ህወሓት የምርጫ ኣስፈፃሚዎች በገንዘብ እየገዛች ነው!…… አምዶም ገብረ ስላሴ

በመቐለ ከተማ ሓድነት ክፍለ ከተማ የሚገኙ 5 ቀበሌዎች ኑዋሪ የሆኑት 30 የምርጫ ኣስፈፃሚዎች የምርጫው ው ጤት ለህወሓት ኣሳልፈው እንዲሰጡ በማለት ለ3 ወር የሚቆይ ስራ ተደራጅተው ይሰሩ ከነበሩ ወጣቶች ተቀምቶ ተሰጣቸው።

ከየንዳንዱ ቀበሌ 6 የምርጫ ኣስፈፃሚ የተመለመሉ ሲሆኑ ከመነሃርያ (ኣውቶቡስ ተራ )ስራ የሌላቸው ተደራጅተው ይሰሩት የነበረው የገበያቀን(የከብቶች ገበያ) ቀረጥ የመሰብሰብ ስራ ሲሆን ወጣቶቹ በሳምንት እስከ 10 ሺ ብር ገቢ ያገኙበት የነበረው ስራቸው ድንገት ለምርጫ ኣስፈፃሚዎች ተሰጥቶባቸዋል።

ወጣቶቹ የስራቸው ቀነ ገደብ 3 ወር ቀርቶበት የነበረው ሲሆን ለዚሁ የሚሆን ከ20 ሺ ብር በላይ የወጣበት ሰነዶች ኣዘጋጅተው እየሰሩ እያሉ በቃቹ መባላቸው ኣግባብነት እንደሌለውና መፍትሄ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ለክፍለ ከተማው ኣስተዳዳሪዎች ኣብዮቱታቸው ያቀረቡ ቢሆኑም ሰሚ ኣላገኙም።

የህወሓት ውሳኔ 1) የህዝብ ድምፅ ለመዝረፍ የህዝብ ገንዘብ ያለኣግባብ መጠቀማቸው።

2) በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው ይሰሩ የነበሩ ወጣቶች ያለ ኣግባብ ከስራቸው መባረራቸው

3) ምርጫው ፍትሃዊ፣ ሰለማዊ፣ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ጠቃሚ ከሆነው የምርጫ ኣስፈፃሚዎች ገለልተኝነት በገንዘብ ደልሎ ኣገልጋይ ማድረጋቸው ነው።

ህወሓት ለነዚህ የምርጫ ኣስፈፃሚዎች በህዝብ ገንዘብ ገዝቶ ምርጫው ሊያጭበረብር መወሰኑ ስርኣቱ ምን ያህል የራስ መተማመኑ እንደተሸረሸረ፣ ምን ያህል ከህዝቡ እንደተነጠለና እንደተ ጠላ የሚያመለክት ነው።

የህዝብ የምርጫ ታዛቢነት እንደ የስራ እድል እየተጠቀሙ ያሉት ወገኖችም ከህሊናቸው ሆዳቸው እንዳስቀደሙ የሚያሳይ ኣፀያፊ ስራ ነው።

ሰብ ክሳብ ዝፀልኣካ ዕድመ ኣይሃብካ( ስው እስኪ ጠላህ እድሜ ኣይስጥህ ) የሚባለው ኣባባል ኣሁን ለህወሓት ስርዓት ትክክለኛ መገለጫ ሁነዋል።

ነፃነታችን በእጃችን ነው..!አምዶም ገብረ ስላሴ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.