህ በታች የምታዩት በሰው ሰራሽ(የጎሳ ግጭቶችና) በተፈጥሮ ችግሮች(ደርቅ፣ ረሃብ…) ምክንያት በሶማሌና በኦሮሞ ክልል የተፈናቀሉትን ዜጎች ቁጥር ያስቀምጣል። በድርቅ ምክንያት በሶማሌ ክልል 341425 በኦሮሞ ክልል ደግሞ 111936 ዜጎች ተፈናቅለዋል። በአጠቃላይ ወደ 453341 ሺህ ህዝብ።

በጎሳ ግጭቶች ደግሞ. እንደ ጥናቱ 453341 ሲፈናቀሉ፣ 565346 ኦሮሞዎች ተፈናቅለዋል። በአጠቃላይ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ናቸው። በጎሳ ግጭቶች ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች በዋናነት በሶማሌና ኦሮሞ ድንበር አካካቢ ፣ በምስራቅ ሃረርጌ ሃረርና ጂጂጋ አካባቢ፣ በምእራብ ሃረርጌ ሜኤሶ ወረዳ፣ በሞያሌ፣ በሊበንና ቦረና ዞኖች ነው። እነዚህ አካባቢዎች ሶማሌዎችና ኦሮሞዎች ከሌሎች ጋር አንድ ላይ ሆነው ለዘመናት የኖሩባት አካባቢዎች ናቸው። ሆኖም አሁንም ባለው የጎሳ አወቃቀር መሬቶች በዘር ስለተሸነሸኑ፣ የሶማሌ፣ የኦሮሞ ስለተባለ ብዙ ሶማሌዎች በኦሮሞ ክልል፣ ኦሮሞዎች ደግሞ በሶማሌ ክልል በመጠቃለል በአገራቸው እንደ መጤና ሁለተኛ ዜጋ እንዲቆጠሩ አድርጓል። ያም አድልዎ ፈጥሮ፣ መብት እንዲረገጥ ሁኔታዎች አመቻችቶ ፣ ግጭቶችን አስከትሏል።

ስለሶማሌና ኦሮሞ ክልል ስንሄድ ደግሞ ድሬዳዋንና ሞያሌ ሳይጠቅሱ ማለፍ አይቻልም። ድሬዳዋ የቻእርተ ከተማ ናት። ሶማሌዎች፣ ኦርሞዎችም የኛ ናት ስላሉ፣ ስላልተስማሙ፣ ድሪዳዋ የማን ሳትሆን በፌዴራል ስር ነው ያለችው። ሞያሌ ከተማን ደግሞ ለሁ፤እ ትከፍለዋታል። ከዋናው መንገድ በስተምስራቅ ሶማሌ ሲሆን ደግሞ በስተ ምእራብ ደግሞ ኦሮሞ ነው። ለዘመናት በፋር የኖሩ ከተሞችን ሁሉ አሁን ያለው አወቃቀር እያተራመሰ ነው።

አሁን ያለውን የጎሳ አወቃቀር መቀየር ዶ/ር መራራ እንዳሉት ዋጋ አያስከፈልም። ይልቅ ይሄ የተረገመ ሰይጣናዊ፣ ከፋፋይ አፓርታይዳዊ አወቃቀር ወደዚያ ጥለን በተሻለ፣ ለአስተዳደር አመች በሆነ፣ ማንም ዜጋ በዘሩና በጎሳ ልዩነት እንዲደረግበት የማይፈቀድ፣ ኢትዮጵያዉያን በሁሉም የአገሪቷ ምድር በነጻነት የመኖር፣ የመስራት፣ የመማር፣ የመነገድ፣ የመምረጥ፣ የመመረጥ ..መብታቸውን የሚያረጋገጥ ፣ ዘመናዊ፣ ተራማጅ ፣ ለአስተዳደር አመች የሆነ፣ ህዝብን የማያጉላላ የፌዴራል አወቃቀር ካላመጣን፣ በአገራችን ትልቅ ደም መፋሰስን ጠብቁ !!!!!

6 COMMENTS

 1. A short message for Dr. Merara Gudina

  Dr. Merara Gudina is one of the beloved Oromo sons. But something I dought his honesty and integrity. He has no often clear stand on the political development in Ethiopia. Even sometimes he speaks against the political programs of his own party (the OFC). I believe, Merara is not naive. But always he tries to cool down the ultra nationalists of the Menilik worshipers. But such double standards will not work in the Ethiopian politics and also elsewhere. Therefore, I would like to advise my dear brother (Dr. Merara) to guard his integrity and speak honesty his mind and the truth. The truth will triumph on falsehoods and bigotry soon or later.

  A massage to those bigots:

  The Ethiopian peoples have been suffering from man-made political syndrome of a century old which was created by greedy politicians all the times so far. All these politicians have never cared about collective and individual rights. That is why we are still struggling against all sorts of odd ideologies, mentalities and thinking. The century old struggles of the peoples in Ethiopia have produced most of the political organizations like TPLF, OLF, ONLF, SLF and EPLF. No one of them were created by default or by accident.

  The current ethnic federal structure of Ethiopia is the political arrangements which were mainly constructed and promoted by the beloved Oromo intellectuals and OLF leaders like Gelassa Dilbo, Lenchoo Lataa, Dima Nagawo and others. The TPLF has accepted it by making few modification. The TPLF tried to implement it at least nominally after banning the OLF, in order to win the hearts of the Oromo nation. Therefore, the main shareholder of this federal arrangement is the OLF, the freedom fighter. Accusing the TPLF in regard of the federal structure is unfair. The TPLF must be accused for shortcomings of the implementation and wrong boundaries. Thus, this federal structure was not implemented at the free will of the TPLF. It is a fruit of the century old bitter struggles of the Oromo nation in particular and other subjugated nations in general. Consequently, accepting these federal arrangements is a must for all stockholders. The political merchants like Ginbot 7 make only noises temporarily which will not last long. Watch out! Girma Kassa and Girma Seifu are good for nothing. Therefore, their noses make no sense.

 2. ለረዥም ጊዜ በዘር የተመሰረተ ፌደራሊዝምን ኢህአዴግ በሕወሓት መሪነት የመንግስተ ሰማያት መሰል ሲያሞግሷት ኖረዋል።ይሄም ዴሞክራሲን በማፈን የኢት ህዝቦች በሰላም እንዳይኖሩ፣በፈለጋቸው አካባቢ ሰርተው ተቀማጭነታቸው ሳይከበር፣በግፍ ተፈርጀዋል ።
  እላይም እንደተጠቀሰው በህወሓትና በኦነግ የተጠነሰሰ ሴራ በሕገመንግሥቱ በማሳበብ የኢትዮ ህዝቦችን በድለዋል። አሁን ይሄንን ጉዳይ ዶክተሩ ለምን ለምን አነሱት ቢባል በህዝብ ውሳኔ ላይ ከባድ ጥርጣሬ ስላለ ይሄንን አደባብሶ በፌዴራሊዝም ስም ንግድ ነው። በተጨማሪም የምርጫውን ሁኔታ በተፋጠነ ሁኔታ ለማካሄድ ይፈልጋሉ። መልሱም አንድ ነው ፣አሁን በተያዘው ሕገመንግሥት ስር ምርጫው ከተካሄደ የህዝብ ተቀባይነት አለው ለማለት የተፈለገው ይመስላል ። የኢትዮ ህዝቦች ጥያቄ ግን ህገመንግቱን አለመቀበል ብቻ ሳይሆን እሱም የፈጠረውን የዘር ክልል ጭምር ነው።ይሄ ሂደት የመናገር መብት ከተጀመረበት የዶር አብይ ጊዜ የተዳፈነው መብት በማቆጥቆጡ የዘር አቀንቃኞችን አደናግጧል። እንደትርክቱ የብዙሃንነትና ጊዜው አሁን የኛ ነው ባዮችን አሰደንግጧል። በፊት ለፊት እንነጋገር ከተባለ ይሄን የሚያስተናግዱት ኦነግና መሰሎቹ ናቸው ።አሁን አስመስለው የስም ለውጥ ቢያደርጉም ፣መሰረታቸውን በበግ ለምድ ተኩላነታቸውን እያንፀባረቁ ነው። ደስም ያላለቸው ባመጡት የዘር መዋቅር አሁን ብዙዎች ብሎም አማራ ስለተደራጀ አይሆንም ከማለት ምክንያት ፈልጎ መከራከርን መርጠዋል።
  የኢትዮጵያ ህዝቦች አስተዋይ ስለሆኑ ይፋጃሉ የሚለውን አመለካከት ለመቀበል ይከብደኛል ።

 3. የዜግነት ፖለቲካ የምታራግቡ ሰዎች በዚህ ወቅት ለአማራው ህዝብ ከፍተኛ አደጋ እየጋበዛችሁ ነው:: መሬት ላይ ነባራዊ ሀቅን ክዶ የሚሻልልህን አውቅልህለሁ ዘመን አክትሟል:: ኦሮሞው በኦሮሞነቱ ብቻ ትግሬውም እንደዚሁ በተደራጀበት የፖለቲካ ዘመን አማራው በአማራነት ብቻ ተደራጅቶ ኢትዮጵያን የሚገነባበት ወቅት አሁን ነው:: ከ 30 አመታት በሗላ የዜግነት ፖለቲካውን ያኔ ታሽከረክራላችሁ

 4. ውድ ግርማ፣
  “እነ ዶ/ር መራራ ማሳመን ሲያቅጣችው ማስፈራራቱን እንደ ስትራቲጂ እየተጠቀሙበት ነው” ያልክበት ምክንያቱን ርቀህ ሳትሄድ ገልጸኸዋል! በመጀመሪያ የዶ/ሩ ስም መረራ እንጂ መራራ አይደለም፡፡ ሁለተኛ፣ የከነከነህ “አማራ ነጻ አውጭ” የምትለዋ አባባል ነው፤ ይህም በየድረ ገጹ የሚጻፉትን እንዳላነበብክ ይገልጻል፤ እንጂ አማራ በጎሳ/በክልሉ መደራጀቱ አማራጭ የለውም የሚሉ ጥቂት አይደሉም፡፡ ሌላኛው፣ ዶ/ር መረራ እንዳሉት፣ “ፌዴራሊዝም” እርግጥ የተዋቀረው በጎሳ አሠፋፈር ነው፡፡ አማራ በአማራ ክልል፣ ኦሮሞ፣ ደቡብ በየክልሉ፡፡ ህወሓት/ትግራይ ብቻ ነው ቦታው ስላልበቃው ሁሉ ቦታ ለመሆን የሞከረውና የከሸፈበት፡፡ ህወሓት “ፌዴራሊዝምን” ለእኲይ ኣላማ ኣዋለው እንጂ የኢትዮጵያን አንድነት የሚያስከብር አመራር እስከ ኖረ ድረስ ለአገር ልማት እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ አማራ ተነካ በማለት በትንሹ በትልቁ መናቆሩን ትተን ልበ ሰፊ መሆን ብቻ ያዘልቀናል፡፡

 5. Girma Kaasaa says: “ማሳመን ሲያቅጣ[ታ]ችው”! You are right, who can convince persons like you?? You are not arguing based on a given rationale, to convince others or otherwise to be convinced by a counter-argument.
  First answer the question: “አሁን ያለውን የጎሳ አወቃቀር ይቀየር በሚባልበት ጊዜ “, WHAT IS YOUR ALTERNATIVE POLITICAL ARRANGEMENT???
  Without putting forward an alternative agenda, crying for “የጎሳ ፌዴራሊዝም ይቀየር!” ad infinitum, is non-sensical!

  As you have admitted, you can not be convinced, i.e. you want to dicate your will, and your will is the old ‘Xeqlay Gizat’. That is dead and buried 40 years ago, but unfortunately that evil spirit of empire is burnt into your soul! You can lament to the end of your time!

 6. የፌዴራል ስር ኣት ኣበይት ጥቅሞች መሀል፣
  1 . ረጂም የመንግስት ሰንሰለቶችን በማሳጠር፣ዜጎች መሪዎቻቸውን በቅርብ ለማግኘት እና ለመቆጣጠር እኒድያስችላቸው . የኦሮሚያና ኣማራ ክልሎች ከመጠን ያለፈ መንቦራቀቅን /Unmanageable and remote access to authorities by average citizen of the region/ ፣ በኒሻጉል አና ሃረሪን ባንጻራዊ መልኩ እጅግ ማነስን ልብ ይሉኣል።/ They cannot even cover the very basic necessities of their inhabitants /
  2. የፌዴራል ኣስተዳደሮች ኣንዱ ካንዱ በረሶርስ/ resources / እና በፖለቲካዊ ሀይል/ political power / ተመጣኝ በማድረግ ጤናማ የሆነ ውድ ድርን ማበረታታትን ያካትታል።/ see the above /
  ለህዝብ ቆመናል የሚሉ በጥቅም ጥማት ናላቸው የዞረ ፖልተከኖች ምን መልስ ኣላቸው???
  ደምቢዶሎ ያለው ዜጋ ጉዳዩን ለማስፈጸም ለቀምት መሄድ ይቀለዋል ??? ወይስ ፊን ፊኔ ??
  በተመሳሳይ ኮምቦልቻ ያለው ደሴ ይቀርበዋል ?? ባህር ዳር ??
  እንደ እኔ ለህዝብ መልካም ኣስተደደር ፣ ተመጣጣኝ እድገት ፣ፍጹም ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ኣማራ ክልል እንደቀድሞው ክፍለ ሀገሮች መመለሱ የሚደገፍ ነው።
  ኦሮሚያ ከፌዴራላዊ ኣመራር ኣንጻር ግቡን የማይመታ መቦራቀቅ ስለሚስተዋል ቢያንስ በሶስት(3) ቦታ ማለትም ደቡብ ኦርሚያ ፣ ማእከላዊ ኦሮሚያ ወይም ሸዋ፣ አና ምእራብ ኦሮሚያ መከፈል ይኖርበታል።
  ክፍለ ሀገር ሲነሳ ኣንዳድ ኣክቲቪስቶች ነን ባዮች ወደ ድሮ ፊውዳል ስር ኣት መመለስ ነው ሲሉ ይደመጣሉ።ይህን የሚሉት ክድንቁርና ይሁን ህዝቡን ኣያቅም በሚል ንቀት ኣልገባኝም።
  የዲሞክራሲ ቁንጮ የሆነችው ፈረንሳይ በኣሃዳዊ / unitary , not Federal /መንግስት በክፍለ ሀገር / ጠቅላይ ግዛት ተከፋፍላ የምትተዳደረው። ቻይናም እንዲሁ ።
  ከሁሉም በላይ ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ፣ በግርግር የጸደቀው ህገ መንግስት ያስቀመጠው የጎሳ ሉኣላዊነት ተቀዶ ሉኣላዊነት ለኢትዮጵያ ህዝብ በሚል መተካት ይኖርበታል።
  ስግብግብነት ይጥፋ !!
  ወንድማማችነት እና እኩልነት ይለምልም !!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.