የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽንን ማቋቋሚያ አዋጅ ፀደቀ

የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በሕግ ይፅደቅ ወይንስ አይፅደቅ የሚለው የህዝብ እንደራሴዎች አባላትን በእጅጉ ካከራከረ በኋላ ፀድቋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ከዚህ ቀደም ለምክር ቤቱ ቀርቦ ለዝርዝር እይታ ለውጪና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መመራቱ ይታወሳል፡፡
ረቂቅ አዋጁ እንዲፀድቅ ዛሬ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት ግን ይፅደቅ አይፅደቅ በሚለው በሁለት ጎራ ተከፍለው ሰፊ ክርክር አድርገዋል፡፡
አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት የማንነትንና የአስተዳደር ወሰንን በተመለከተ ስልጣን የተሰጠው ለክልሎችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የኮሚሽኑ መቋቋም የህገ መንግስቱን አንቀፆች የሚንድ ነው፣ አዋጁ ለመፅደቅ ለምክር ቤቱ ከመቅረቡ በፊት ክልሎች ተወያይተውበት መስማማት ላይ መድረስ ነበረበት ሲሉ ረቂቅ አዋጁ እንዳይፀድቅ ተከራክረዋል፡፡
ሌሎች ደግሞ፣ ኮሚሽኑ ለዘመናት በአስተዳደር ወሰንና በማንነት ጥያቄ ምክንያት ሲቆራቆሱ የቆዩ ሕዝቦችን ሰላም ይመልሳል ሲሉ አዋጁ መፅደቅ አለበት ብለው ሞግተዋል፡፡
ኮሚሽኑ የተሰጠው ስልጣን ለግጭት ምክንያት የሆኑ የወሰንና የማንነት ጉዳዮችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማጥናት ምክረ ሀሳቦችን ለፌዴሬሽን ምክር ቤትና ለሚመለከተው የመንግስት አካል የማቅረብ ሀላፊነት ይኖረዋል፡፡
ኮሚሽኑ በራሱ ውሳኔዎችን የማሳለፍ ስልጣን አልተሰጠውም፡፡
በመሆኑም፣ የየትኛውንም ተቋም ስልጣን አይጋፋም፣ የህገ መንግስቱን አንቀፆች አይሸረሽርም ሲሉ ከፊሎቹ አባላት አዋጁ እንዲፀድቅ ተከራክረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ዜጎች ሲኮላሹ፣ ሲገደሉና ሲሰቃዩ ይህ ምክር ቤት ህገ መንግስት ተጣሰ፣ የሚል ቃል ወጥቶት አያውቅም ያሉት አባላቱ ዞር ብለን አይተነው የማናውቀውን ህገ መንግስት ሲመቸን ብቻ እንደፈለግን እየተረጎምን ልናወራበት አይገባም ሲሉም አዋጁ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.