የብሔርተኝነት ጉዞ! (አበበ ወዛ አንጣሎ )

ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ በብሔርተኝነት ከልሎ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተጓዘበት የጥፋት መንገድ ነው። የኢትዮጵያን ዘሮች አንድነት የሚያራርቅ ጠባብ፣ በግለኝነት በክልል ላይ የተመሰረተ የድንበር ግጭት መንስኤና ምክንያት ሆኗል። የብሔር ፌደራሊዝም ከ27 ዓመታት በላይ የወያኔ ሥርዓት የበላይነትን ያጎናጸፈ፣ የአንድ ዘር ጥቅም አስከናሪና አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ቀለም ምልክት የሆነችውን አርማችንን የቀየረ፣ አንድነታችንን ያናጋ ሕወሐት በደደቢት ተራራ ያበቀለው ኢትዮጵያዊነትን በዘረኝነት ያጨቀየን መርዝ ነው።

ሕዝብን በዘሩ ከፋፍሎ ለመግዛት መሞከር ለኢትዮጵያችን አያስፈልጋትም ስል ከማንም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ላይ ምንም ጥላቻ የለኝም። እኔ የተወለድኩት በጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር በጎፋ አውራጃ ሲሆን ያደግኩትና የተማርኩት ከሁሉም የኢትዮጵያ ዘሮች ጋር ነው። ለከፍተኛ ትምሕርት ዕድል ወደ ሩሲያ ሄጄ በኋላም ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ፋንታ ወደ አሜሪካን አገር ከኮበለልኩ። በአሜሪካ አገር ሳለሁም ወያኔ በምዕራባውያን ተደግፎ መለስ ዜናዊ ከለንደን ኢትዮጵያ ሲገባ፡ መድኅን የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በኮሎኔል ጎሹ ወልዴ በአሜሪካ ሲመሠረት መሥራች አባል በመሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ አደገኛ የፖለቲካ ቀውስ እንደወደቀበት ዲያስፖራው በአገሩን ፖለቲካ እንዲሳተፍ ስንቀሰቅስ የዓለም ሕዝብ የወያኔን አጥፊነት እንዲረዳ በሰፊው ስናጋልጥ በግንባር ቀደም ተሳታፊ ነበርኩ። ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ ትውልድ አገሬንና ቤተሰቦቼን ለማዬት ኢትዮጵያ እንደ ተመለስኩ ከጥቂት ቀናት በኋላ በአዲስ ዘመን ጋዜጣና በአሜሪካ ራዲዮ በሽብርተኛነት ፍርጃ ታውጆብኝ ከቤት ሳልወጣና ምንም ቦታ ሳልጎበኝ ወደ አሜሪካን አገር የተመለስኩ ኢትዮጵያዊ ነኝ።

ብሔርተኝነት ሲወሳ ያለፈውን ታሪካችንን የነ አፄ ምንሊክን ዘመን የአንድነትን ተጋድሎን ያስታውሰናል። ፖለቲካ ያለፈውን እያወሱ መወነጃጀልና በቂም በቀል መንፈስ የምናራምደው ሳይሆን የነገን በማለት በተስፋ ለመጪው ትውልድ ማሰብን ያስተምረናል። ከጫካ ትግል ወደ ሥልጣን የመጡ የወያኔ/ሕወሐት መሪዎች በታጠቁት ጥላቻና ከተፈጥሮ ጋር ከተያያዙ ችግሮች የበቀሉ ናቸው።

 1. የትግራይ ግዛት በተፈጥሮ መሬቱ ደረቅና ድንጋያማ፣ ለእርሻ ባለመመቸቱና በቆዳ ስፋትም ትንሽ በመሆኑ ወያኔ ሥልጣን እንደያዘ ኢትዮጵያን በክልል መከፋፈል በትግራይ ክልል የግዛት መስፋፋት ምክንያት በወልቃይት፣ በራያ፣ በአፋርና በቤንሻንጉ እንዲሁም በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የድንበርና የማንነት ችግሮችን ፈጥሯል። ለእርስበርስ ግጭት ምክንያት ሆኗል።
 • የቀድሞው የተማሪዎች ንቅናቄ በትግራይ ልጆች ላይ ያመጣው የፖለቲካ ንቃት እነ መለስ ዜናዊን የመሳስሉትን የአልባኒያ ኮሚኒስቶች በትግራይ የነጻነት ትግል ተደራጅተው ኢትዮጵያዊነትን ለማዳከም ሕወሐት/ወያኔን ማኒፌስቶ በደደቢት ተራራ ሥር በመንደፍ በትግራይ ነጻነት ስም ሕዝባዊ ሐርነት የመጀመር ምክንያት ሆነ፣
 • አማርኛ ቋንቋ ከነበረው ሰፊ ስርጭት አኳያ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመንግሥት ቋንቋ በመሆኑ ሕወሐት የአማራን ሕዝብ እንደ ገዢ መደብ አድርጎ በመፈረጁ ወያኔ ሥልጣን እንደያዘ በኢትዮጵያ የጎሳ ጭቆና እንዳለ አድርጎ ኢትዮጵያዊነት በየአቅጣጫው እንዲዳከም ተደረገ።

የሕወሐት ጐጠኛ መሪዎች የ27 ዓመቱ የግፍ አገዛዝ አልበቃ ብሏቸው በክልላቸው መሸገው አንድነታችንን እየወጉ ነው። የትግራይ ሕዝብ ሆይ! ከአብራክህ የወጣሁ ነኝ ባዩ የሕወሐት/ወያኔ መሪ “የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው?”፥ “የላስታ አብያተ ክርስቲያናት ለኦሮሞው ምኑ ነው?” እንዲሁም “የጐንደር ቤተ መንግሥት ቅርሶች ለከምባታው ምኑ ናቸው?” አቶ መለስ እንዳለውና በዚህ ወቅት ዶክተር ደብረጽዮን በአንድ አጋጣሚ ለእኔ ከትምክተኛ ኢትዮጵያዊ የሱዳን ሰው ይቀርበኛል እንዳሉት ሳይሆን ኢትዮጵያዊው ወገንህ በባዶ እግሩ ከየአቅጣጫው በመምጣት በአድዋና በማይጨው ሕይወታቸውን በመሰዋት ማንነትህን ያስከበሩትን የውድ አባቶቻችን አጥንት አትርሳ። ዋጋ ለአጣውም የባድሜ ጦርነት ሰማኒያ ሺ ያህል ሕይወት የተሰዋውና አጽሙ እንኳ ተለቅሞ ያልተቀበረውና ዘለላ እንባ ያልፈሰሰለት የወንድምህ አጽም ይፋረድሃል። ዶክተር ምንም የሃሳብ ልዩነቶች ቢኖሩንም የሚቀርብህ ኢትዮጵያዊው ወንድምህ ነው።

1ኛ/ የትግራይ ሕዝብ ትናንት የኢትዮጵያና የሕዝቧ ታሪክ ግንባታ ማዕከል እንዳልሆንክ ሁሉ ዛሬ አንድነታችንና በማኅበራዊ ህልውናችን በአንተ ስም በሚነግዱ ከወያኔ/ሕወሐት መሪዎች ሳይሆነ ከኢትዮጵያውያን ወገኖችህ ጐን በመቆም በወያኔ/ሕወሐት መሪዎች ላይ ክንድህን ማንሳት ይጠበቅብሐል።

2ኛ/ የትግራይ ተወላጅ ያልሆኑ የወያኔ ሥርዓት አፍቃሪዎችና ጉርሻ ተቋዳሾች ከግል ጥቅም የኢትዮጵያን ጥቅም በማስቀደም ሕወሐት/ወያኔ እኩይ ተግባር መላቀቅና ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጐን በመሰለፍ ይፈለግባቸዋል።

1

3ኛ/ ማናችንም የኢትዮጵያ ልጆች በራሳችን በመተማመን በገንዘባችን፥ በዕውቀታችንና ባለን ሁለንተናዊ አቅም ሁሉ አንድ ኢትዮጵያን ለመገንባት ከራስ ብሔር አልፈን በፍቅር ትስስር በአንድነት በመደራጀት ወደ ሕዝባዊ ዲሞክራስያዊ ምርጫ ለመሄድ እራስን ማዘጋጀት ይጠየቃል።

4ኛ/ ለወያኔ መጠቀሚያ መሣሪያ እዳንሆን በተፎካካሪ ኃይሎች መሃል የሚከሰቱትን ልዩነቶችን ሆኑ ቅራኔዎችን ማጥበብ። በፖለቲካ ስጥቶ መቀበልን መማር፣ በሐሳብ ወደ ሚያስማማን አማካይ መምጣት የኢትዮጵያዊነት ግዴታ መሆን አለበት።

5ኛ/ ማንኛችንም የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተኛል ባይ ግለሰብ፥ ቡድኖች፥ የፖለቲካ ድርጅቶች፥ ከግል ጥቅምና ከሥልጣን ጥማት ከዘረኝነትና ራስን ከማኰፈስ ተላቆ ከዘረኝነት ኢትዮጵያዊነት፥ ከግለኝነት ሕዝባዊነት በማስቀደም ሕዝቡን በአንድ በኢትዮጵያ መንፈስ ማደራጀትና ለመምራት ብቁ ሆኖ መገኘት።

6ኛ/ ወይኔ አንድነታችንን ከሚፈታተንበት በርካታ ፈርጆች ጥቂቶቹን በሐይማኖትና በክልሎች የድንበር (መሬት) ጉዳይ ነው። የሕዝባችንን አንድነት መሰነጣጠቅና ደም ማቃባት ዋነኛው የወያኔ ተግባሩ ሰለሆነ ሕዝባችን ይህንን የወያኔ እኩይ ተግባር ተረድቶ ያለአማራጭ መደራደርና መቻቻልን ማስቀደም። ኢትዮጵያዊ በትውልድ ክልሉ መወሰን ብቻ ሳይሆን በዜግነቱ በየትኛውም የኢትዮጵያ ግዛቶች በነፃ ተንቀሳቅሶ፣ ሠርቶና ኃብት አፍርቶ የመኖር መብቱ መጠበቅና መቻል አለበት። የቡራዩ ዓይነት አረመናዊ ግድያ በማንም የኢትዮጵያ ዘሮች ላይ መደገም የለበትም። ገዳዮችም ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።

የትግራይ ታጋዩች ያመጡትን በጥላቻ ላይ የተመሠረተ ዘርን ከዘር በማጋጨት የተነደፈውን የብሔር ፖለቲካን በዚህ ወቅት የምናራምደው ምን ለመሆን ይሆን? የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የትግሬ ወይስ የእየአንዳንዳችን ዘሮች የብሔር/ብሔረሰቦች መንግሥት ለመመሥረት ማለት ነው? ይህ ድርጊት አብሮ በመኖር ዙሪያ ችግር የሚፈጥር ሲሆን በይበልጥም በየክልሉ ተበታትኖ ተዋልዶና ተቀላቅሎ ያለውን የአማራን ዘር የሚያስጠቃ ነው።

ኢትዮጵያውነት ከብሔርተኝነት በላይ የሚመዝን በመሆኑ ብሔርተኝነት ጠባብነት ነው። አመለካከታችን ከሰፈርና ከጎሳ ወጣ ብሎ በኢትዮጵያዊነት ላይ ያተኮረ ሆኖ፤ በምድሯ ስንፈጠር ዘርን በምርጫ የወሰድነው ሳይሆን እግዚአብሔር የሰጠን ጸጋ በመሆኑ በመወለድ እትብታችን ከኢትዮጵያ አፈር በመቀበሩ ከአፈሯ በመቀላቀላችን በእኛነታችን ኮርተን በአንድነት ላይ የተመሰረተ ልዩነታችንን አምነን የኢትዮጵያ ዜጎች በምድሯ የበቀልን አበባዎች እንደ መሆናችን መጠን ጎሳን ተከትሎ የሚመጡ እንቅፋቶችን ማጥበብና ማስወገድ። የሰው ዘር መገኛ በመሆናችን ለብዙ ዘመናት በሰላም አብረን ኖረናል ። ወደፊትም አብረን እንኖራለን። ከአንገት በላይ ሳይሆን በመሰረታዊ የሰው ልጆች መብት እኩልነት ማመን አለብን። አዲስ አበባ በጋሞ ቋንቋ “ቱንጋ” ትባላለች። የኢትዮጵያ መንግሥት መናገሻ ከተማ እንደ መሆንዋ መጠን አንዳንዶች እንደሚሉት ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ከተማ ናት። በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች ለምሳሌ የጎጃም ሰፈር፣ ወሎ ሰፈር፣ የጎፋ ሰፈርና በሌሎች ሌሎችም ስም የሚጠሩ ቦታዎች አሉ። እነዚህ ቦታዎች አገራችን በጠላት በተወረረችበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን ለማዳን ከተለያዩ አካባቢዎች ለዘመቻ በመምጣት አርበኞች የሰፈሩበት ቦታዎች ናቸው። ለነፃነታችንና ለአንድነታችን በጋራ መቆማችን በኢትዮጵያዊነት አስከብሮናል። የወደፊት ሐላፊነቱም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው።

ወያኔ ከሰማኒያ በላይ የኢትዮጵያ ዘሮችን በጎሳ ከፋፍሎ አደራጅቶና አጋጭቶ ኢኮኖሚዋን አራቁቶ ከጨረሰ በኋላ ዛሬ እንደ ምሳሌ የአማራው ፓርቲ “እንደ ሚዛን” አስጠባቂ የትግል ስልት በማስመሰል በብሔር ፓርቲ መደራጀት መጀመሩ በወያኔ ዝርፊያ ከተራቆተው የኢትዮጵያ ካዜና እጅ ለማስገባት ከሆነ፤ “ጅብ ካለፈ ወሻ ጮሄ” እንዳሉት፣ ተርፎም ከወያኔ ጋር የሥልጣን ፉክክር ከሆነም የተዛባ አመራርን ለማጎልበት ከድጡ ወደ ማጡ የቁልቁል ጉዞ መሆኑ ነው። በዬትም አገር ተቀባይነት የሌለውና በዓለም ላይ ብቸኛን ዘርን መሰረት ያደረገ የብሔር ፌደራሊዝምን ለማጠናከር ወያኔ ላለፉት 27 ዓመታት ሲሠራ ቆይቷል። ዛሬ ደግሞ አማራውን ዘር ከሌላው ዘር ለይቶ “የአማራውን ሕዝብ ጥቅም ለማስከበር” በማለት ማደራጀቱ የአማራው መሪዎች ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያደረሰውን ስህተት ሊደግሙ ነው የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም። ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሆነ ለአማራው ሕልውና ጥሩ አይደለም። ለኢትዮጵያ አንድነት እንቅፋት ይሆናል። በተጀመረው ሰላማዊ ለውጥ ላይም ችግር ይፈጥራል። በኢትዮጵያ እንደ ቋንቋው ብዛት ክልል ጥየቃው ይበዛል። በብሔር ፓርቲዎች መደራጀት ትላልቅ የክፍፍል ግርግዳዎች በኢትዮጵያ ሕዝቦች መሐል መገንባት ማለት ነው። ፓርቲ ለሥልጣን የሚመራ ጎዳና በመሆኑ በብሔ ጉዞ ማን ከማን ክልል ተመርጦ ማንን ሊያስተዳድር ይሆን? ወያኔ ኢሕአዲግ ነኝ በማለት በየክልሉ ተለጣፊዎችን በማስቀመጥና የምርጫ ሣጥኖችን በመስረቅ ለ27 ዓመታት በማጭበርበር ገዝቶናል። አሁን ለሚያጋጩን ችግሮች ሁሉ ዳርጎናል። ይህን ስህተት ማረም እንጂ ከስህተት ወደ ስህተት ተመልሰን መግባት የለብንም። ይህን የማይረዱ ጽንፈኛ ብሔርተኞች ብሔርተኝነትን ከሕብረብሔራዊነት አክብደው ስለሚያስቀምጡ ማናችንም አንድ ኢትዮጵያን የምንፈልግ ኢትዮያውያን በተለይም የአማራው ምሁራን ይህን ጠባብነት በለዘብተኝነት መመልከት የለበትም።

2

ወያኔ ኢትዮጵያን በጐሳ ሽንሽኖ፣ ብሔራዊ አንድነታችን አናግቶ ሲገዛ፥ አገር ሲገነጥልና ሲያስገነጥል ቆይቷል። በአገራችን ከብዙ መቶ ሺ በላይ ወገኖቻችን በወያኔ/ሕወሐት በእስር ቤት ማቀዋል። እናት፥ አባት፥ አዛውንት፥ ወጣትና ሕፃን ሳይባል ግንባራቸው ለወያኔ አጋአዚ ሠራዊት ኢላማ ሆነዋል። የሰው ሕይወት ክብር የታጣበት አገር አድርገውን ነበር። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህ ዓይነት ሥርዓት በቃን እያለን ነው፤ እኛም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተፎካካሪ ነን ባዮች ልዩነታችንን አጥብበን ወደ ተወሰኑ ፓርቲዎች በመምጣት በቃን በማለት ኢትዮጵያን እናስቀድም። የአሁኑ መንግሥት ወደ ምርጫ ሲወስደን በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን ተረካቢው አንድ ፓርቲ ብቻ ነው። በአገራችን የብሔር፣ የሰፈር፣ የጎሳ፣ የአንድ ዘር ነፃ አውጪና ግንባር ብዛቱ መጠን የሌለው ቢሆንም በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝቦች የተመረጠ ሕብረብሔራዊ ፓርቲ አመራርና ሰላማዊ ሥርዓት ለማምጣት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለፉክክር እንዲመች እንደሌላው አገር ፓርቲዎች ከአምስት በታች መሆን አለባቸው። በጃንሆይ ዘመን የፓርላማ ምርጫ እንጂ የብሔር ምርጫ እንዳለ አላውቅም። በደርግ ዘመን ተፎካካሪ ነኝ ባይ ፓርቲዎች በተገኘው መድረክ ሥልጣን በያዘው ላይ ሳይሆን ትግሉ እርስ በርስ መነታረክ በመሆኑ የወያኔን ዕድሜ አራዝሞታል። ከአሁኑ በኋላ አገር ለመምራት ብቁ ነኝ የምትሉ የፓርት መሪዎች “እንደ ሰው” በአገራችን ችግሮች ላይ በማትኮርና ሕዝቡን በማንቃት ችግሮችን ተወያይቶ ለመፍታት መቻልና አገር የመምራት ብቃትን የመካን አለባችሁ። ከትውልድ ወደ ትውልድ እርስ በርስ እየተፋተግን ከመኖር ዲሞክራሲያዊ ምርጫና ሰላማዊ ሥርዓት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማምጣት በቅንነት አብረን እንድንነሳ አደራ እላለሁ። ኢትዮጵያ የሁላችን አገር ናት።

ከአበበ ወዛ አንጣሎ abebew@yahoo.com (619) 200 6245   ሳንዲያጎ ካሊፎርኒያ አሜሪካ።

2 COMMENTS

 1. The Ethiopian peoples have been suffering from man-made political syndrome of a century old which was created by greedy politicians all the times so far. All these politicians have never cared about collective and individual rights. That is why we are still struggling against all sorts of odd ideologies,  mentalities and thinking. The century old struggles of the peoples in Ethiopia have produced most of the political organizations like TPLF, OLF, ONLF, SLF and EPLF. No one of them were created by default or by accident.

  The current ethnic federal structure of Ethiopia is the political arrangements which were mainly constructed and promoted by the beloved Oromo intellectuals and OLF leaders like Gelassa Dilbo,  Lenchoo Lataa,  Dima Nagawo and others. The TPLF has accepted it by making few modification. The TPLF tried to implement it at least nominally after banning the OLF, in order to win the hearts of the Oromo nation. Therefore, the main shareholder of this federal arrangement is the OLF, the freedom fighter. Accusing the TPLF in regard of the federal structure is unfair. The TPLF must be accused for shortcomings of the implementation and wrong boundaries.  Thus, this federal structure was not implemented at the free will of the TPLF. It is a fruit of the century old bitter struggles of the Oromo nation in particular and other subjugated nations in general. Consequently, accepting these federal arrangements is a must for all stockholders. The political merchants like Ginbot 7 make only noises temporarily which will not last long. Watch out!

  Narrow nationalists are those who are against the democratic rights of the differet nations in Ethiopia. They have been using always derogatory terminologies in order to undermine the demands of the Oromo, the Sidama and all other nations. Such efforts are futile and a sign of desperation and hopelessness. No more business as a usual. You should have to swallow these naked realities.

 2. Dear Abebe, I do believe your ideas will only work if the issue at hand was between equals in terms of ability and commitment. Unfortunately the reality on the ground is different. Blaming woyane is not gonna find solutions at all at a minimum you should point your fingers to all members of EPRDF. Isolation techniques are not enough. It is time to wake up and put pressure on those in power who ever they are. They still do not want to solve the issue, even though they know what should be done. By now every one should know the enemy includes those who call themselves oromo nationalists. also by now we should all know and admit there has never been peoples struggle in Ethiopia but struggle by interest groups who imposed themselves. If you were a student in the 60’s at the university you certainly should know this fact. One of the biggest lies in
  Ethiopia “peoples struggle” deciphered unashamedly. Applies to all interest groups, TPLF, ELF, OLF, Derg etc. In the end understanding and accepting this truth will be the answer to all problems.
  Poor Gemeda, your views are always anti-oromo although you think you are pro-oromo. You just told everyone the cause to the problems in Ethiopia are the oromos’. What are you thinking? You should stop making the cause to all ills in Ethiopia. The fact of the matter is, your so called beloved oromo intellectuals haven’t done anything to the oromo gossa other than pain and suffering. Re. thousands jailed hundreds killed because of their half baked ideas and policies. My suggestion to you my brother is stop writing for a while until you figure out things.
  Enqoqo

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.