ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለCGTN, Arabic Service ከሰጡት ቃለ-ምልልስ የተወሰደ!! በአማርኛ ተተርጉሞ እንደቀረበው

“…በሕይወትህ የተደሰትክበት ቀን ላልከኝ፣ እንደ መሪ ሳይሆን
እንደ ግለሰብ ብዙ ማለት ይቻላል። ዩንቨርስቲ የገባህበት፣ ትዳር የያዝክበት፣ ልጅ የወለድክበት፣ ደርግ የወደቀበት ወዘተ።

በአጥንትና ደሜ ምዬ የምናገረው ግን አሁን ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ከተስማማንበት ቀን የላቀ ደስታ የለኝም። ለዚህም አብይን ላመስገነው እፈልጋለሁ።

እኔ አርጅቻለሁ። ብዙ ዘመን የለኝም፣ በአብይ አመራር ግን የወደፊቷ ኤርትራ ጉዳይ አያሳስበኝም።

ወያኔ ብዙ ቢናገርም እኛ ለኢትዮጵያውያን ነፃነት እንጂ ክስረት አስበን አናውቅም።
እመነኝ እኔ አላስመስልም አልሰርቅም።”

“ሃያ ሰባት ዓመት ስለ አማራ ክፋት ተናግረን አማራው እንዴት በፍቅር እንደ ተቀበለን ሳይ አንገቴን ደፋሁ።

ኢትዮጵያውያን ለኛ ያላቸውን ንፁህ ፍቅር በሕይወቴ ሳለሁ ቆሜ ከማየት በላይ ምን ደስታ አለ?”

“ሆኖም በኢትዮጵያ ወንድሞቻችን ላይ እዛም እዚህም ሞት አለ።

ይህን እያየን እኛም በሰላም አንተኛም፣ የተሟላ ሕብረት አይኖረንም።

ይህን የከሳሪዎች ሴራ ደግሞ ግዜ ቢፈጅም እናሸንፋለን። እኛ ኤርትራውያን ለወንድሞቻችን ሰላምና ደህንነት ጦር፣ ጉልበት፣ ግዜ ብቻ ሳይሆን በግሌ ሕይወቴን ለመስጠት ዝግጁ ነኝ። ይህ እምነቴ
ነው። በነፍሴ የምምለው ውሸት የሌለበት እውነት ነው።

ትርጉም ዳኒ ዐውፍ

2 COMMENTS

 1. ውድ ሳተናው፣
  ኢሳይያስ “ወያኔ ብዙ ቢናገርም እኛ ለኢትዮጵያውያን ነፃነት እንጂ ክስረት አስበን አናውቅም” አለ ነው የምትሉን??
  ይኸ አዲስ ነገር ነው! ኢሳይያስ በእርግጥ “ወያኔ ብዙ ቢናገርም እኛ ለኢትዮጵያውያን ነፃነት እንጂ ክስረት አስበን አናውቅም” ብሏል?
  ብሎ ከሆነ ኢሳይያስ ትልቅ የአእምሮ ችግር ገጥሞታል ማለት ነው! ማርጀት ብቻ ሳይሆን ጃጅቶ የተናገረውን ወደ መርሳት ተሻግሯል፤
  የሚለው ጠፍቶበታል፡፡ ወይንስ የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ያስተላለፈው እንዳይሆን! የአቀባዩ እድሜ 27 ኣመት ቢሆነው ነው፤
  የገረመኝ ሳተናው ይህን አስተርጉሞ ማቅረቡ ነው፤ ያውም ከዐረብኛ፡፡ ሳተናውም እንደ ኢሳት የኢሳይያስ ቲቮዞና ፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ሆኖ እንዳይሆንና
  ተስፋ ያደረግነው ሁሉ እንዳይጨልም አደራ!

  ኢሳይያስ እንኳን በውኑ በህልሙም ይህን አይልም፤ ይልቅ ስም በማጥፋት ወንጀል እንዳትከሰሱ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.